Blog Archives

የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት አለም አቀፍ ውይይትና የድጋፍ ማሰባሰብ መርኃግብር

የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት አለም አቀፍ ዉይይትና የድጋፍ ማሰባሰብ መርኃግብር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል 1. Zoom link :- https://zoom.us/j/91246388078 ; (January23/2021 ከጠዋቱ 11:00 AM EST) 2. በ “GoFundeMe” የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ለመደገፍ https://gofund.me/2c41f2da 3. በባንክ አካዉንት ለመደገፍ : – Acount No. 501025436006; Routing number 122400724; Zenaw b Kassa ; 4. በ’Zelle’ ገንዘብ ለመርዳት (702)338-0658 5.የሀሳብ መንሸራሸር እንዲያደርጉ ከተጋበዙ እንግዶች ዉስጥ ጥቂቶቹ :- አቶ ገለታዉ ዘለቀ(የባልደራስ ም/ፕ): አቶ አብርሃም ጌጡ(የመኢአድ ም/ፕ): ዶ/ር አበባ ፈቃደ: ዶ/ር አረጋህኝ ንጋቱ: ዶ/ር ካሳዉ ተፈራ: ዶ/ር ደብሩ ነጋሽ: አቶ ሙሉጌታ ደስታ(የሰ/አሜሪካ ባልደራስ ድጋፍ ሰብሳቢ): አቶ ኪዳኔ ምስክር(የሰ/አሜሪካ መኢአድ ድጋፍ ሰብሳቢ) ————————————————————————————————————- በኢትዮጵያ የአንድነት ተቃዉሞ ጎራ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠዉን የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅትን በመደገፍ ሀገር የማዳን ሀላፊነትዎትን ይወጡ ! እስክንድ ነጋ በፕሬዝዳንትነት እንዲሁም ማሙሸት አማረ በም/ፕሬዝዳነት የሚመሩት የመኢአድ ባልደራስ ቅንጅት በኢትዮጵያ የአንድነት ተቃዉሞ ጎራ ዉስጥ የሞራል የበላይነቱን የጨበጠ እንቅስቃሴ ያለዉ ነዉ:: ለሞራል የበላይነቱም ሶስት ሁነኛ ምክንያቶች አሉ:- 1ኛ. ለሰላሳ አመታት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ፍትህ እና ለዜጎች እኩልነት አንድም ቀን ግንባሩን ሳያጥፍ የታገለዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድን) ያካተተዉ የመኢአድ-ባልደራስ ቅንጅት ከመሃል አዲስ አበባ እስከ መላዉ ኢትዮጵያ ጠረፎች ኢትዮጵያዉያንን በጋራ የማንቀሳቀስ መሰረት ያለዉ ሀይል ነዉ:: ከመአህድ እስከ መኢአድ: ከመኢአድ እስከ ቅንጅት የዘለቀዉን የዲሞክራሲ የእኩልነት: የፍትህ እና የአንድነት ጥያቄ አንግቦ በዘረኞች እና በአምባገነኖች ፊት “የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ህዝብ ነዉና ኢትዮጵያዊ ሁሉ እኩል ፍትህ ዲሞክራሲ ነጻነት ብልጽግና
Posted in Ethiopian News

በአል ነጃሲ መስጊድ ላይ ስለደረሰው ጥቃት የተሰጠ መግለጫ

በአል ነጃሲ መስጊድ ላይ ስለደረሰው ጥቃት የተሰጠ መግለጫ መግለጫውን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ስለ አል ነጃሲ መስጊድ የወጣ መግለጫ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ (ኢ.ው.ቅ.ማ.ሰ.አ.) ጥር 2003 ዓ.ም. ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ያወረሱንን ታሪክ፣ ትውፊትና ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍና ተተኪው ትውልድ በአገራችን ባሕልና ወግ እንዲታነጽ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷና አንድነቷ የተጠበቀ አንዲሁም ዜጎቿ በሰላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን የኢ.ው.ቅ.ማ.ሰ.አ. ጽኑ ምኞት አለው። የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አማሪካ በአል ነጃሲ መስጊድ ላይ በደረሰው ጥቃት በእጅጉ ማዘኑን ይገልጻል። የአል ነጃሲ መስጊድ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክርስትናን ከእስልምና ጋር ያስተሳሰረ ታሪካዊ መስጊድ ነው። ይህ ጥንታዊ መስጊድ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚኮሩበት ቅርሳቸውና ታሪካቸው ከመሆኑም በላይ ለጎብኝዎችም መስህብ ነው። የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ በታሪካዊ ቤተ እምነቶች፣ሀወልቶች፣ቅርሶችና የተለያዩ አገር ንብረቶች ላይ ለጠባብ ፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ በተለያዩ ቡድኖችና አካላት የሚደርሰውን ጥቃት በጥብቅ ያወግዛል። ኢትዮጵያዊያን የመረጡትን ኃይማኖታቸውን በግላቸው ይዘው እርስ በርስ ተከባብረው፣ተጋብተው፣ ተጎራብተውና ተፋቅረው ለዘመናት ኖረዋል፣ አሁንም እየኖሩ ነው ለወደፊቱም ይኖራሉ። በአል ነጃሲ መስጊድና በሌሎችም ኃይማኖታዊና ታሪካዊ ቦታዎች ላይ ጥቃት፣ውድመትና ቃጠሎ ያደረሱ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ማንነታቸው ተጣርቶ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማህበራችን ይጠይቃል። ለአገር ቅርሶችና ቤተ እምነቶች ጥበቃ ማድረግና ደህነነታቸውን ማረጋገጥ የመንግስት ግዴታና ኃላፊነት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን። ካለፉት ሶስት አመታት አንስቶ የምዕመናን መጨፍጨፍና መፈናቀል እንዲሁም የቤተክርስቲያኖችና
Posted in Ethiopian News

“እስክንድር ነጋ ይፈታ” freeeskindernega.org በትዊተር ላይ @FreeEskinderN እና Instagram ላይ @freeeskindernega

“እስክንድር ነጋ ይፈታ” ዓለም አቀፍ ዘመቻ freeeskindernega.org በትዊተር ላይ @FreeEskinderN እና Instagram ላይ @freeeskindernega  ከሁለት ዓመት በፊት በንዴት የተበሳጨው ተረኛው አብይ አህመድ በአዲስ አበባና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥሪ በማድረጋቸው ብቻ በሰላማዊው እስክንድር ነጋና ባልደራስ ላይ ጦርነት እናካሂዳለን ሲል ደንፍቷል። በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ መቆጣጠር ስላልቻለ እያለከለከ አቅራርቷል። ከታሪክ አለመማር ነው እንጅ እነ ስብሃት ነጋም ህዝብ ላይ ሲሳለቁ፣ ሲያቅራሩና ሲያናፉ ነበር የኖሩት። “እግዚአብሔር እውነትን ያያል፣ ግን አይቸኩልም እንደሚባለው” ስብሀት ነጋና ባልደረቦቹ  ጊዜያቸው ሲደርስ ከቤተ መንግስት ተወግደው ወደ መደበቂያ ጉሮኖ ወርደዋል። አብይ አህመድም ከእብሪቱ ተመልሶ በግፍ ያሰራቸውን እነ እስክንድር ነጋን በአስቸኳይ ካልፈታና አገሪቷን ከቁማርና ከሸር በጸዳ መልክ ለማስተዳደር እስካልቆረጠና ነጻና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ ካላደረገ በስተቀር ከስብሃት ነጋ የከፋ ውርደት ውስጥ በፍጥነት እንደሚገባ የሚያጠራጥር ነገር የለም። እንደ እስክንድር ነጋ ያሉ ንፁሃን ሰዎች እንዴት እንደ ስብሃት ነጋ ካሉ የትህነግ ወንጀለኞችና ደም አፍሳሾች ጋር አብረው ይታሰራሉ? ንጹሃንና ወንጀለኞችን ሁለቱንም ወህኒ ቤት ማስገባት የተጨናበረውና የተወናበደው የአብይ አህመድ ፍልስፍና “መደመር” ይሆን እንዴ? ስብሃት ነጋና መሰሎቹ ለሰሩት ግፍና ወንጀል እስር ቤት መግባታቸውና ፍርዳቸውን መቀበላቸው ተገቢ ሲሆን እስክንድር ነጋና ባልደረቦቹ ምን አደረጉ? አብይ አህመድ እኮ የጊዜ ጉዳይ ሆኖ እንጅ ለስብሃት ነጋ በተላላኪነት ሲያገለግል በነበረበት ጊዜ እስክንድር ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ዲሞክራሲ በመታገሉ ምክንያት በትህነግ በግፍ ታስሮ ዋጋ ይከፍል እንደነበር አይዘነጋም። እስክንድር ነጋ በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ
Posted in Ethiopian News

