በሶማሊ ክልል አቶ ሙስጠፋን ከስልጣን ለማውረድ የተደረገው ሙከራ እንደከሸፈ ተነገረ

በሶማሊ ክልል አቶ ሙስጠፋን ለማውረድ የተደረገው ሙከራ እንደከሸፈ ተነገረ – ESAT
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የክልሉ ባለስልጣን እንዳሉት ፕ/ት ሙስጠፋን ከስልጣን ለማውረድ የተጀመረው እንቅስቃሴ አልተሳካም። የደህንነት ሹሙና የፕሮቶኮል ሹሙ በቁጥጥር መዋላቸውንም ባለስልጣኑ ተናግረዋል።
ከልሉ ከሰዓታት በሁዋላ መግለጫ እንደሚሰጥም ታውቋል።
ከኢሳት ዘገባ ጎን ለጎን ኢትዮ ኤፍ ኤም ባሰራጨው ዘገባ በሶማሊ ክልል መፈንቅለ መንግስት ተሞከሮ ከሸፈ መባሉ ሐሰት መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ የኮሙንኬሽን ጉዳዮች ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሂቦ መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት “በክልሉ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሃሰት ነው” ብለዋል።
“ወሬውን የሰማነው ከማህበራዊ ድረገጽ ነው እንጂ የክልሉ አጠቃላይ አመራር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ ላይ ነው እየተንቀሳቀሰ ያለው” ሲሉ ገልጸዋል።
አሐዱ ሬዲዮ ባሰራጨው ዘገባ የሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ሙስጠፌ መሐመድ ከስልጣን ለማውረድ የተደረገው ሙከራ ሳይሆን በካቢኔ አባላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተከሰተ ግርግር ነው ተባለ።
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዲ ኡመር ለአሐዱ እንደተናገሩት በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች እየተሰራጨ እንዳለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ሳይሆን አንዳንድ አሰጊ ነገሮች ተፈጥረው መቆጣጠር መቻሉን ተናግረው.
በተነሳው ግር ግር የተጠረጠሩ የደህንነት ና የፕሮቶኮል ሹሙ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዬ እየተጣራ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል
አሐዱ ሬዲዮ