በአፈር መደርመስ አደጋ 4 ሰዎች ሞቱ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

(ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የመረጃ ኢንተለጀንስ ቡድን መሪ ሳጅን ጌታሁን ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ አደጋው የተከሰተው በወረዳው ጋንታ ካንቻሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በሚባል ስፍራ ነው።

አደጋው በአንድ ብሎኬት ማምረቻ ድርጅት ውስጥ መድረሱንም ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ የብሎኬት ማምረቻ ሰራተኞች አፈር በመቆፈር ላይ እያሉ በዙሪያው ከፍተኛ መጠን ያለው አፈር መደርመሱ መሆኑንም አስታውቀዋል ፡፡

ሳጅን ጌታሁን እንዳሉት በአደጋው በአፈር ቁፋሮ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ወድያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።

ከሟቾች መካከል ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

በቁፋሮ የወጣው የሟቾች አስክሬን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎለት ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱንም የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።