“እስክንድር ነጋ ይፈታ!” የሚል ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ ይፋ ተደረገ

“እስክንድር ነጋ ይፈታ!” የሚል ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ ይፋ ተደረገ የህሊና እስረኛ የሆነውን እስክንድር ነጋ በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር እንዲፈታ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ለማሳሰብና ለመጠየቅ ገለልተኛና የፓርቲ ልሳን ያልሆነ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ተጀምሯል። በአብይ አህመድ አገዛዝ በግፍና በማን አለብኝነት በህገወጥ ሁኔታ በፖለቲካ ጥላቻና ቁማር ምክንያት እስር ቤት እየተሰቃዩ የሚገኙትን እስክንድር ነጋንና ባልደረቦቹን ለማስፈታት የተጀመረውን ዓለም አቀፋዊ ጥረት እንድትቀላቀሉ ትጠየቃላችሁ። www.freeeskindernega.org ይጎብኙ! በትዊተር @FreeEskinderN በInstagram ላይ @freeeskindernega ላይ ይከተሉን እንዴት እስክንድር ነጋን የሚያክል የሰላምና የዲሞክራሲ ሐዋርያና ዋርካ በትህነግ ዘመን የተሰቃየው ሳያንሰው አሁን ደግሞ በአብይ አህመድ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት ሲጣል ኢትዮጵያዊያን ዝም ብለን እናያለን? አባዱላ ገመዳ፣ ወርቅነህ ገበየሁና የመሳሰሉት ነፍሰ ገዳዮችና ዘራፊዎች በድሎትና በምቾት አየተንቀባረሩ ሲኖሩ እድሜ ልኩን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዋጋ እየከፈለ የሚገኘው እስክንድር ነጋ በእስር ይማቅቃል? እስክንድር ነጋ እስር ቤት እየተሰቃየ ለአብይ አህመድ ማሸርገድና ከገዳዮችና አሳሪዎች ጎን መቆም ኢትዮጵያዊያን ለሆኑ በሙሉ ትልቅ ውርደትና የቁም ሞት ስለሆነ እስክንድር ነጋ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥረትና እርብርቦሽ መደረግ አለበት። ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚላኩ በቅድሚያ የተጻፉ ኢሜሎች አዘጋጅተናል። በአሜሪካ ሴኔትና በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የሚያገለግሉትን ተወካዮች በኢሜል፣ በደብዳቤና በስልክ እያነጋገሩ ከዚህ የተቀደሰ ዓላማ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ። ስለ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ወቅታዊ የዜና ዘገባዎችንና ሌሎች መረጃዎች ስለሚለቀቁ የኢሜል አድራሻዎትን ይስጡ።    
Posted in Ethiopian News

“ትኋን ውጪ”በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ትኋን ውጪ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ “ትኋን ውጪ ቁንጫ ግቢ” የሚለው አባባል ባንድ ዘመን ባንድ ትውልድ የተከሰተ የመከራና የሥቃይ መዘክር ነው። በመከራው ያለፉት የቀደሙ አባቶች በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይረሱት ለተከታዮቻቸው አውርሰውታል። በጀማሪወች ቀዳማውያን አባቶቻችንና በኛ መካከል የነበሩት  ኢትዮጵያውያን አባቶቻችንም ለኛ አቀብለውናል። የትግራይ የጎንደር የወሎ የጎጃም የሸዋና ሌሎችም እንደየአካባቢያቸው  ይገልጹታል። በትግራይና በወሎ “ትኋን ውጪ ቁንጫ ግቢ” እንደሚባል በደብረ ሊባኖስ ከነበሩት ምሥጢር ማደላደል የሚባለውን ጉባዔ ይመሩት ከነበሩት ከየኔታ ፍስሀ ሰምቻለሁ።  በጎጃም ይባል እንደነበረ አውቃለሁ። ራሴም ብሂሉን ተሳትፌአለሁ። በጎንደር ደግሞ “የሳማ ምንቼት ውጭ የጎመን ምንቼት ግቢ” ይባል እንደነበረ ሰምቻለሁ። ይህ አባባል በደርግ ዘመን እንደፈዘዘና እንደ ደበዘዘ፤ ወያኔወች ደግሞ አባባሉ ጭራሽ እንዲረሳና እንዲደመሰስ እንዳደረጉት፤ እንዲያውም ራሳቸውን ወደ ትኌንነትና ወደ ሳማ ምንቼትነት እንደቀየሩ ይነገራል። ሳማ የምትባለው ቅጠል ከቅጠል የተለየች የምትለባለብ ናት። ትኋንም የሰው ደም በመምጠት ተለባላቢ ክርፋትም ህዋስ ናት። ትኋንም የሳማ ቅጠልም የጸነሱት ሀሳብ የማይረሳ ታሪክ ነው። መረሳት የሌለበትን ታሪክ አባቶች እንዳንርሰው በባህል መልክ አውርሰውናል። “ሰው በግሉ የደረሰበትን በደል ከበደለውና ቅር ካሰኘው ሰው ጋራ ተነጋግሮ በይቅርታ የሚያልፈው ላለመደግም ቃል በመገባት ነው።  ደጋግሞ የሚፈጽመውን  በደል ላለመድገም ሳይወስን  ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ተስለክላኪ እባብ ነው ።  በተመሳሳይ ስህተት በተደጋጋሚ እየተበደለ ለመኖር ፈቃደኛ የሚሆን ግለሰብ  የስህተት መፍሰሻ ቦይ፤ የኃጢአት መጠራቀሚያ አዘቅት ለመሆን የፈቀደና ለመማርም ለማስተማርም አቅም የተሳነው የህብረተ ሸክም ነው ይላሉ ። ይህ አይነት ባህርይ ያላቸው ሰዎች ፍርሀታቸውና አቅመ
Posted in Ethiopian News

ከምዕመናን ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

Posted in Ethiopian News

ይህ ወቅት በቤተክርስቲያን ላይ ጥሎ የሚሄደው ጠባሳ እንዴት ይገለጻል? ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

