የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስካሁን የሠላም ሚንስትር የነበሩትን ብናልፍ አንዷለምን ሽረዉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለሥልጣን የበላይ ኃላፊ የነበሩትን መሐመድ ኢድሪስን በሠላም ሚንስትርነት ሾመዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት አቶ መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ የሠላም ሚንስትርነቱን ሥልጣን የተሾሙት ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ሕዳር 18፣2017 ነዉ።
አቶ መሐመድ ኢድሪስ ከመጋቢት 2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሐን ባለሥልጣን የበላይ ኃላፊ (ዋና ዳይሬክተር) በመሆን ሲያገለግሉ ነበር።
ከጥቅምት 2013 ጀምሮ የሠላም ሚንስትርነቱን ሥልጣን ይዘዉ የነበሩት አቶ ብናልፍ እንዷለም አዲስ የተሾሙበት ኃላፊነት ሥለመኖር አለመኖሩ የተባለ ነገር የለም።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ሥልጣን ከያዙ ከመጋቢት 2010 ወዲሕ በተደጋጋሚ የሚንስትሮችና የከፍተኛ ባለሥልጣን ሹም ሽር ያደርጋሉ።