የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናትና ተሳዳቢዎቻቸው በኤርትራ ላይ “በግዴለሽነት” የሚያካሂዱትን “ወታደራዊ ዛቻ” እንደገና ቀጥለውበታል

የኤርትራው ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናትና ተሳዳቢዎቻቸው በኤርትራ ላይ “በግዴለሽነት” የሚያካሂዱትን “ወታደራዊ ዛቻ” እንደገና ቀጥለውበታል በማለት ከሰዋል።

የማነ፣ ይሄ የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናት የኤርትራን ጥንታዊ፣ የመካከለኛው ዘመንና ዘመናዊ ታሪክ ያዛባሉ በማለት ወቅሰዋል።

የሰሞኑ ትርክት ከኤርትራ ሕዝበ ውሳኔ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት የማነ፣ ሕዝበ ውሳኔው ኤርትራን በወረራ የያዘችው አገር በቅድሚያ ፍላጎቷ ሊጠየቅበት ወይም ሕዝበ ውሳኔውን እንድትቀበል በቅድመ ሁኔታነት ሊቀርብ የሚችልበት ሁኔታ እንዳልነበረና ሊኖርም እንደማይችል ገልጸዋል።

የማነ ይህን ያሉት፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ በነበራት የባሕር በር ላይ የተሠራው ስህተት ነገ ይታረማል በማለት በተናገሩ ማግስት ነው።