Blog Archives
“ጅራፍ አጮህን አልሰማ አሉ፡ ነፍጥ አነሳን” በደቡብ ጎንደር የክምር ድንጋይና የአከባቢው ታጋይ አርሶ አደሮች!
“ጅራፍ እያጮህን የአፈር ማዳበሪያ ስጡን ብለን ጠየቅን፡ አልሰማን አሉ።እንደውም “የጅራፍ ፖለቲካ” እያሉ ተሳለቁብን። እቅዳቸው ከጦርነት የሚተርፈውን አማራ በረሃብ ለመጨረስ ነበር። እኛ ግን ቀድመን ስለነቃን ጅራፍ እያጮኽን በጠየቅንበት፡ አሁን አልቢንና ጓንዴያችንን አንስተን መብታችንን ለማስከበር መራር ትግል እያደረግን ነው።”
“እቅዳችን አማራን እንደ አማራ የሚያስከብር፣ አርሶ አደሩን ምን ጎደለባችሁ እያለ ዝቅ ብሎ የሚጠይቅ ከኛው ከአማራ አብራክ የወጣ መሪ ማስቀመጥ ነው”
በደቡብ ጎንደር የክምር ድንጋይና የአከባቢው ታጋይ አርሶ አደሮች ከመረብ
የህዳሴ ግድብ የፈጠረው ሀይቅ የሚይዘው የውሀ መጠን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ያሏት ሀይቆች ከሚይዙት ውሀ መጠን ይበልጣል በሚል የቀረበው መረጃ የተሳሳተ ነው
/ኢትዮጵያ ቼክ/- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተሰራጨ ንግግራቸው ላይ የህዳሴ ግድብ የፈጠረው ሀይቅ የሚይዘው የውሀ መጠን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ያሏት ሀይቆች ከሚይዙት ውሀ መጠን ይበልጣል የሚል መረጃ ተናግረዋል (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/r/19wghsZ58y/)
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚህ ንግግራቸው ላይ “ኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጥሮ ጣና፣ አብያታ፣ ሻላ፣ ላንጋኖ የሚባሉ ሁሉም ሀይቆች ተደምረው አሁን ያላቸው አቅም 70 ቢልየን ሜትር ኪዩብ ነው” ብለዋል።
አክለውም “ህዳሴ በሚሞላበት ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሀይቆቹን በሙሉ የሚበልጥ አቅም አለው ማለት ነው። አንድ ሰው ሰራሽ ግድብ በተፈጥሮ እስካሁን ኢትዮጵያ ያላትን ሀይቆች በሙሉ የሚበልጥ መጠን (size) የውሀ ክምችት ያለው ሆኖ ይታያል” ሲሉ ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ንግግር ዙርያ ማጣራት ያደረገ ሲሆን ‘ንጋት’ የሚል ስያሜ የተሰጠው የህዳሴ ግድብ በሚይዘው የውሀ መጠን ከኢትዮጵያ ቀዳሚው ሰው ሰራሽ ሀይቅ ቢሆንም ሁሉም ሀይቆች ተደምረው ግን ከህዳሴ ግድብ ሀይቅ በላይ ይይዛሉ እንጂ አያንሱም።
የተለያዩ በመንግስት ጭምር የተለቀቁ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እና ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንዳሉት የህዳሴ ግድብ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ውሀ የመያዝ አቅም 74 ቢልዮን ኪዩቢክ ሜትር ገደማ ነው።
ይሁንና በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ሀይቆች ውሀ የመያዝ አቅም ከ87 እስከ 97 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር እንደሆነ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ።
ለምሳሌ ‘International Journal of Applied Earth Observation and Geoinformation’ የተባለው የምርምር ተቋም
መንግስት የሚልከውን ነዳጅ በአካባቢው በሚመረት ወርቅ ቀይረው የሚቀበሉት ባለስልጣናት
“የኮፖሬሽኑ አመራሮች ኮርፖሬሽኑ የመንግስት ተቋም እንደመሆኑ መጠን ድርጊቱን ተከታትሎ ማስቆም ሲገባው ከዚህ ፍፁም ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ በአካባቢው በሚከናወናው ነዳጅን በወርቅ የመቀየር ስራ ላይ ተጠምደዋል”
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://tinyurl.com/pppxe93h
