ዐቢይ በአገሪቱ በየቦታው የሚፈጠሩ ቀውሶችን ከዓባይ ወንዝ ጋር አያይዘዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ፈተናና ችግር ዋና ምንጭ የነበረው ዓባይ ወንዝ እንደነበርና አሁን ግን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ እዚህም እዚያም የሚስተዋሉ ችግሮች በሂደት ይፈታሉ በማለት በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈ ንግግራቸው ገልጸዋል። ዐቢይ በአገሪቱ በየቦታው የሚፈጠሩ ቀውሶችን ከዓባይ ወንዝ ጋር አያይዘዋቸዋል። ዐቢይ፣ መንግሥት በቀጣዮቹ ዓመታት በርካታ የኃይል ማመንጫ ግድቦችን የመገንባት እቅድ እንዳለውም ተናግረዋል። ቀይ ባሕር በኢትዮጵያ እጅ እንደነበር ያስታወሱት ዐቢይ፣ በቀይ ባሕር ላይ የተሠራው ስህተት እንደሚታረምና የቀይ ባሕር ጉዳይ ከእንግዲህ ለኢትዮጵያ ከባድ እንደማይኾን ጠቁመዋል።