Posted in Ethiopian News

የኢትዮጵያን መጻኢ እድል በአንድነት ለማቆም እንዲቻል የቀረበ ሀገራዊ ጥሪ

ታህሳህ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. (December 10, 2020) ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት – አዲስ አበባ ለኢፌድሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – አዲስ አበባ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ-ዋሽንግተን ዲሲ ለህብር ሬዲዮን ጣቢያ-ሰሜን አሜሪካ ለአዲስ ድምጽ ሬዲዮ–ሰሜን አሜሪካ ለኢትዮ360 ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ ለርዕዮት ሚዲያ – ስሜን አሜሪካ ለሚዛን ቴሌቪዥን-ሰሜን አሜሪካ ለምኒልክ ቴሌቪዥን-ሰሜን አሜሪካ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ/-ሰሜን አሜሪካ ለመረጃ ቴሌቭዥን ጣቢያ-ሰሜን አሜሪካ ለዘመድኩን በቀለ-መረጃ ቲቪ-ጀርመን ለአባይ ሚዲያ-አዲስ አበባ ለኢቲቪ-አዲስ አበባ ለአማራ ቡዙሃን ሚዲያ ኤጀንሲ-ባህርዳር ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ-ሰሜን አሜሪካ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ -ጀርመን ለዘሃበሻ-ሰሜን አሜሪካ ለኢትዮጵያ አንድነት ሬዲዮ-ስዊድን ለርዕዮት ቲቪ-ሰሜን አሜሪካ ለአደባባይ ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ ለኢትዮ-ቤተሰብ ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ ለመረጃ ሚዲያ-ሰሜን አሜሪካ ለፍትሀ መጽሄት-አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ለምትሉ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በሙሉ-ባላችሁበት ለሀገር ወዳድ ማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች-ባላችሁበት ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዩ:-የኢትዮጵያን መጻኢ እድል በአንድነት: በህግ የበላይነት :በፍትህ፣ በእኩልነት ብሎም በዲሞክራሲያዊ መሰረት ላይ ለማቆም እንዲቻል የቀረበ ሀገራዊ ጥሪ ( ክፍል-1) ሕወሓትና ኦነግ ኢትዮጵያን  በዘር ከፋፍለዉ፣ የሕዝቡን የአብሮነት የወል ዕሴቶች በማጥፋት፣ ሕዝቡ ከኢትዮጵያዊነት ማንነቱ ወጥቶ አጥፊና ጠፊ ሆኖ እንዲቆም በማድረግ፤ ከሁሉም በላይ ዐማራና ኢትዮጵያዊነት ጠል የሆነ ሕገ መንግሥት  በሕዝቡ ላይ መጫናቸው ግልጽ ነው። ይህ ሕገ-መንግሥት ዛሬ በአገራችን ላይ በሁሉም አካባቢዎች ለሚታየው መገዳደል፣ መፈናቀል፣ መሳደድና አገር አልባ መሆን ዋናው የችግሮቻችን ቋጠሮ ነው። በአገሪቱ ታሪክም ሆነ በማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ ሒደት ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱት ነገዶች አንዱ የሆነውን ዐማራ፣ በትሕነግ የሚመራው ኢሕአዴግ
Posted in Ethiopian News

የአብይ አህመድ የርቀት መነጽር መቀሌን ሲመለከት፣ ደምቢዶሎን ግን አይቃኝም

የአብይ አህመድ አገዛዝ ስልጣንን ከህወሃት ከወረሰ ወዲህ እጅግ ዘግናኝ የሆኑና በዓለም አቀፍ ደረጃም ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ጭፍጨፋዎች በአማራ ህዝብና በኦርቶዶክስ ተወኅዶ እምነት ተከታዮች ላይ እየደረሱ ነው። ለነዚህ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አብይ አህመድ በአብዛኛውና ወንጀሉን በመካድ አንዳንዴም በማቃለል ደንታ ቢስነቱን ሲገልጽ ቆይቷል። የጉዳቱ ሰላባዎች ግን ለሚደርስባቸው የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ተጠያቂው የአብይ አህመድ አገዛዝ እንደሆነ በማስረጃ አስደግፈው እያቀረቡ ነው። ከአንድ ዓመት በላይ ደምቢዶሎ ውስጥ አማራ በመሆናቸው ምክንያት በጥላቻ ባበደ መንጋ ታፍነው ጭካ ውስጥ የደረሱበት ስለማይታወቁ ልጃገረዶች አብይ አህመድ ምንም የሚተነፍሰው ነገር የለም። የአማራ ደም ከውሻ ደም ያነሰ ዋጋ ስለሚሰጠው ነው እንጅ ይህ ወንጀል ብቻ አብይ አህመድ የህዝብን ሰላምና ደህነት ማስጠበቅ ስላልቻለ ከስልጣኑ እንዲወገድ ማድረግ የሚገባው ነበር። አሁን ደግሞ አማራ ላይ ማላገጫና መሳለቂያ የሆነው ነገር መቀሌ ውስጥ የሚገኘውን ደብረ ፅዮንን ያለበትን ጉድጓድ መመልከት የቻለ የአብይ አህመድ የርቀት መነፅር (drone) ደምቢዶሎ ላይ የታፈኑትን ልጃገረዶች መመልከት አለመቻሉ ነው። ምናልባት በአገራችን በተደጋጋሚ መብራት ሲለሚጠፋ ይሆን ወይስ ባትሪ አልቆ ነው ማየት ያልተቻለው? ይህንን እጅግ የሚያሳዝን ነገር አስመልክተው ቀሲስ አስተአአየ ጽጌ ያስተላለፉትን መልዕክት አቅርበንላችኋል።  
Posted in Ethiopian News

እነ እስክንድር ነጋ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘደንትና ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዘደንት የፃፉት ደብዳቤ

እነ እስክንድር ነጋ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘደንትና ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዘደንት የፃፉት ደብዳቤ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዘደንትና ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዘደንት ጉዳዩ፡- የተፋጠነ ፍትህ ስለመጠየቅ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እነ እስክንድር ነጋ በተከሰስንበት የወንጀል መዝገብ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ምክንያቶች አቅርበን፣ ጉዳያችንን የያዘው ችሎት የተፋጠነ ፍትህ እንዲሰጠን መጠየቃችን ይታወሳል፡- 1ኛ. ተከሳሾች በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ የፖለቲካ ድርጅት አባላት መሆናችንን፣ 2ኛ. የታሰርነው በያዝነው ዓመት ይደረጋል ተብሎ እቅድ በተያዘለት ምርጫ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ በነበርንበት ጊዜ መሆኑን፣ 3ኛ. የክሱ አላማ፡- ሀ. ጥፋተኝነታችንን በፍ/ቤት አረጋግጦ ለማስቀጣት አለመሆኑን ለ. በኮቪድ 19 ሳቢያ ተዘግተው የቆዩት ፍ/ቤቶች ያሉባቸውን የተደራረቡ መዝገቦች ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ዋስትና የሚያስከለክል ክስ በመመስረት ጉዳዩ በእንጥልጥል እያለ በምርጫው እንዳንሳተፍ  ማድረግ መሆኑን፣ ሐ. በምርጫው እንዳንሳተፍ በፈጠራ ክስ የታሰርን መሆናችንን፣ መ. በተዘዋዋሪም ቢሆን፣ ፍ/ቤት የዚህ ህገ-ወጥ ተግባር ተባባሪ መሆን እንደሌለበት፣ 4. ፍ/ቤቱ ከምርጫ ጋር ባሉታዊ መልኩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ላለመነካካት ለመዝገቡ ፈጣን ውሳኔ መስጠት እንዳለበት፣ ይህንንም ለመተግበር የሚከተሉትን የመፍትሄ እርምጃዎች አስፈላጊ እንደሆኑ፣ ሀ. በ1998 ዓ.ም በእነ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል መዝገብ እንደተደረገው፣ ይህን መዝገብ ብቻ የሚመለከት ችሎት እንዲቋቋም፣ ለ. እንደገና፣ በ1998 ዓ.ም በእነ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል መዝገብ እንደተደረገው ጉዳዩ በየእለቱ በተከታታይ እንዲታይ፣ ሐ. በምርጫው የሚሳተፉ እጩዎች ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት በመዝገቡ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መሰጠት እንዳለበት አሳስበናል፡፡ በዚህም መሠረት፣ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም በነበረን ቀጠሮ ምላሽ እናገኛለን
Posted in Ethiopian News

በአክሱም ከተማ የዘንድሮው የህዳር ጽዮን በዓል አከባበርና የህወሃት ካድሬ “ካህናት”

  ከሊቃውንት አባቶቻችን የተማሩት በሊቃውንት አበው መንገድ የሚያቀርቡት ትምህርት የጥንቷን የዛሬዋንና የነገዋን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ትክክለኛ ማንነቷን ያሳያል። እባካችሁ ቤተ ክርስቲያናችን በጉባዔዋ በለዛዋና በስልቷ የማትወክላችሁ ጭምብል ለባሾች እንወክላለን ብላችሁ አትቅረቡ። መዕመናንም ጭምብል ለባሾችን ከቤተ ክርስቲያናችን ጋራ በማያያዝ እያቀረባችሁ ቤተ ክርስቲያናችንን የማይመጥን ነገር አታሰራጩ። በዘንድሮው የህዳር ጽዮ በዓል አከባበር ላይ ታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሐይማኖት መነሻ የሆነችው አክሱም ውስጥ ምን ተፈጸመ? ለነፍሳቸው ሳይሆን ለህወሃት ያደሩ ካህናት ምን የማይረሳ ነገር ፈጸሙ? በዚህ ዓመት በ 2013 አክሱም ውስጥ የተከበረውን የህዳር ጽዮንን እንዴት እንዳከበርነው እንዴት እንዳሳለፍነው የሚዘግበውን አቀረብንላችሁ።
Posted in Ethiopian News

አጅሪት ህወሓት ዛሬም በፓርላማው አባላት ዘንድ “አሸበርቲ” የሚለው የማእረግ ስሟ አልተሰጣትም በመምህር ዘመድኩን በቀለ

አጅሪት ህወሓት ዛሬም በፓርላማው አባላት ዘንድ “አሸበርቲ” የሚለው የማእረግ ስሟ አልተሰጣትም በመምህር ዘመድኩን በቀለ ቅር የሚለው ካለ ቅራሪ ይጠጣ ፥ እናንተም ሃሳባችሁን መስጠት መብታችሁ ነው። … የሚያስደንቀው ነገር… አጅሪት ህወሓት ዛሬም በተከበረው ፓርላማና በፓርላማው አባላት ዘንድ “ አሸበርቲ ” የሚለው የማእረግ ስሟ አልተሰጣትም። እንዲሰጣትም ፍላጎት ያለም አይመስልም። … አቢቹም ያን ሁሉ እነ አልሸባብ፣ እነ ቦኮሃራም፣ እነ አልቃይዳ እንኳ ያልሠሩትንና የልፈጸሙትን፣ እጅግ አደገኛና ነውረኛ በሰው ልጆችም ላይ የተፈጸመን ግፍ ስለፈጸሙት ህወሓቶች ዘርዝሮ ሲያበቃ ህወሓትን ግን አሁንም በዶሮ ማነቂያ ሰፈር የአራዳ ልጆች ቋንቋ “ ጁንታ” ብለው የመጥራት ምርጫቸውን አጽንተዋል። ወይ ጁንታ፣ ጀቶ፣ ጆተኒ፣ ሶቶ፣ አጃኳቢ፣ ጆካ … … በዚህ ምድር ላይ እንደፈለገ የሰውን ልጅ እያረደ፣ መሰረተ ልማት እያወደመ፣ በጅምላ እየጨፈጨፈ ወታደር፣ ቴሌቭዥን፣ ራዲዮ፣ ያለው፣ በፓርላማ መቀመጫ ያለው። ሮኬት ሚሳኤልም የሚተኩስ፣ ሙሉ የሰሜን ዕዝ የሃገሩን መከላከያ ሰሠራዊት በተኙበት የሚያርድ፣ የሚማርክ፣ እንደፈለገ የፈለገውን ያሻውን እንዲያደርግ፣ ባንክም ታንክም ያለው ሕጋዊ አሸባሪ ቡድን የፖለቲካ ፓርቲም ነኝ ባይ አላየሁም። … ሃገር እየመራ ሰፈሩን፣ ክልሉን፣ ጎጡን ገንጥሎ፣ ነፃ አወጣዋለሁ ብሎ በነፃ አውጪ ስም ሕጋዊ የምርጫ ቦርድ ፈቃድ አግኝቶ ተኮፍሶ ሼም ሳይሸምመው ለዘመናት የሚኖር አላየሁም። በዐማራ ገበሬ፣ በኦሮሞ አርሶአደር፣ በደቡብ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ ህዝብ ግብር ትግራይን አልምቼ ከኢትዮጵያ እገነጥላለሁ የሚል ነውረኛ ከሃዲ ወንበዴ በዓለም ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። … ትርፍ እንኳን ማምረት እንዳይችል የመሬቱ ተፈጥሮ የሚከለክለው መሬት ይዞ፣
Posted in Ethiopian News

የኅዳር ጽዮንና አክሱም ጽዮን ማርያም በመምህር ዘመድኩን በቀለ

የኅዳር ጽዮንና አክሱም ጽዮን ማርያም በመምህር ዘመድኩን በቀለ   በትግራይም ሆነ በኢትዮጵያ ተተክሎ ይመለክ ያስመልክ የነበረው ህወሓት የተባለ ዳጎን የተሰባበረበትና የደቀቀበትም ዕለት ነው። “ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።” መዝ 87፥5 ዛሬ የኅዳር 21/2013 ዓም ነው። የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ሀገራችን መናገሻ ከተማ በነበረችው አክሱም ከተማ ውስጥ በምትገኘው” በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን “ውስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ ታላቅ የሆነ ሃይማኖታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይፈጸማል። የዛሬው የኅዳር ጽዮን ማርያም በዓል ስለ 8 ዓበይት ነገሮች ይከበራል  ፩፣ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለን ስመ ጥር የአህዛብ ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበት ዕለትን በማሰብ። 1ኛ ሳሙ 1-6። ፪፣ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተ መቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ። 1ኛ፣ ነገ 8፥ 1-66። ፫፣ ታቦተ ጽዮን በንግሥት ሳባ ልጅ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ ምድር የገባችበትን ዕለት በማሰብ። ፬፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት በአብርሀ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት መሆኗ የታወጀበት ዕለት በመሆኑ። ፭፣ በብሉይ ኪዳን መስዋዕተ ኦሪት/የእንስሳት ደም ከሚሰዋባት ሙኵራብ / ወደ ሀዲስ ኪዳን/ አማናዊው በግ የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት /” ጽዮን ማርያም ተብላ ወደ ቤተ ክርስቲያንነት የተቀየረችበት ዕለት በመሆኑ። ፮፣ የቀደሙ ነብያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ህብረ አምሳል ያዩበት፤ ለምሳሌ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ኢትዮጵያና ቤተክርስቲያን” በሚል ርዕስ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዩቱብ ቻናል ላይ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያንን ጉዳይ አስመልክተው ከቀሲስ ጌታቸው ዘለቀ ጋር ያደረጉትን ውይይት አቅርበንላችኋል።  
Posted in Ethiopian News

“ዋይታና ለቅሶ ዐማራውን ከዘር ማጥፋት አይታደገውም!” ከዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

“ዋይታና ለቅሶ ዐማራውን ከዘር ማጥፋት አይታደገውም!”        ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. መግለጫውን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ የወለጋ የአማራ ጭፍጨፋ ላይ የተሰጠ መግለጫ ዐማራው በውስጥም በውጪም ወዳጅ የለውም።  በውስጥም በውጪም ያሉ የተደራጁና ያልተደራጁ ዐማራው እንዲጠፋ ተግተው የሚሠሩ ናቸው። ይህ ከ1888 ዓም የዐድዋ ጦርነት ድል ማግሥት ጀምሮ በተከታታይ ሢሠራበት የኖረ የሸበተ ሐቅ ነው። ከሁሉም በላይ ባለፉት 30 የትሕነግ/ኢሕአዴግ እና ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ በኦሕዴድ/ ኢሕአዴግ ዘረኛና ፀረ ዐማራ አገዛዝ ዐማራው በታቀደ፣ በተጠናና መዋቅራዊ በሆነ መንገድ በገፍ ተጭፍጭፏል፣ ተፈናቅሏል፣ ተገድሏል፣ ታስሯል፣ ተሳዷል። በኢትዮጵያ የመኖር የዜግነት መብቱን ተነጥቆ እንደክፉ ዐውሬ በተገኘበት እየታደነ ይገኛል። እስከአሁን ድረስ እየተካሄደ ያለውን ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ  መዋቅራዊና «መንግሥታዊ» መሆኑን ለመገንዘብ ብዙ ማሰብን አይጠይቅም። ይህንን እያየንና እያወቅን ይኸው አካል ለዐማራው ህልውና እንዲቆም መጠየቅ የዋህነት ነው። ሲበዛም ጅልነት ነው። ዛሬ በወለጋ በዐማሮች ላይ የተደረገው የዘር ፍጂት በ1980 እና 81 በሻዕቢያና በኦነግ ጥምረት በተመሳሳይ መልኩ የተፈጸመ ነው።  በማከታተልም በሐረርጌ አሰቦት ገዳም፣ በመቻሬ፣ በጉርሱም፣ በአስበተፈሪ፣ በአርሲ አርባ ጒጒ፣ በኤሊባቡር፣ በከፋ ጉራ ፈርዳ በቅንጅት ዐማራው በጅምላ ታርዷል፣ ተጨፍጭፏል። የዚህ ሁሉ አቀነባሪዎች የነበሩት ሌንጮ ለታ፣ ሌንጮ ባቲ፣ ዲማ ነገዎ፣  ዳውድ ኢብሣ ፣ ገላሣን ዲልቦ፣ ኩማ ዲመቅሳ፣ አባዱላ ገመዳ፤ ሽፈራው ሽጉጤ ወዘተ በሠሩት ወንጀል ከመጠየቅ አልፈው በሥልጣን ላይ ሥልጣን ተሰጥተው በዐማራው ላይ ተከታታይ ፍጅት እንዲፈጸምበት እያደረጉ ነው። የሕወሓት ስሪት የሆነው ብአዴንም በዐማራው ስም ወንበር ይዞ
Posted in Ethiopian News

ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን እንዴት ትገልጻታለች? የቀሲስ አስተርአየና ጽጌና መጋቢ ስርአት ጌታቸው ዘለቀ ውይይት

“ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን እንዴት ትገልጻታለች?” ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና መጋቢ ስርአት ጌታቸው ዘለቀ በቤተክርስቲያን ዕይታ ኢትዮጵያን እንደ አገር እንዴት እንደምትታይ ያደረጉትን እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ዝግጅት አቅርበንላችኋልና ተከታተሉት። “ኢትዮጵያዊነት ነፍስና ስጋ ነው”።
Posted in Ethiopian News

ከኦሞ የኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል ሰሞኑን በጉራፈርዳ፣ መተከልና ሌሎች ቦታዎች ውስጥ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ  በማውገዝ የተሰጠ መግለጫ

ከኦሞ የኢትዬጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል (OMO Ethiopia Unity and Justice Center) ሰሞኑን በጉራፈርዳና እንደዚሁም መተከል ወዘተ በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ  በማውገዝ የተሰጠ መግለጫ         October 27th 2020 እኛ ኦሞ ኢትዮጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል አባላት በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የተፈጸሙትን ዘር ተኮር ጥቃቶች በጥሞና ተከታትለናል:: ላለፉት ተመሳሳይ ድርጊቶች በጥፋተኞች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው እየተባለ ባለበት በአሁኑ ወቅት በመተከልና ጉራ ፈርዳ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ዘር ተኮር ጥቃቶች ያውም በተደጋጋሚ መፈጸማቸውን ስንረዳ  ልባችን ተሰብሯል:: ሐዘናችን ከባድ ሆኗል:: እስከዛሬ  እንደዚህ ያለ ጉዳት በሕብረተሰቡ ላይ በሚያደርሱት ላይ ሁኔታው እንዲገታ የሚያደርግ ተከታታይና የማያዳግም ጠበቅ ያለ ሕጋዊ እርምጃ  ሲወሰድ አይታይም ! ሰዎች ታሰሩ ሲባል ይሰማል: ግን ተፈረደባቸው ሲባል ብዙም አይሰማም:: መንግሥት ቀዳሚ ተግባሩና ሚናው የሕዝብን ሰላምና ደሕንነት በአራቱ የአገሪቱ ማዕዘናት የመጠበቅና የማስጠበቅ ኃላፊነት ከመንግሥታዊ ተግባሩ ዋነኛው ማድረግ ምንግዜም ይጠበቅበታል ፤ ስለዚህ የሚመለከታቸው ሰላምንና ደሕንነትን የማስጠበቅ መንግሥታዊ ተቋማት ሁሉ በተናበበ መልኩ ይህ መቋጫ ያጣው የዜጎች እልቂት እንዲገታ የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት ፤ ስለሆነም መጪውን ተመሳሳይ አደጋ  ለማስወገድ ግልጽ የሆነ መርህና ስልት እንዲኖረው የግድ ይላል::  ያለዚያ ጠባሳው መጪውንም ትውልድ ከቶውንም አይለቅም:: በዚህ ረገድ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ሞት የኦሞ ኢትዬጵያ አንድነትና ፍትህ ማዕከል ከባላት ልባዊ ሃዘናችንን ስንገልፅ እምላክ ሟቾችን በገነት ያኑራቸው: ፣  ለቤተሰቦቻቸው ዘመድ አዝማዶቻቸው ሁሉ መጽናናት ይስጥልን እንላለን። በዚህም ሰላምና መረጋጋት በአገራችን ይሰፍን ዘንድ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ የመጫወት ኃላፊነት
Posted in Ethiopian News

ለሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸመ ስላለው ጀኖሳይድ የቀረበ ተማጽኖ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጀኖሳይድ እንዲገታ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ድጋፍ እንድትሰጥ የቀረበ ተማፅኖ።
Posted in Ethiopian News

“የደመራ በዓል ለምን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ” የቀሲስ አስተርአየና የቀሲስ ጌታቸው ዘለቀ ውይይት

“የደመራ በዓል ለምን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ” በሚል ርእስ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና ቀሲስ ጌታቸው ዘለቀ ያደረጉትን ወቅታዊ ውይይት አቅርበንላችኋል።  
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያ ውስጥ አየተፈጸመ ስላለው ጀኖሳይድና የንብረት ውድመት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈለግለት ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ያወጣው መግለጫ። መግለጫውን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ አየተፈጸመ ስላለው ጀኖሳይድና የንብረት ውድመት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈለግለት ስለማሳሰብ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ (ኢ.ው.ቅ.ማ.ሰ.አ.) ጥር 2003 ዓ.ም. ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ያወረሱንን ታሪክ፣ ትውፊትና ቅርስ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍና ተተኪው ትውልድ በአገራችን ባሕልና ወግ እንዲታነጽ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷና አንድነቷ የተጠበቀ አንዲሁም ዜጎቿ በሰላም የሚኖሩባት አገር እንድትሆን የኢ.ው.ቅ.ማ.ሰ.አ. ጽኑ ምኞት አለው። ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ውስጥ ግምባር ቀደም የሆነውን የአድዋ ድል በማስመልከት የታሪክ ምሁራንን፣ ተመራማሪዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በመጋበዝ ለረዥም ዓመታት ውጤታማ ዝግጅቶችን አካሂዷል። ከዚህም በተጨማሪ በሜሪላንድ ክፍለ ሀገር ውስጥ በሚገኘው የሞንትጎመሪ አውራጃ ውስጥ የአድዋ ድል በአዋጅ እንዲዘክርና እንዲታሰብ አስደርጓል። ድርጅታችን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚመለከቱ ጉዳዮችን ይከታተላል። በዚህም መሠረት ካለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል አንስቶ በተለየ ሁኔታ በበርካታ የአገሪቷ ክፍሎች ውስጥ እየደረሰ ያለው ማንነትንና ሐይማኖትን መሠረት ያደረገ ጥቃት በእጅጉ አሳዝኖናል አስቆጥቶናልም። የተሳሳተ የፖለቲካ አስተሳሰብ የወለደው የጭካኔ ድርጊት የዜጎች ፍጅትን፣ ንብረት ውድመትን፣ ዘረፋን፣ የአብያተ ክርስትያናትን መቃጠል በማስከተሉ መራራ ሀዘንን አስከትሎብናል። ክርስቲያንና ሙስሊም ተከባብሮና ተፋቅሮ በሚኖርባት አገር ውስጥ በማናቸውም ቤተ እምነት ላይ የሚደርስ ጥቃት እጅግ ከባድ ወንጀል በመሆኑ በዝምታ መታለፍ እንደሌለበት እናምናለን። ኢትዮጵያዊያን በፈለጉትና በመረጡት ቦታ የመኖርና የመሥራት ህጋዊ መብታቸው ተጥሶ ለስደተኞች ሊደረግላቸው የሚገባ
Posted in Ethiopian News