የተገባደደው 2017 በጨረፍታ
የተገባደደው 2017 በጀት ዓመት የተጀመረው በማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ዕርምጃ ዜና ነበር፡፡ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ግድም በእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ታጅቦ የተበሰረው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም… https://ethiopianreporter.com/145366/
ጉምሩክ ኮሚሽን አዋጅ በሚፃረር ሰርኩላር የሕግ ጥሰቶችን እያለማመደ ነው ተባለ
‹‹ሰርኩላር ከአዋጁ ጋር የሚጋጭ ከሆነ አዋጁን ለማሻሻል እየተሠራ ነው›› ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ኮሚሽን በሕዝብ ወካዮች ምክር ቤት የወጣ አዋጅ የሚፃረር ሰርኩላር በማውጣት ሕጎች እንዲጣሱ ልምምድ… https://ethiopianreporter.com/145209/
በኢትዮጵያ 37 ሚሊዮን ዜጎች ለመሠረታዊ አገልግሎቶች ውኃ ማግኘት እንደማይችሉ ተመድ በሪፖርቱ አስታወቀ
ማኅበራዊ ሲሳይ ሳህሉ – September 3, 2025
የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅትና የዓለም ጤና ድርጅት በጋራ ባወጡት ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ 37 ሚሊዮን ዜጎች ለመሠረታዊ አገልግሎት የሚሆን ውኃ ለማግኘት አይችሉም አሉ፡፡ የሁለቱ የተመድ ድርጅቶች… https://ethiopianreporter.com/145309/
በጎንደር ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ሥራቸው መዳከሙ ተገለጸ
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የሆቴሎች ባለቤቶች ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃሴ በመቀዛቀዙ፣ የሆቴል ሥራቸውም መዳከሙን አስታወቁ፡፡ ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡ የከተማዋ የሆቴል ባለቤቶች አንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት… https://ethiopianreporter.com/145314/
ዘጠና በመቶ የሚሆነው ዓመታዊ የመንግሥት በጀት በጥቂት ግብር ከፋዮች ጫንቃ ላይ ወድቋል ተባለ
በመድረኩ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ ተወድሷል ዘጠና በመቶ የሚሆነው ዓመታዊ የመንግሥት በጀት የሚደገፈው ከጠቅላላ ግብር ከፋዮች ውስጥ ከአሥር በመቶ በታች በሆኑ ጥቂት ግብር ከፋዮች መሆኑ. …. https://ethiopianreporter.com/145364/
መንግሥታት ሃይማኖታዊ የሲቪል ማኅበራትን በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ተጠያቂ እያደረጓቸው መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ
ኢትዮጵያን ጨምሮ የሴኔጋል፣ የማሊ፣ የኒጀርና የሱዳን አገሮች መንግሥታት ሃይማኖታዊ የሲል ማኅበረሰብ ደርጅቶችን ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና የገንዘብ ማሸሽ ወንጀል ተጠያቂ እንደሚደርጓቸው የአፍሪካ ኅብረት አስታወቀ፡፡ በኅብረቱ ሴክሬታሪያት… https://ethiopianreporter.com/145185/
የተበከለ ውኃ የከተማ ግብርና ምርቶችን ለማምረት ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገለጸ
ከፍተኛ የታክስ ክፍያና ተከታታይ መዋጮዎች በችግርነት ተነስተዋል ….. በአዲስ አበባ ከተማ የተበከለ ውኃ በከተማ ግብርና ለኅብረተሰቡ የሚቀርቡ ምርቶችን ለማምረት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ በጥናት ተመላከተ፡፡ የአዲስ አበባ… https://ethiopianreporter.com/145206/
