ለምን ባለአደራውን እንደምደግፍ #ግርማካሳ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የባለ አደራ ድጋፍ ማህበር በአሜሪካ ተቋቁሟል። ያለፈው ሳምንት በአዉሮፓ ኢትዮጵያዊያን በለደን በነቂስ በሰላማዊ ሰልፍ ለባለአደራ ድጋፍ እንደሰጡ ይታወቃል።

የባለአደራው ንቅናኤ

አንደኛ – የተመሰረተው በአዲስ አበባ አስር ሺሆች በሚቆጠሩ ነዋሪዎች ነው። አገር በቀል እንቅስቃሴ ነው። ዳያስፖራ ያቋቋመው ወይንም በፌስቡክ የተቋቋመ አይደለም።

ሁለተኛ – አላማው እኩልነት ነው። አዲስ አበባ ሕብረብሄራዊነት መልኳን ለማጥፋት፣ በአዲስ አበባ የአንድ ጎሳ የበላይነትን ለመጫን፣ አንዽ ክልል ወይም ጎሳ ልዩ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ዘረኛ ቡድኖችን ለመመከት፣ በአዲስ አበባ ሁሉም እኩል ተጠቃሚ፣ ሁሉም፣ ዘራቸውና ሃይማኖታቸው ሳይታይ እኩል እንዲታዩ ለማድረግ የተመሰረተ ነው። የልዩ ጥቅም ሳይሆን የእኩል ጥቅም ተጠቃሚ መርህ ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው።

ሶስተኛ፡፡ ዱላና ቆንጨራ ይዞ፣ ሌላውን በማስፈራራትና በሌላው ላይ በመዛት ያል የተመሰረተ አይደለም። በብእርና በሐሳብ ላይ የተመሰረተ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ነው። ሰላማዊ በሆነ መንገድ በምርጫ የአዲስ አበባን ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሰራ ነው።በአንዳንድ ወገኖች መንፈቀለ መንግስት እየተባለ የሚወራው ወሬ፣ ትኩረት ለማስቀየር የሚወራ መሰረተ ቢስ ተራ ወሬ ነው። ምርጫን የሚፈራ፣ ህዝብ አይደግፈኝም ብሎ የሚፈራ አካል ካልሆነ በቀር ባለ አደራውን ከሰላማዊነት ውጭ በሌላ መፈረጅ ተሸናፊነት ነው።

አራተኛ – የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። ግን ለሕዝብ ቅርብ የሆኑ ፖለቲከኞች እነ ማን እንደሆኑ ለይቶ፣ ለነርሱ ድጋፍ ያደርጋል።

አምስተኛ – ሁሉን አቃፊ፣ ሁሉንም አሳታፊ ነው።፡የዘር ወይንም የሃይማኖት ልዩነት የለም። ጋሞ ሆንክ፣ ጉራጌ፣ ኦሮሞ ሆንክ አማራ፣ ሶማሌ ሆንክ ሲዳማ ዘርህ ምንድን ነው ? የት ነው የተወለድከው ተብለህ አትጠየቅም። ሰው መሆንህ፣ ኢትዮጵያዊ መሆንህ ብቻ በቂ ነው የሚል እምነት ያለው፣ inclusive የሆነ፣ የሰለጠነ አመለካከትን የሚያራምድ ንቅናቄ ነው።