“በቋራ ቃል ኪዳን ድርጅታችን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልን (አፋብኃ) ከመሰረትን በኋላ በአማራ ፋኖ በጎጃም በኩል የተነሱ የልዩነት ሃሳቦች ነበሩ። እነዚህ የልዩነት ሃሳቦች በውስጥና በውጭ ገፊ ምክንያቶች መልካቸውንና ዓይነታቸውን እየቀያየሩ ቢቆዩም በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች በዛሬው ዕለት ማለትም ነሃሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም. መቋጫ አግኝቷል። በመካከላችን የተፈጠሩ ልዩነቶችን ፈትተን አንድ ሆነናል። በውይይታችንም የቋራ ቃል ኪዳንን አድሰናል።”