የግብጽና ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ሌሎች የተፋሰሱ አገራት አያገባቸውም ሲሉ ካይሮ ውስጥ ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።
ኹለቱ አገራት ግድቡ በምሥራቅ የናይል ተፋሰስ አገራት ላይ ዘላቂ ስጋት ደቅኗል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለግድቡ የውሃ ሙሌት ወስደዋለች ያሉትን የተናጥል ርምጃ የተቃወሙት ኹለቱ አገራት፣ የውሃ ደኅንነታቸው “አንድ” እና “የማይነጣጠል” መኾኑን አጽንዖት ሠጥተዋል።
ኢትዮጵያ በምሥራቃዊ የናይል ተፋሰስ ዙሪያ የምትከተለውን ፖሊሲ መቀየር እንዳለባትም ኹለቱ አገራት አሳስበዋል።
በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ በሕጋዊ የድንበር ዘለል ንግድ የተሠማሩ ኬንያዊያን ነጋዴዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ የኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ፣ “ማስፈራሪያ”፣ “የዘፈቀደ እስር” እና “የንብረት መውረስ” ድርጊቶችን እየፈጸሙብን ነው በማለት መክሰሳቸውን የኬንያው ስታንዳርድ ጋዜጣ ዘግቧል። የጸጥታ ኃይሎቹ ድርጊት ድንበር ዘለል ንግድን እያስተጓጎለና የኛንጋቶምና ቱርካና ጎሳዎችን መተማመን እየሸረሸረ ነው መባሉንም ዘገባው ጠቅሷል። አንድ ኬንያዊ በኢትዮጵያ ጸጥታ ኃይሎች ታስሮ እንደሚገኝ የጠቀሠው ዘገባው፣ ኬንያዊውን ለማስለቀቅ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ጣልቃ እንዲገባ የቱርካና ግዛት የጸጥታ ኃላፊዎች ጠይቀዋል ተብሏል። ሃላፊዎቹ፣ የኢትዮጵያው ደቡብ ኦሞ ዞን የአስተዳደርና ጸጥታ አካላት እንዲኹም የኹለቱ ጎሳዎች የአገር ሽማግሌዎችም ተሰብስበው ለችግሩ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጥሪ ማድረጋቸው ተነግሯል።
ሁለት የሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ 102.1 ጋዜጠኞች ነሐሴ 28 ቀን 2017 ዓ፣ም በወንጀል ተጠርጥረዉ መታሰሠራቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
ጋዜጠኞቹ የታሠሩት፣ ነሐሴ 23 ቀን ጣቢያው በጤና ባለሙያዎች ዙሪያ ካስተላለፈው አንድ ዘገባ ጋር በተያያዘ መኾኑን ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ጋዜጣው አመልክቷል።
በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መምሪያ ውስጥ የታሠሩት የጣቢያው ጋዜጠኞች፣ ትዕግስት ዘሪሁን እና ምንታምር ጸጋው ናቸው ተብሏል።
ሸገር ስለ ጋዜጠኞቹ እስር ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው ነገር የለም።
የሕወሓት ታጣቂዎች በደቡባዊ ትግራይ ዞን መኾኒ ከተማ ትናንት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ አንድ ወጣት ሲገድሉ ኹለቱን ማቁሰላቸውን የአካባቢው ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። ሟቹ በጥይት ተመቶ ከወደቀ በኋላ በተደጋጋሚ በታጣቂዎቹ ጥይት መመታቱን ምንጮች ገልጸዋል።
የጸጥታ ኃይሎቹ ተኩስ የከፈቱት፣ የአካባቢው ማኅብረሰብ እያቀረበባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማፈን ነው ብለው እንደሚያምኑም ምንጮች ተናግረዋል።
በተያያዘ፣ በአላማጣ ከተማ አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ በታጣቂዎች ተደብድቦ ወደ ካምፕ እንደተወሰደ በአማራ ክልል በኩል ለከተማዋ ከንቲባነት ተሹመው የነበሩት ሃይሉ አበራ ነግረውናል።
