የኦህዴድ/ኦዴፓ ሜዲያዉን የመቆጣጠር እርምጃ #ናኦሚን በጋሻው


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የኦህደድ/ኦዴ የስራ አስፈጻሞ ኮሚቴ አባል ናቸው። የዶ/ር አብይን ሹመት በማጽደቅ ፓርላማው ፣ የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ እንደመረጣቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማል።  አቶ ፍቃዱ በሃላፊነት፣  በኦሮሞ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ውስጥም ሰርተው የነበረ ሲሆን፣ በኦህዴድ አመራር አሉ ከሚባሉ ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው ይነገራል።

በአገሪቷ ውስጥ አሉ ከሚባሉ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ የመንግስት ሜዲያ አንዱ የሆነው ኢቢሲ፣ ለአመታት ህዝብን ገለልተኛ በሆነ መልኩ ከማገለገል፣ የገዢው ፓርቲ የፕሮፖጋዳ አውታር ሆኖ የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ኢቢሲ በፊት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ መረጃዎችን ለሕዝብ ማቅረብ መጀመሩም ብዙዎችን አስደስቷል።

ሆኖም በአሁኑ ወቅት ሕዝብ በኦህዴድ/ኦዴፓ ላይ ከፍተኛ ተቃዉሞና ትችት እያቀረበ ባለበት ወቅት፣ ኢቢሲ በኦሮሞ ክልል የሚፈጸሙ ግፎችንና ሰቆቃቸውን በስፋ በመዘገቡ፣  በኦሮሞ ክልል መንግስትና በኦህዴድ/ኦዴፓ  አመራሮች የተወደደለት አይመስልም።

ኢቢሲ ብቃት ባላቸው፣ ገለልተኛ በሆኑ ኢትዮጵያዉያ እንዲመራ በሚፈለግበት ጊዜ፣ የኦህዴድ/ኦዴፓ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ፍቃዱ የኢቢሲ የቦርድ ሰብሳቢ መሆናቸው፣ ኦህዴድ/ኦዴፓ የሜዲያዉን ነጻነትና ገለልተኛነት በመገደብ፣ ሜዲያው በፊት ህወሃትን ያገለግል እንደነበረውም፣ አሁን ኦህዴድ/ኦዴፓን እንዲያገለግል፣ የነበረውን አንጻራዊ ነጻነት እንደገና ለመገደብ ታስቦ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያስቸግርም።