ሕዝብን የማደራጀትስራ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች በሁሉም ክ/ከተሞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይደረጋሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሕዝብን የማደራጀትስራ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች በሁሉም ክ/ከተሞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይደረጋሉ

መጋቢት አንድ ቀን በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች “ አዲስ አበበ ለሁሉም ኢትይጵያ፣ ሁሉም ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ” በሚል መርህ ድምጻቸውን ማሰማታቸው ይታወቃል። በወቅቱም አዲስ አበባ ተወካይ ስለሌላት፣ አሁን በአመራር ላይ የተቀመጡት የአዲስ አበባን ሕዝብ የሚወክሉ ስላለሆነና መርጭ እስኪደረግ ድረስ ለአዲስ አበባ ህዝብ የሚሰራ የተደራጀ ሃይል መኖር ስለላበት፣ በአቶ እስክንደር ነጋ ለሚመራው ኮሚቴ በሺሆች የሚቆጠሩ የከተማ ነዋሪዎች ዉክልና መስጠታቸው ይታወሳል።

በዚህ መሰረት፣ “የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት” ተቋቁሞ ስራዉን ጀመሯል። አንዱና ትልቁ ስራም ሕዝብ የበክፍለ ከተማ፣ ወረዳ፣ ቀበሌ ማደራጀት ስለሆነ፣ ምክር ቤቱ በአንድ ወት ጊዜ ውስጥ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል። በቦሌና ቦሌ እና አቃቂ ቃሊቲ  ክፍለ ከተሞች ስብሰባዎች በማድረግ ይጀምራል።

ምክር ቤቱ፣  “ በአንድ ወር በሁልም ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ! ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በ10 ክፍለ ከተማ ሙሉ በሙሉ ሕጋዊ መዋቅር ለመዘርጋት እና የየክፍለ ከተማ ተወካዮች ለመምረጥ እንዲሁም ስለ-አዲስ አበባ ምክክርና ወይይት ይደረጋል፡፡

ይህ በአዲስ አበባ በሁልም ክፍለ ከተማ የተጠራወ ታላቅ ህዝባዊ ሰብሰባ ከመጋቢት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት “ባልደራስ” በየክፍለ ከተማ የሚካሄደውን ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ መራኀ-ግብር በቅደም ተከተል የሚገልፅ ይሆናል።

በዚህም መሰረት የቦሌ ክፍለ ከተማ እና አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ነዋሪዎች እሁድ መጋቢት 15/ቀን 2011ዓ.ም ከ 8 ሰዐት ጀምሮ እስከ 11 ሰዐት ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ጀርባ በሚገኘዉ የመድህን ዲኮር አዳራሽ ሁሉም የማይቀርበት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ተዘጋጅቷል፡፡ የሁለቱ ክፍለ/ከተማ
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በሚካሄድው ህዛባዊ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት “ባልደራስ” ጥሪውን ያስተላልፋል ፡፡

ድል ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ !!!!