የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ፣ ከአገራዊ ምክክር ሂደቱ ለመውጣት መወሰኑን አስታውቋል።
ፓርቲው ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ የምክክር ኮሚሽኑ በሀዋሳ ከተማ ሰሞኑን ከጀመረው የምክክር አጀንዳ ማሰባሰቢያ ጉባዔ ተወካዮቼ በግዳጅ እንዲወጡ ተደርገዋል በማለት ከሷል።
ፓርቲው አምስት ተወካዮቹ በመድረኩ ላይ የተገኙት፣ አጀንዳዎቹን እንዲያቀርብ በኮሚሽኑ በቀረበለት ግብዣ መሠረት እንደነበር ጠቅሶ ኾኖም ተወካዮቹ ለምን በግዳጅ ከመድረኩ እንዲወጡ እንደተደረጉ እንዳልተገለጠለት ጠቅሷል።
ፓርቲው፣ ድርጊቱ ኮሚሽኑ “ከገዢው ፓርቲ ጫና መላቀቅ ያልቻለ” መኾኑን የሚያሳይና “በገለልተኝነቱ” ላይ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብሏል።