ታላቅ ወገንን የመርዳት ዘመቻ በአዲስ አበባ ወጣቶች (ግርማ ካሳ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 21 – 2011ዓ.ም በሐገር ፍቅር  በአዺጽ አበአብ ወጣቶች ለሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ህይወት ማቆያ አስቸኳይ እርዳታ ለማሰባሰብ የተጀመረው ዘመቻ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ ነው። ወጣቶቹ በአገራቸው የመፈናቀል አደጋ የደረሰባቸው ወገኖቻችን ለመፈናቀላቸው ምክንያት የሆነው በዋናነት አገሪቱኢአ ያለው የዘር ፖለቲካን የዝሸር ፖለቲካውም የፈጠረው የዘርና ይጎሳ ግጭቶች መሆኑ ይታወቃል።

ሆኖም ፖለቲካውን ማስተካከል፣ ዜጎች በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ዘራቸውና ሃይማኖታቸው ሳይጠየቅ፣ ሳይፈሩ እንዲኖሩ በማድረጉ አንጻር ትልቅ ስራ መስራት እንዳለበት  ቢታወቅም.፣ ፖለቲካው በአንድ በኩል እንዲስተካከል ጥረት እየተደረገም፣ በአጓዳኝ ለተጎዱ ወገኖች መቆም አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያዊያን ግደታም ነው።

ከዚህም የተነሳ ነው ከሁሉም በፊት ሰባአዊነት ይቅደም በሚል የአዲስ አበባ ወጣቶች በአገሪቷ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማሰባሰብ ዘመንቻ የከፈቱት።

የማሪዮት ሆቴል፣ የአፍሪካ ዩኒየን፣ የኢትፖል ሴኪዩሪቲ አባላት ብዙ ድጋፎች አሰባብሰው ይሄን ዘመቻ እያንቀሳቀሱ ላሉ፣ እንደ አክቲቪስት ያሉ፣ እነ አክቲቪስት ያሬድ ሹመቴ ላሉበት ግብረ ሃይል እርዳታዎች አቅርበዋል።

የሐምሌ 19 ቁጥር 2 ተማሪዎች ብዛታቸው 400 የሚሆኑ እያንዳንዳቸው ከቤተሰቦቻቸው 1 ፓስታ እና 1 ሳሙና በድምሩ 400 ፓስታና 400 ሳሙና በመሰብሰብ  ለወገናቸው አስረክበዋል።

አስተባባሪቹ አሁን ለኢትዮጵያዉያን ጥሪ እያቀረቡ ነው። ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አስቸኳይ እርዳታዎች የሀገር ፍቅር ቴአትር የጀርባውን በር በመጠቀም በቅጥር ግቢ ውስጥ፣  “የአቅማችሁን ያህል አስቸኳይ እርዳታዎች ታመጡልን ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን” ይላሉ። አስተባባሪውፖቹ  ገንዘብ እንደማይቀበሉ አሳውቀዋል።

ለበለጠ መረጃ
መሐመድ ካሳን እና ያሬድ ሹመቴን በተከታዩ ቁጥር ያነጋግሩ።
094 014 0813