“መተከል ውስጥ ለተጨፈጨፉት ወገኖች ዝም አልልም” ክፍል 3 በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ንጹሀን የአማራ ብሔረሰብ አባላትና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ላይ የሚደርሰው ጭፍጨፋ በአስከፊ ሁኔታ ቀጥሏል። የአማራ ክልል ሹመኞችም እንደለመዱት ህዝብን ማወናበዳቸውንና ማደናገራቸውን ቀጥለውበታል። የሚፈሰው የንጹሃን ደም ከገዳዮቹ ባልተናነሰ ሁኔታ በአማራ ክልልና በፌዴራል መንግስቱ  እጅ ላይ መሆኑ በስፋት እየተነገረ ነው። ይኸው መስከረም ከጠባ እንኳን ለሁለተኛ ጊዜ የአማራ ርስት በሆነችው መተከል ላይ የንጹሐን ደም እንደጎርፍ እየፈሰሰ ይገኛል። ዓለም እያየና እየሰማ በዝምታ ለግድያው ይደልዎ እያለ ነው። የሩዋንዳውንም ጀኖሳይድ እንደዚሁ ነው “አልሰማንም አላየንም” ያሉት።  የአማራና የኦርቶዶክስ እናት እንደ ራሔል እንባዋን ወደ ሰማይ እየረጨች ነው። “እግዚአብሔር እንዲህ ይላይ፣ የዋይታና የመራራ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች” ትንቢተ ኤርምያስ 31 ቁጥር 15  የመተከሉን ጀኖሳይድ አስመልተው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ከሆኑት ከቀሲስ ጌታቸው ዘለቀ ጋር ያደረጉትን ጠቃሚ ውይይት አቅርበንላችኋል። ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና ቀሲስ ጌታቸው ዘለቀ ብዙዎች በተለጎሙበትና እውነቱን መመስከር ተስኗቸው በፍርሃት ቆፈን በሚቆዝሙበት ጊዜ ክርስቲያናዊ ተልዕኳቸውን እየተወጡ በመሆናቸው ሊደገፉና ሊበረታቱ ይገባል።  
Posted in Ethiopian News

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በብስራተ ገብረኤል ቴሌቪዥን ያደረጉት ውይይት

Posted in Ethiopian News

ዘር ማጥፋት በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ህግ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌና መጋቢ ስርዓት ቀሲስ ጌታቸው ዘለቀ “ዘር ማጥፋት በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ህግ” በሚል ርዕስ ያካሄዱን ጠቃሚ ውይይት አቅርበንላችኋል።
Posted in Ethiopian News

የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ እንዲሁም ዘመድኩንና ዘበነ ሲመዘኑ

መጋቢ ስርዓት ጌታቸው ዘለቀ ከኒውአርክ፣ ኒውጀርሲ በሚስያስተላልፉት ብስራተ ገብርኤል ቴሌቪዥን ላይ ቀሲስ አስተርአየጽጌ በውይይት መልክ ያቀረቡን መልዕክት አቅርበንላችኋል። በዚህ አጋጣሚ መጋቢ ስርዓት ጌታቸው ዘለቀ በሚያስተላልፉ መርኃግብር ለቤተክርስቲያን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አንገብጋቢ ጉዳዮችን እያነሱ ምዕመናን ግንዛቤያቸውን እንዲያዳብሩ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የሚደገፍና የሚበረታታ መሆኑንን እንገልጻለን። ለወደፊቱም በዚሁ መልክ እንደሚቀጥሉበትና በተለይም ክህነታቸውን ለገንዘብ ማጋበሻና ኪሳቸውን ማደለቢያ ያደረጉና የተለያዩ የማይገቡ ድርጊቶችን በመፈጸም ቤተክርስቲያንን መነገጃ ያደረጉ ቀሳውስትን እያጋለጡ ምዕመናን ከእነሱ እንዲጠበቁ ትምህርት እንደሚሰጡ እንጠብቃለን። ቤተክርስቲያንን ለውጭ ጥቃት የሚያጋልጡ ከውስጥ ሆነው የቤተክርስቲያኒቷን ህግጋት በመጣስ ወንጀል የሚፈጽሙና የሚገዘግዙ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው።  
Posted in Ethiopian News

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለፍልሰታ ጾም በውይይት መድረክ ያደረጉት ቆይታ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እንዳመለከቱት የጾምና የሱባዔን ትርጉም ሳንረዳና ጠንቅቀን ሳናውቅ የምንጾም በሙሉ “እንደዘንዶ ሱባዔ“ ሆነናል ይላሉ።የሰው ልጅ ጾምና ሱባኤ “ዘንዶው የበላውና የዋጠው ሲከብደው (hibernate) እንደሚያደርገው አይደለም ። ዘንዶው የበላው ተቃጥሎ እስኪያልቅ አይመገብም። ከዛም የበላው ሲያልቅና አዲስ ቆዳ ሲቀይር በአዲስ ጉልበት ሊበላና ሊውጥ እየተንቀለቀለ ለአደን ይሰማራል። እኛም ክርስቲያኖች ንስሐ ሳንገባ፣ የሐዋርያትን ምሳሌነት ሳናውቅ የምናደርገው ጾም ከዘንዶው ጾም አይለይም”። የሰው ልጆች ጾም ግን እንደዚህ አይደለም በማለት ቀሲስ አስተርአየ ከወንጌል እያመሳጠሩ በጥያቄና  መልስ በብስራተ ገብርኤል ቴሌቪዥን የሰጡትን ትምህርት አቅርበንላችኋል።
Posted in Ethiopian News

“ውድነሽ አምሳሉ በፍቅር እስከመቃብር” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሐዱ አምላክ  ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ግንቦት 30 ቀን፡ 2012 ዓ.ም. [email protected] ውድነሽ አምሳሉ በፍቅር እስከመቃብር “ብኪ ወልድየ ላዕለ ዘሞተ ወላህወ ወአህምም ርእሰከ ወበከመ ግዕዙ  ግበር ሎቱ ተዝካሮ ወኢተጸመም ሞቶ ለዘተልእከከ” (ሲራክ 38 ፡16) ”በህይወት እያለ ያገልግሎት ውለታ ለሰጠህ ወገን አልቅስለት መታሰቢያውን ለመግለጽ አትርሳ“ ወይዘሮ ውድነሽ አምሳሉ የወይዘሮ ውድነሽን ሞት ከሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ከሰማሁባት ቅጽበት ጀምሮ ብዙ የተደራረቡ ትዝታወች እርስ በርሳቸው እየተጓተቱ መጡብኝ። ከታላቁ አባታቸውና ከመሳሰሉት ሊቃውንት ወይዘሮ ውድነሽ ስለ አገራችን ስለ ኢትዮጵያና፤ ስለ ቤተ ክርስቲያንችን የሰሙትን ይነግሩኝ የነበረው ሁሉ መጣብኝ።  በፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፋቸው “ከብዙ ስርዝና ድልዝ ጋራ የጻፍኩትን የመጀመሪያውን ረቂቅ በብዙ ትጋትና ጥንቃቄ እንደገና ደህና አርጋ ባትጽፍልኝ ኖሮ ብዙ  ችግር ይገጥመኝ ስለነበረ ውለታዋን አልረሳውም” ብለው ክቡር ዶ/ር አቶ አዲስ ዓለማየሁ የተናገሩላቸው ወይዘሮ ውድነሽ አምሳሉ ማርያም እንተ እፍረትንና ፌቤንንም አስታወሱኝ። ማርያም (እንተ እፍረት)እንድትታወስ የተነገረባትን ወንጌልንና ፌቤን እንድትታወስ የተነገረባትን መልእክት በእኩልነት እንደማናየቸው፤ ወይዘሮ ውድነሽ እንዲታወሱ የተነገረባት ፍቅር እስከ መቃብርን  ከሁለቱም ቅዱሳት መጻሕፍት ጋራ አናነጻጽርም። ይሁን እንጂ ማርያምንና ፌቤንን እንዲወሱ ያደረጋቸውን አገልግሎት ከወይዘሮ ውድነሽን  አገልግሎት ጋራ ብናመሳሰለው የምሳሌነቱ እርከን ብዙ የሚራራቅ አይመስለኝም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማርያም እንተ እፍረትን በወንጌሉ፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ፌቤን በመልእክቱ እንዲታወሱ ከፈቀዱላቸው፦  ስርዝ ድልዝ  (ራሳቸው እንዳሉት) የእጅ ጽሑፍ አስተካክለው በመጻፍ  ክቡር አቶ አዲስን  ያገለገሏቸውን፤ ይልቁንም እኛን በአካልና በቃል ያገለገሉንን እናታችን ወይዘሮ ውድነሽን  
Posted in Ethiopian News

ጎርጎርዮስ የደረሰው “መጽሐፈ ቅዳሴ”