የኤርትራው ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናትና ተሳዳቢዎቻቸው በኤርትራ ላይ “በግዴለሽነት” የሚያካሂዱትን “ወታደራዊ ዛቻ” እንደገና ቀጥለውበታል በማለት ከሰዋል።
የማነ፣ ይሄ የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናት የኤርትራን ጥንታዊ፣ የመካከለኛው ዘመንና ዘመናዊ ታሪክ ያዛባሉ በማለት ወቅሰዋል።
የሰሞኑ ትርክት ከኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት የማነ፣ ሕዝበ ውሳኔው ኤርትራን በወረራ የያዘችው አገር በቅድሚያ ፍላጎቷ ሊጠየቅበት ወይም ሕዝበ ውሳኔውን እንድትቀበል በቅድመ ሁኔታነት ሊቀርብ የሚችልበት ሁኔታ እንዳልነበረና ሊኖርም እንደማይችል ገልጸዋል።
የማነ ይህን ያሉት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ በነበራት የባሕር በር ላይ የተሠራው ስህተት ነገ ይታረማል በማለት በተናገሩ ማግስት ነው።
ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት በምሥራቁ መስመር የፍልሰተኞች እንቅስቃሴ እንዳልቀነሠ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ከሳዑዲ ዓረቢያ በግዳጅ የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ወደ አማራ፣ ትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች በብዛት መሄዳቸው፣ ሰብዓዊ ቀውሱን ይበልጥ እንዳባባሰው ሪፖርቱ ጠቅሷል። ሪፖርቱ፣ በጅቡቲ በኩል የሚያልፉ ሴት ፍልሰተኞች ቁጥር ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እጥፍ በላይ ከፍ ማለቱንም አውስቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለኢንቨስትመንት እንዲሁም ለመኖሪያ ቤትና ለመኪና መግዣ የሚያውሉት 50 ቢሊዮን ብር ለማበደር መዘጋጀቱን ይፋ አድርገዋል። አቤ፣ ወደ አገሪቱ የሚገባው የውጭ ምንዛሬ እየጨመረ ቢሄድም፣ በሕጋዊ መንገድ የሚገባው ግን አነስተኛ መኾኑን ገልጸዋል። በኤምሬቶች የሚገኙ ሕገወጥ የገንዘብ አስተላላፊዎች ለዚህ ችግር ተዋናይ ተጠያቂ እንደኾኑም አቤ በኢምሬቶች ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተወያዩበት ወቅት ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ኢትዮጵያዊያን በባንኩ አመቺ የውጭ ምንዛሬ መላኪያ አማራጮች እንዲጠቀሙም ጥሪ አድርገዋል። ባንኩ ኢምሬቶች ውስጥ ወኪል ቅርንጫፍ ለመክፈት ማቀዱም ተገልጧል።
እናት ፓርቲ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሐይማኖት አባቶችን መግደል ያልተጻፈ ሕግ ኾኗል ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ ከሷል። ፓርቲው፣ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ሮቤ ወረዳ፣ የመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የ78 ዓመቱ መምሬ ንጉሤ ወልደ መድኅን በታጣቂዎች መገደላቸውን ሰሞኑን በግፍ ገልጿል። በተለይ የአርሲ ዞን የደም መሬት ኾኗል ያለው ፓርቲው፣ የሐይማኖት አባቶች ግድያ ወደመለመድ ደረጃ ደርሷል ብሏል። ዕሁድ’ለትም በቦሌ ክፍለ ከተማ የጎጆ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን የድጓ መምህር አፈወርቅ አበባው በጥይት መገደላቸውን ፓርቲው ጠቅሷል። የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎትም ይህንኑ ግድያ አረጋግጧል።
