“እያጣራን ነው የምናስረው ቀርቶ”፣ ዜጎች በጅምላ እየታሰሩ ነው


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፣ በጋዜጠኛና ሰብ አዊ መንብት ተሟጋች እስክንድር ነገአ የሚመራውን የባንደራስ ባላደራው ምክር ቤትን በተመለከተ ጠንካር ታለ፣ ዛቻ አዘል ንግግር መናገራቸው ይታወሳል። ባላደራው የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ፍጹም ሰላማዊና ሕጋዊ መሆናቸው እየታወቀ ጠቅላይ ሚኒስተሩ፣ “ጦርነት እንገጥማለን” ማለታቸው በወቅቱ ከፍተኛ ተቃዉሞ አስነስቶባቸው ነበር።

በተመሳሳይ ሁኔታ የገዢው ፓርቲ የኦህዴድ/ኦዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊም  “በቄሮ ትግል ፌስታሉን ይዞ ከእስር ወጥቶ ሲያበቃ ዛሬ ‘ባለደራ መንግሥት’ ብሎ ራሱን መሾም አልያም ‘ባላተራ መንግስት’ ብሎ ለውጥን ማጣጣል በምንም ስሌት ተቀባይነት የለውም። መንግስታችንን ለመፈታተን ባለተራ ባላደራ እያለ የሚያላዝነውን ወደ ትክክለኛ መስመር ለመመለስ እንሰራለን” ሲሉ የባላደራዉን ሠላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሃሳብ እንዳለ ገልጸው ነበር።

የባላደራው ሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ በገዢዎች ስላልተፈለገ፣ ምክር በቱ የአዳራሽ ስብሰባዎችን ፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን በአዲስ አበባ ከተማ እንዳያደረግ በተደጋጋሚ ክልከላ የተደረበት ሲሆን፣ ያለፈው ሳምንት በባህር ዳር ህዝብ ጥያቂር ሰኔ 16 ቀን ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አስቦ የነበረ ቢሆንም በባህር ከአንድ ቀን በፊት በተፈጠረው ቀዉስ ስብሰባው ሊራዘም ችሏል።

ሰኔ 15 በአዲስ አበባ በባህር ዳር የተከሰተውው እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ተከትሎ፣ “የምናስርው አጣርተን ነው” የሚል አባባል ሲጠቀሙ የነበሩት የኦህዴዴ/ኦዴፓ አመራሮች የሚቃወሟቸውን ሁሉ ፣ እነርሱ የመፈንቀለ ሙከራ ብለው በጠሩት እንቅስቅሴ ተሳትፋቹሃል በሚል፣ ከተፈጠረው ቀውስ ጋር ያልተገናኙ ዜጎች እያሰሩ ነው።

ከዚህ በታች ያሉት አቶ ስንታየሁ ቸኮል የባላደራው ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የኢሳት የኦሮምኛ ክፍል ጋዜጠኛ የሆነው አቶ አማኑለም መግስቱ ነው።

በዚህ ጉዳይ ቢቢሲ የሚከተለውን ዘግቧል

——————————–

ግለሰቦቹ አንደኛ ተጠርጣሪ በሪሁን አዳነ፣ መርከቡ ኃይሌ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ጌዴዮን ወንድወሰን፣ ማስተዋል አረጋና አቶ ሐየሎም ብርሃኔ ናቸው።

ፖሊስ ግለሰቦቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት በአማራ ክልል ተፈፀመ በተባለው “መፈንቅለ መንግሥት” እና አዲስ በአበባው ግድያ “እጃቸው አለበት፤ በተለያየ ደረጃ ተሳትፎ ያላቸው ስለሆነ ጠርጥሬያቸዋለሁ ፤ ህገ መንግሥታዊ ስርዓት ለመናድ፤ በሽብር ተግባር ተሳትፈዋል።” በማለቱ እንደሆነ የአራቱ ጠበቃ የሆነው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ገልጿል።

አቶ መርከቡ ኃይሌና አቶ ስንታየሁ ቸኮል የምክርቤቱ አመራሮች ሲሆኑ አቶ ጌዴዮን ወንድወሰንም የባላደራ ምክር ቤቱ አባል ነው። አቶ በሪሁን አዳነ ጋዜጠኛ ሲሆን፤ አቶ ማስተዋል አረጋ የኮሌጅ መምህር መሆናቸውን የገለፀው አቶ ሄኖክ አቶ ኃየሎም ብርሃኔ ስለተባሉት ተጠርጣሪ ዝርዝር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።
ጠበቃው እንዳሉት ግለሰቦቹ በፀረ ሽብር አዋጅ መሰረት 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አደረጉት የተባለው ነገር ተለይቶ በዝርዝር የቀረበ ሳይሆን በደፈናው “በመፈንቅለ መንግሥቱ” ጠርጥሬያቸዋለሁ የሚልና ዝርዝር ያልቀረበበት ነው።

ስለዚህም በመፈንቅለ መንግሰቱ ይህን ይህን አድርገዋል ብለህ በሁሉም ተከሳሾች ላይ አቅርብ፣ በሁለተኛ ደረጃ በዛሬው እለት ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ይዞ ስላልመጣ እነሱ ደግሞ የተከበረው ፍርድ ቤት መዝገቡን ይይልን እነዚህን ሰዎች ለመያዝ ምንም የሚያስጠረጥር ምክንያት የለም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳታቸውን ጠበቃ ሔኖክ ተናግረዋል።

ክስ እንዳልተመሰረተ የሚናገረው አቶ ሔኖክ ማስረጃ ሊያሸሹ ስለሚችሉ በማረፊያ ቤት ቆይተው ምርመራው እንዲቀጥል ፖሊስ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ፖሊስ አደረጉት የሚባለውን ነገር በዝርዝር ለየብቻ እንዲያቀርብ፤ የምርመራ መዝገብ ይዞ ባለመቅረቡም፤ የምርመራ መዝገብ ይዞ እንዲቀርብ በማለት ለሐምሌ 17 ቀጠሮ ትእዛዝ መስጠቱንም ያስረዳል።
ግለሰቦቹ በትክክል መቼ እንደተያዙ ዝርዝሩን ባያውቅም ጥቃቱ ተፈፀመ ከተባለበት ከሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በኋላ ሰኔ 17 እና 18 መያዛቸውን ይናገራል።

ተጠርጣሪዎቹ ባህርዳር ሄደው ነበር ? ለሚለው ጥያቄ በሁሉም እርግጠኛ ባይሆንም ከሳምንት በፊት አቶ ስንታየሁ ወደ ባህር ዳር እንደሄደ፤ ባህርዳር የሄዱት በመኪና ባላደራ ምክርቤቱ እሁድ እለት ሊያደርገው ለነበረው ህዝባዊ ስብሰባ እንደነበር ሄኖክ አስረድቷል።

“ፖሊስ እንዳለው በስልክ እየተነጋገሩ ከጉዳዩ ጋር የተገናኘ ነገር ይፈፅሙ ነበር የሚል ጉዳይ አንስቷል። ፖሊስም ሁሉም ባህርዳር ሄደዋል ሳይሆን የሚለው ባህርዳር የሄዱትና ያልሄዱት ተሳትፎ አድርገዋል የሚል ነው” ሲልም አክሏል።

ስድስተኛው ተጠርጣሪ ጄኔራል ሰዓረና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ ሽኝት ፕሮግራም ላይ “የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባሉበት ጥቃት ለማድረስ መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል” በሚል ሲያዝ ግለሰቡም የጥበቃ ስራ ስለሚሰራ መሳሪያ እንደያዘ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን አቶ ሔኖክ ይናገራል።
BBC amharic