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ማሰሰቢያ፦   ይህች ጦማር ጎርጎርዮስ በደረሰው መጽሐፈ ቅዳሴ ላይ የተመሰረተች  ናት። ጎርጎርዮስ የደረሰው መጽሐፈ ቅዳሴ  በ 18 ገጾች ተወስኖ፤  በ 107 ቁጥሮች ተከፍሎ በትንሣዔ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት በ 1994 ዓ/ ምህረት አዲስ አበባ በታተመው ከ14ቱ ውስጥ አንዱ ነው ። የጎርጎርዮስ ድርሰት ከገጽ 269 እስከ 286 ገጽ ላይ ኛል። የመጽሐፉ ይዘት በዚህ ዓመት የገጠመንን ካሮና ቫይረስ የመሰለ ክስተት ጎርጎርዮስን የገጠመው ይመስላል። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ራቁቷን የቆመች ቀን ሳምንት ወርና ዓመት የሉም የተደራረቡ ክስተቶችን በዓላት የተሸከሙ ናቸው ። በውስጥ ከሀዲወች በውጭ ወራሪወች የሚያስጠላትና የሚያስተቻትም  የድርብርብ ትዝታ ማህደርና መዘክርነቷ ነው። ሰው በማወቅም ባለማወቅም የሚያመጣቸው የመከራና የደስታ ክስተቶች በዕለታት በሳምንታት በወራትና በዓመት እየታዘሉ  የሚከሰቱ ናቸው። በተረት፤ በአፈ ታሪክ፤  በቅኔ በግድላትና በታምራት መጻሕፍት በብራና ይመዘገባሉ፤ በስም አጠራራቸው አማካይነት በዚያው ዘመን ተጸንሰው በሚወለዱ  ሕጻናት ሕሊና ላይም ይቀርጿቸዋል ። ከነሱ የተረከብናቸውን ክስተቶች የኛንም ደርበን በሚቀጥለው ትውልድ  ሕሊና ላይ እንድንቀርጻቸው በምሳሌነት አስተምረውናል። የዚህ ዓመት ሆሳዕና ደርባ ለያዘቻቸው ክስተቶች ሁሉ መታሰቢያ ትሆን ዘንድ እኔም የጎርጎርዮስ ቅዳሴ ያለንበትን ዘመን ሲቃኘው በሚል ርእስ በዘመኔ ላላችሁት ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቼ በዘንድሮው ሆሳዕና በዐል ላይ ተደርበው የተከሰቱትን አቀረብኩላችሁ። ================================*********============================ ጎርጎርዮስ  በዚህ ዓለም ስንት ዘመን እንደኖረና በዘመኑ ዑደት ውስጥ ሆሳዕናን ስንት ጊዜ   እንዳከበረው አላውቅም። የጎርጎርዮስን እዚህ ላይ ላቁመውና፤ ካይሮቫይረሷ ተከስታ ፊቴን በደቂቃ ስንት ጊዜ እንደምነከው ሲነገር እስክሰማ ድረስ እንደማላውቅ፤ እስካሁን
Posted in Ethiopian News

“ሆሳዕና” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አሰተርአየ ልክ የዛሬ 3 ዓመት በፊት የሆሳዕና በዓልን አስመልክተው የሰጡት ትምህርተ ወንጌል በተለይ አሁን ካለንበት ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር ቀጥተኛ መስተጋብር አለው ለማለት ይቻላል። ቀሲስ እንደገለጹት “ሆሳዕና“ ማለት ትርጉሙ “አሁን አድነን”ሲሆን እሳቸው የዛሬ 3 ዓመት በፊት በአገራችን ውስጥ የነበረውንና አሁንም ቀጥሎ ያለውን በፖለቲካ አስተዳደር፣ በቤተክህነት አመራርና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በሞላ ስላለው ምስቅልቅልና የተዛባና ሁኔታና እንዲሁም በህዝብ ላይ ያስከተለውን ችግርና መከራ በስፋት ወንጌሉ ከሚለው ጋር እያስማሙ ትምህርት ሰጥተውበታል። አሁን ደግሞ ከ 3 ዓመታት በፊት የነበረው ችግር መሻሻል ሲገባው ጭራሹን ተባብሶና ስር ሰዶ ከመገኘቱም በላይ የኮሮና ወረርሽኝ ደግሞ ተጨምሮበት የአገራችን ሁኔታ “በቡአ ላይ ጆሮ ደግፍ” ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በመላው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ደካማነታቸውንና አቅማቸው የተወሰነ መሆኑንና በአጠቃላይም የሰው ልጅ ልኩን ያወቀበት ጊዜ ነው። በወረርሽኙ ምክንያት ትልቅ ሰማይ ጠቀስ ተራራ ያክላሉ የተባሉ መንግስታት ኩይሳ መሆናቸውንና የሰው ልጅ ዕውቀትና ሀብት ከንቱና ባዶ መሆኑንና የእግዚአብሔርን ታላቅነት ፍጹምነት ለመረዳትና ወደ መንፈሳዊ ህይወት ለመመለስ በር የከፈተ አጋጣሚ ነው ለማለትም ይቻላል። ልዑል እግዚአብሔር ሁላችንንም ከበሽታው ይጠብቀን፤ የታመሙትን ሰዎች በሙሉ ይማርልን፤ የሞቱትንም ነፍስ ይማርልን! ለሁላችንም ወደ ህሊናችንና ወደ መንፈሳዊ ህይወት እንድንመለስ ልቦና ይሰጠን እያልን እውነትም በዚህ የኮሮና ወረርሽኝ አስጨናቂ ወቅት የዓለም ህዝብ በሙሉ“ሆሳዕና” ማለትም “አሁን አድነን” ብለን የምንማጸንበትና የምናለቅስበት ጊዜ ነው። የቀሲስ አሰተርአየን ትምህርተ ወንጌል ቪዲዮ እንድተከታተሉት ለሆሳዕና በዓል አስረጅ የሆነውን የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ከዚህ በታች
Posted in Ethiopian News

“ኒቆዲሞስ” የሚስጢረ ጥምቀትና የስነ አዕምሮ መገለጫ“ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ኒቆዲሞስ” “የሚስጢረ ጥምቀትና የስነ አዕምሮ መገለጫ“ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
Posted in Ethiopian News

“ቤተ መቅደሱን ማን በዘጋልኝ” (ሚል 1፡10) በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ       ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ                “ቤተ መቅደሱን ማን በዘጋልኝ” (ሚል 1፡10) በዚህ ፈታኝ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ህንጻ ውስጥ በህብረት የሚደረገውን ጸሎት አቁመን በየቤታችን መደረጉን ክህደት እንደሆነ የምታወሩ፤ የወሬኞችን ልፍለፋ ሰምታችሁ ቅር የተሰኛችሁ፤ ስለ ካሮናቫይረስ ተረድታችሁ ሳትሰለቹ ህዝባችሁን ለማስተማር በትግል ያላችሁ የስነ ፍጥረት ተማሪወች፤ የራሳችሁን ሰውነት ሰውታችሁ የወገናችሁን ህይወት ለማትረፍ በትግል ያላችሁ ሀኪሞች ይህች ጦማር ትድረሳችሁ! በደቂቀ አዳም ላይ የሞት ጥላዋን ከዘረጋቸው ኃያሏ ኢምንት ህዋስ እንድንጠነቀቅ የስነፍጥረት ተማሪወች የሚነግሩን ነብያት ክርስቶስ ሀዋርያት ከተናገሩት ጋራ ተመሳሳይ እንጅ የሚቃረን አይደለም። በቤተ ክርስቲያን ህንጻ ውስጥ በህብረት የሚደረገው ጸሎት መቅረቱንና፤ በየቤታችሁ ጸልዩ መባሉን አንዳንድ ሰወች እየተቃወሙ በሚነግሯችሁ ከመቆጣትና እንደ ክህደትም ከመቁጠር ይልቅ፤ ማዘንና እንደ ክህደትም ልንቆጥረው የሚገባን ምን እንደሆነ ልንረዳ ይገባል። አምላካችን የምናየውን የምንዳስስውን አቅማችን የሚያሸንፈውን ጠላት ታግለን እንድናሸነፍ ጥበቡን ኃይሉን ብርታቱን ይሰጠናል፤ ከማናየው፡ ከማንሰማው፡ ባቅማችን ታግለን ከማናሸነፍው ከረቂቅ ጠላት እንዲሰውረን ቆመንም ተቀምጠንም ተኝተንም ቢሆን ከያለንበት የምናቀርብለትን የምህላ ድምጽ ይሰማናል። በህንጻ ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን በማህበር የምናቀረበው ምህላ ለጥያቄ የሚቀርብ ባይሆንም፤ ይህን በመሰለ ወቅት በየቤታችን ተወስነን በምናቀርበው ጸሎት ላይ መጠራጠር ደግሞ አምላካችንን በህንጻ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ ማድረግ ትልቅ ክህደት ነው። በቤተ ክርስቲያን ብቻ መጸለይም አማራጭ እንደሌለው አድርጎ መቃወም አይገባም። ልንቃወም የሚገባን፤ ራሳቸውን ነብያት አድርገው “ መአቱ እስኪያልፍ ድረስ ” ገለል በሉ የሚለውን የነብያትን ቃል በድፍረት የሚቃወሙትን ነው። ይህን የመሳሰሉ ቸነፈሮች
Posted in Ethiopian News