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ፈተናና ችግር ዋና ምንጭ የነበረው ዓባይ ወንዝ እንደነበርና አሁን ግን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ እዚህም እዚያም የሚስተዋሉ ችግሮች በሂደት ይፈታሉ በማለት በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው ገልጸዋል። ዐቢይ በአገሪቱ በየቦታው የሚፈጠሩ ቀውሶችን ከዓባይ ወንዝ ጋር አያይዘዋቸዋል። ዐቢይ፣ መንግሥት በቀጣዮቹ ዓመታት በርካታ የኃይል ማመንጫ ግድቦችን የመገንባት እቅድ እንዳለውም ተናግረዋል። ቀይ ባሕር በኢትዮጵያ እጅ እንደነበር ያስታወሱት ዐቢይ፣ በቀይ ባሕር ላይ የተሠራው ስህተት እንደሚታረምና የቀይ ባሕር ጉዳይ ከእንግዲህ ለኢትዮጵያ ከባድ እንደማይኾን ጠቁመዋል።
“በቋራ ቃል ኪዳን ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን (አፋብኃ) ከመሰረትን በኋላ በአማራ ፋኖ በጎጃም በኩል የተነሱ የልዩነት ሃሳቦች ነበሩ። እነዚህ የልዩነት ሃሳቦች በውስጥና በውጭ ገፊ ምክንያቶች መልካቸውንና ዓይነታቸውን እየቀያየሩ ቢቆዩም በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች በዛሬው ዕለት ማለትም ነሃሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. መቋጫ አግኝቷል። በመካከላችን የተፈጠሩ ልዩነቶችን ፈትተን አንድ ሆነናል። በውይይታችንም የቋራ ቃል ኪዳንን አድሰናል።”
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ መንግሥት ያስታጠቀው “የወለጋ ፋኖ” የተሠኘ ታጣቂ ኃይል በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሰ ይገኛል በማለት አዲስ ባወጣው መግእ ከሷል። ቡድኑ፣ መንግሥት ለዚህ ቡድን ድጋፍ የሚሠጥበት አንዱ ምክንያት፣ በአካባቢው ሕዝብ ላይ የፍርሃት ድባብ በመፍጠር ሕዝቡ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለሚመራው ዓላማ የሚሠጠውን ድጋፍ እንዲቀንስ ማድረግ ነው ብሏል። ሁለተኛው የመንግሥት ዓላማ ደሞ በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች መካከል መቃቃርና “የእርስ በርስ ግጭት” እንዲፈጠር ማድረግ ነው በማለት ቡድኑ ከሷል። ሕዝቡን ከእነዚህ ታጣቂዎች ጥቃት ለመጠበቅ፣ አስፈላጊውን ርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ቡድኑ አስጠንቅቋል። ራሳቸውን “ፋኖ” በማለት የሚጠሩ ታጣቂዎች በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎች በሲቪሎች ላይ ጥቃት እንደሚፈጽሙ፣ ዋዜማ የአካባቢውን ነዋሪዎች በመጥቀስ ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ በቅርቡ በደቡባዊ ትግራይ ዞን የፈጠረው አዲስ መዋቅር የትግራይ ወረዳዎችን በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሥር ያደረገ “ፖለቲካዊ ውሳኔ” ነው በማለት ከሰዋል። ጀኔራል ታደሠ ዛሬ አክሱም ውስጥ በተከበረ አንድ የኦርቶዶክስ ኃይማኖታዊ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የትግራይ የኃይማኖት መሪዎችና ምዕመናን የሲኖዶሱን ውሳኔ እንዲቃወሙት ጠይቀዋል። የክልሉ የኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶች፣ ሲኖዶሱ በማይጨው አገረ ስብከት ሥር የነበሩት አላማጣ፣ ኦፍላ፣ ዛታ እና ጨርጨር ወረዳዎች እንዲኹም አላማጣና ኮረም ከተሞች ራሱን በቻለ አገረ ስብከት እንዲተዳደሩ ወስኗል በማለት በቅርቡ ተቃውሟቸውን ገልጠው እንደነበር አይዘነጋም። ጀኔራል ታደሠ፣ የትግራይ ሕዝብ ችግሮች በዋናነት የሚመነጩት ከትግራይ አመራሮች መኾኑንና የሕዝቡ ችግሮች ከውስጥም ከውጭም ሥር እየሰደዱ መሄዳቸውንም በዚሁ ንግግራቸው ጠቁመዋል።
የይስሙላ ምክክር ኮሚሽኑ የዲሲ ስብሰባ ከሽፏል: የተገኙት ራሳቸው የአገዛዙ ተወካዬችና የብልፅግና አባለት ናቸው: የለንደን ፋኖ አዲስ ሰለሞን የህዝብን መልዕክት አድርሷል:: ሌላው ተቃዋሚ ከአዳራሹ ውጭ ድምፁን በጋራ አሰምቷል:: ቀጣዩ ቶሮንቶ ነው! https://www.facebook.com/reel/776026735072671