ሕፃናቱ በየትምህርት ቤታቸው መመገባቸውን እንደበጎ ተግባር ብንወስደው መልካም ነገር ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በረሐብ ራስን ከመሳት ወደ ተረጋግቶ መማር – (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ሕፃናት በረሐብ ምክንያት በየትምሕርት ቤቱ ራሳቸውን እየሳቱ እየወደቁ ነው የሚሉ ዘገባዎችን በቅርብ አመታት ውስጥ በተደጋጋሚ ስናዳምጥ ከፍተኛ ቁጭት አድሮብን ነበር ።

የኦዴፓው ከንቲባ ታከለ ኡማ ገንዘቡን ከኪሱም ያውጣው ፣ ለምኖም ያምጣው ፣ ከመንግስት ካዝናም ያውጣው ፣ ከፈለገበትም ያመንጨው ገንዘቡ የዋለው ባለፉት አመታት ስንቆጭበት ለነበረው የሕፃናት ተማሪዎች ጉዳይ በመሆኑ በፍፁም ሊያሳስበን አይገባም።

ሕፃናቱን መመገቡ በዘላቂነት ይሁን ፣የምርጫ ስትራቴጂ ይሁን ፣ መሰረታዊ ድጋፍ ይሁን ፣ ለገፅታ ግንባታም ይሁን ፣ በጎፈቃደኞች ይሁኑ ፣ በወላጆች ላይ የስነ ልቦና ጫና ይሁን ፣ የፈለገ ይሁን ብሩም ከፈለገበት ይምጣ ዋናው ቁምነገሩ ለሚቀጥለው አንድ አመት ትውልድ በረሐብ ራስን ስቶ ከመውደቅ ወደ ተረጋግቶ መማር እንዲሸጋገር ሆኗል።

ስለዚህ ሕፃናቱ በየትምህርት ቤታቸው መመገባቸውን እንደበጎ ተግባር ብንወስደው መልካም ነገር ነው። ሲተችም እኮ አዋጪ የፖለቲካ ስልት መምረጥ ብልሕነት ነው። #MinilikSalsawi