ከሳዑዲ ዓረቢያ በግዳጅ መመለሳቸው ሰብዓዊ ቀውሱን አባብሶታል ተባለ

ዓለማቀፉ የፍልሰት ድርጅት በምሥራቁ መስመር የፍልሰተኞች እንቅስቃሴ እንዳልቀነሠ ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። ከሳዑዲ ዓረቢያ በግዳጅ የሚመለሱ ኢትዮጵያዊያን ወደ አማራ፣ ትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች በብዛት መሄዳቸው፣ ሰብዓዊ ቀውሱን ይበልጥ እንዳባባሰው ሪፖርቱ ጠቅሷል። ሪፖርቱ፣ በጅቡቲ በኩል የሚያልፉ ሴት ፍልሰተኞች ቁጥር ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት እጥፍ በላይ ከፍ ማለቱንም አውስቷል።