የኢትዮጵያ ባንዲራ የያዙ እና የኦነግ ባንዲራን ያነገቡ ደጋፊዎች በዶሀው የአትሌቲክስ ውድድር ፍጥጫ ውስጥ ናቸው

በዶሀው የአትሌቲክስ ውድድር ለሁለት የተከፈሉት የኢትዮጵያ ደጋፊዎች!

ጀምስ ኤሊንግዎርዝ የAP አትሌቲክስ ሪፖርተር ሲሆን በኳታር፣ ዶሀ እየተካሄደ ያለውን የአትሌቲክስ ውድድር ከስፍራው እየዘገበ ይገኛል።

ትናንት የላከልኝ መረጃ እንደሚያመለክተው በአንድ በኩል ልሙጡን የኢትዮጵያ ባንዲራ የያዙ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባንዲራን ያነገቡ ደጋፊዎች ፍጥጫ ውስጥ ናቸው።

እንደውም ከትናንት በስቲያ በአንድ አጋጣሚ ወደ ፀብ ሊገቡ ብለው በፀጥታ አካላት ጣልቃ ገብነት ጉዳዩ እንደተረጋጋ ጨምሮ ገልፁዋል። “ያልተለመደ እና ከአትሌቲክስ መንፈስ ያፈነገጠ” ብሎ በገለፀው ጉዳይ ላይም ዛሬ ከሰአት ዜና እንደሚሰራ ጠቅሷል።

Via : Elias Meseret