በሶማሌና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ በተከሰተ ጦርነት የሞትና የመቁሰል አደጋ ተከሰተ ።

በአፍደም በተከሰተ ጦርነት 3 ሰዎች ሲሞቱ ፣ 4 መቁሰላቸው ተነገረ ። በሶማሌ ኢሳ ጎሳና በአፋሮች መካከል ካለፉት ወራቶች ጀምሮ ሰላም ባለመኖሩ በየጊዜው ግጭቶች እየተከሰቱ ዜጎች ይሞታሉ ። ይፈናቀላሉ ። ይቆስላሉ ።

 

በሶማሌና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አከባቢ በተከሰተ ጦርነት ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ፣አራት ደግሞ መቁሰላቸውን ሲነገር አፋሮች የሶማሌን ልዩ ሀይል ሲወነጅሉ ኢሳዎች የአፋር ክልል ታጣቂዎችን ሲወነጅሉ ሌሎች የኮንትሮባንድ አመላላሾችን ይወነጅላሉ።

ከክልሉ ባለስልጣናት ይህ ጦርነት ለመነሳቱ ማረጋገጫ ተገኝቷል። በሶማሌና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በተከሰተ ጦርነት ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና አራት ደግሞ መቁሰላቸውን የሲቲ ዞን አስተዳዳሪ አስታውቀዋል።ዋና አስተዳዳሪው አቶ ኡመር መይደኒ እንደተናገሩት የሞትና የአካል ጉዳቱ የደረሰው በአፍደም ወረዳ ውስጥ ነው።ይህንንም አስተዳዳሪው ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን መናገራቸውን ገልጸዋል።አደጋው የደረሰው በወረዳው አደሌና አላሌ አርብቶ አደር ገጠር ቀበሌዎች በሚኖሩ አርብቶ አደሮች ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል።በወረዳው ባለፈው ወርም ጦርነት ተመሳሳይ ጉዳት ደርሶ እንደነበር ይታወሳል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US