የእሥር ማዘዣ የወጣባቸው የሕወሐት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ እናቀርባለን


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኅዳር 10 ቀን 2013
እንደ ማይካድራ ባሉ ስፍራዎች የሕወሐት ወታደሮች እና ታማኞቻቸው በሰላማዊ ዜጎች ላይ በማንነት ላይ ያነጣጠረ ግፍ መፈጸማቸውን በተለያዩ የዜና አውታሮች ተዘግቧል፡፡ ይህም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በዚሁ ወንጀለኛ ቡድን ሲቀነባበሩ ከነበሩ ሕዝብ የማስጨረስ ሥራዎች ጋር የሚያያዝ ነው፡፡
የፌዴራል መንግሥት እንደዚህ ላሉት አስከፊ የወንጀል ድርጊቶች ተጠያቂ የሆኑትን ለፍርድ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን በድጋሚ ለመግለጽ ይፈልጋል ፡፡
በሕወሐት ቡድን ላይ የሚወሰደው ሕግን የማስከበር ዘመቻ ወደ መጨረሻው ደረጃ ስንገባ፣ የዚህ ቡድን አመራሮች እንደ ማይካድራ ባሉ ሥፍራዎች ኃይሎቻቸው እና ታማኞዎቻቸው የፈጸሟቸው አሰቃቂ ድርጊቶች፣ በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም አቀፍ ሕግ የሚያስጠይቁ ከባድ ወንጀሎች መሆናቸውን ለማስታወስ እንወዳለን ፡፡
አሁንም የእሥር ማዘዣ የወጣባቸው የሕወሐት አመራሮች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ እና ተጨማሪ ግፍ ከመፈጸም እንዲታቀቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ የመጨረሻዎቹን እንጥፍጣፊ ዕድሎች መጠቀም እጅግ ከከፋው ዕጣ ፈንታ ያድናቸዋል።