ለውጥ ከራስ ይጀምራል! ጠ/ሚኒስትሩም ሆኑ ፕረዜዳንቱ እንደ ማንኛውም ተሳፋሪ ትኬት ቆርጠው መጏዝ አለባቸው፡፡

የእስራኤሉ ፕረዜዳንት “Reuven Rivlin” በኢትዮጲያ ጉብኝት ለማድረግ የመጡት እንደ ማንኛውም ተሳፋሪ በኢትዮጲያ አየር መንገድ ትኬት ቆርጠው ነው፡፡ በአየር መንገዱ ሰራተኞች መስተንግዶም ደስተኛ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡

በተመሣሣይ የታንዛኒያው ፕረዜዳንት “Magufuli” በኢትዮጲያ አየር መንገድ የኢኮኖሚ ክፍል ትኬት ቆርጠው ተጉዘዋል፡፡

በአንፃሩ የእኛ ጠ/ሚኒስትር ግን ኬኒያ እንኳን ለመሄድ አንዱን አውሮፕላን ላይ ለብቻው ይኮናተራል፡፡

ባለፈው ሰሞን ዶ/ር አብይ ባለስልጣናት አላስፈላጊ የውጪ ጉዞ ከማድረግ እንዲታቀቡ መመሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን፣ ራሳቸው አንዱን አውሮፕላን ለብቻቸው ተኮናትረው እየሄዱ ስለ አላስፈላጊ ወጪ መናገር የለባቸውም፡፡ ለውጥ ከራስ ይጀምራል! ጠ/ሚኒስትሩም ሆኑ ፕረዜዳንቱ እንደ ማንኛውም ተሳፋሪ ትኬት ቆርጠው መጏዝ አለባቸው፡፡ ይህ ሲሆን ከስራቸው ተሰግስገው የሚሄዱትን አላስፈላጊ ተጏዦች መቀነስ ይቻላል፡፡

መቼም ጠ/ሚ አብይ ከእስራኤሉ ፕረዜዳንት “Reuven Rivlin” ወይም ፕ/ት ሙላቱ ደግሞ ከታንዛኒያው ፕረዜዳንት “Magufuli” የበለጠ የደህንነት ስጋት አለባቸው ሊባል አይችልም፡፡ ስለዚህ የኢትዮጲያ ጠ/ሚኒስትር እና ፕረዜዳንት የአውሮፕላን ትኬት መቁረጥ አለባቸው!

Source: EthioThinkthank.com