" /> የአቃቂ ገበያ በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደረሰበት | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የአቃቂ ገበያ በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደረሰበት

የአቃቂ ገበያ በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት ደረሰበት

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ ትላንት ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ። በኮሚሽኑ በአደጋ ምላሽ ዘርፍ የአደጋ መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ አሳዬ ለኢቢሲ እንደተናገሩት የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና ህብረተሰቡ ባደርጉት ርብርብብ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአደጋው ወደ 60 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ቢወድምም 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ማዳን ተችሏል። በአደጋው በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተገልጿል። የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጠጣጠር 15 የአደጋ ተሽከሪካሪዎች ተሰማርተዋል፤ አምስት ቦቲ ተሽከርካሪ፣ አምስት ቀላል ተሽከርካሪ፣ ሁለት አምቡላንስ፣ 552 ሺህ ሊትር ውሃ ፣ ወደ 2 ሺህ ሊትር ፎም እንዲሁም 136 ሰራተኞች እና አመራሮች ተሳትፈዋል።

Via EBC
Photo via TIKVAH-ETH

Image may contain: one or more people, night and sky


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV