መገዳደል፣ መጠላላት እና ወገንን ማፈናቀልን ከአሮጌው ዘመን ጋር አብሮ መተው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

መገዳደል፣ መጠላላት እና ወገንን ማፈናቀልን ከአሮጌው ዘመን ጋር አብሮ መተው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።

ቤተ ክርስቲያኗ አዲሱ ዓመት መፈቀቀር እና አንድነት የሚሰፍንበት እንዲሆን በመመኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፋለች፡፡

Image may contain: 2 people, beard

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወ እጨጌ ዘ መንበረ ተክለ ሃይማኖት “ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ በሰላም አሸጋገራችሁ” ብለዋል፡፡

“የዘመን መለወጫ በአል ገጸታው ፍፁም መታደስን የሚያበስር በመሆኑ አዲሱን ዓመት ስንቀበል ልባችንን በደንብ በማደስ መሆን ይኖርበታል” ብለዋል አቡነ ማቲያስ።

መለያየት፣ መገዳደል፣ ወገንን ማፈናቀል እና አብያተ ሃይማኖትን መዳፈርን ከአሮጌው ዘመን ጋር በመተው ለሰላም መትጋት እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።

አዲሱን ዓመት የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድት ማድረግ እንደሚገባም አቡነ ማቲያስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Walta