የመስከረም አራቱ ሰልፍ ከኦሮምያ ቤተክህነትና ከባልደራስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

DW : ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ አስር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተለያዩ ተቋማት ለመስከረም አራት 2012 የታቀደዉን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያስተባብሩ አዲስ አበባ ላይ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ገለፁ።

ተቋማቱ በመግለጫቸዉ ሰልፉ የሚካሄደው በቤተክርስትያኒቱና በምዕመናኑ ላይ እየደረሰ ያለዉ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ የቤተክርስቲያን መቃጠል፣ የካህናት መገደልና ሌሎች በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተቃጡ ጥቃቶችን ለማውገዝ መሆኑን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰልፉ ከኦሮምያ ቤተ-ክህነት ጋር እና ፤ ጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ እስክንድር ነጋ ከሚመራዉ ባልደራስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለዉ አስታዉቀዋል።

ጥያቄ ለመንግሥት አቅርበን የእንወያይ ጥያቄ ቀርቦልናል፤ የፊታችን አርብ መስከረም ሁለት ድጋሚ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን ሲሉ አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታዋህዶ ቤተ ክርስትያን ተቋማት ለመስከረም አራት የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ካስተላለፉ በኋላ በአዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ በእለቱ ተመሳሳይ ሰልፍ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።