“ገብርሔር” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ገብርሔር” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
Posted in Ethiopian News

“ደብረ ዘይት” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ደብረ ዘይት” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  
Posted in Ethiopian News

“ከነአቶ በቀለ ገርባ ኮረዳ የቀረበልን የፍታት ጥሪ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

በነአቶ በቀለ ገርባ ኮረዳ ለኢትዮጵያ ህዝብ የቀረበ የፍታት ጥሪ የቆየ ትዝታየን አስታወሰኝ። “ከራሳችሁ ባህል ወጥታችሁ ከኛ ከእንግሊዞች የተወረሰውን ፍታት አደነቃችሁ። አስተርአየ ግን የኢትዮጵያን ባህላዊ ፍታት እንደያዘ ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ወደ ሰውነት የሚጠጋው ኢትዮጵያዊው የፍታት ባህል ነው። እናንተ ግን ከራሳችሁ  ባህላዊ ስርአተ ፍታት ርቃችኌል” ብለው እንግሊዛዊው መምህሬ ዶ/ር ስሚዝ የተናገሩት  ትዝ አለኝ።  ሲፈቱና ሲያፋቱ የኖሩት ወያኔወች ከቤተ መንግሥት ከራቁ በኌላ፤  ምንም እንኴ  ቤተ ክርስቲያችን የገጠማትን ችግር  በማትገልጽበትና  በማይመጥናት ጫጫታ የሚካሄደውን ብዙወቹ መናገር ቢሞክሩም  ያፍ መፍቻ ንግግር ጫጫታ መስሎ ስለታየኝ፤ የ ጫጫታ አዳማቂ ላለመሆን ብየ  ብዕሬን አስሬ አፌን ዲዳ ለማድረግ ወስኘ ነበር። ለሚያግበሰብሰው ትርፍ ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ ወያኔ ያስረኛል፤ ድርጅቴ ይዘጋብኛል ብሎ አፉን ዘግቶ የኖረው ሸፍጠኛ የወንጀል ሰባኪ ሁሉ አፉ ቢፈታም፦”ትዳር ፍቱ እኔን አግቡ“ ያለች በሽህ ለሚቆጠር ወንድ ያለምንም ሀፍረት ራሷን ያቀረበችውን ኮረዳ ሳይ ዝምታየ ተሰበረ። ስለፍትሀት ከመንደሬ ሳድግ ካየሁት ከኢትዮጵያውያንና ከፈረንጆች መምህሮቼ ከተማርኩት ጥቂት ላካፍላችሁ። ካብነቱ መምህራን የተማርኩትን ላስቀድም። በሰባት ነገሮች ተጣምሮና ተጠናቅሮ የተሰራው ሰው በዚህ ዓለም የሚኖረው ዘመን ሲያበቃ ጥንቅርነቱ ይፋታል ይበታተናል። በመፋታት ይሞታል። በፍታት ወደ መቃብር  ይሸኛል። አትናቴወስ “ኢንክል አብጽሆተ አዕምሮቱ ዘከመ ኀብሩ አርባእቱ ጠባዕያት ከሃሊ እግዚአብሔር ገብረ ሰብአ አስተናቢሮ በውስቴቱ መንፈሰ ሕይወት እንዘ ኢይኀብር እሳት ምስለ ማይ ወመሬት ምስለ ነፋስ ” (ሃይ 28፡31) እንዳለው፦ ማለትም፦ ልንተረጉመው በማንችለው ጥበቡ እግዚአብሔር ተቃራኒ የሆኑትን ነፋስንና መሬትን ውሀንና እሳትን አስማምቶና አጣምሮ 
Posted in Ethiopian News

124ኛው የአድዋ ድል በአል መምህር ታየ ቦጋለ በሚገኙበት ይከበራል

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ ለ9ኛ ጊዜ በምናከብረው በዓል ላይ ሁላችሁም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንድትገኙልን ጋብዘናችኋል።   ቀን፤ ቅዳሜ፣  የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፪   ዓ.ም. (Saturday, February 29, 2020) ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከ 1:30 PM ጀምሮ እስከ 6 30 PM ቦታ፤ 1 Veteran Place in Silver Spring, MD 20910  
Posted in Ethiopian News

ዓመታዊ የአድዋ ድል በዓል ዝግጅት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ (ኢ/ው/ቅ/ማ/ሰ/አ/) የተቋቋመው ጥር 2003 ዓ.ም. (ጃንዋሪ 2011) ሲሆን ከመሠረተ ዓላማዎቹ ውስጥ ዋነኛው የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ትተውልን ያለፉትን ታሪክ በመዘከር ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍና ለተተኪው ትውልድ ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ ነው። ካለፉት ታላላቅ የኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ውስጥ አንዱና ዋነኛው የአድዋ ድል እንደሆነ ይታወቃል። የአድዋ ድል የዓለም የታሪክ ትርክት አንዲቀየር ያደረገ የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝቦች ሁሉ መኩሪያና መመኪያ ነው። የአድዋ ድል ቀደምት ኢትዮጵያዊያን ተባብረው ከውጭ የሚመጡባቸውን ማናቸውንም ወራሪዎችንና ጠላቶችን ድባቅ እንደሚያስገቡ ያሳዩበት ገድላቸው ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያዊያን በጀግነነት ጠላቶቻቸውን የሚፋለሙ፣ ለነጻነታቸው ቀናዒ መሆናቸውንም ለዓለም ያስመሰከሩበት በወርቅ ቀለም የተጻፈ ታሪክ ነው። የአድዋ ጦርነት ለማካሄድ በአጼ ሚኒሊክ መሪነትና በእቴጌ ጣይጡ ብጡል አስተባባሪነት ኢትዮጵያዊያን እንደ አንድ ልብ መስካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው ቋንቋ፣ አካባቢ፣ኃይማኖትና ጾታ ሳይለያያቸው በአንድነት በመትመም እጅግ ዘመናዊ የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀና የሰለጠነ ሰራዊት ይዞ የመጣውን የጣሊያን ወራሪ ኃይል በባዶ እግራቸው ተጉዘው በጦርና በጎራዴ ድምጥማጡን አጥፍተው ደምስሰውታል። ይህ ኢትዮጵያዊያን ያስመዘገቡት ታሪክ በቅኝ ግዛት ተይዘው ይማቅቁ ለነበሩ በአፍሪካ፣ ካሪቪያንና አሜሪካ ውስጥ ለሚኖሩ ጭቁን ህዝቦች ለነጻነታቸው መታገልና የሚያስፈልገውን መስዋዕት መክፈል ብቸኛው የነጻነታቸው መቀዳጃ መንገድ እንደሆነ በተግባር ትምህርት የሰጠ ክስተት እንደነበር በታሪክ ተመራማሪዎችን ምሁራን በስፋት ይጠቀሳል። የኢ/ው/ቅ/ማ/ሰ/አ የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት የታሪክ ምሁራንን፣ ተመራማሪዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በመጋበዝ እንዲሁም የዋሽንግተን ዲሲ ከተማንና የሜሪላድ ክፍለ ኃገር ሞንትገሞሪ አውራጃ  አስተዳዳሪዎችን የአድዋ ድል የተደረገበትን
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያና ጾመ ነነዌ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ከዛሬ የካቲት 2 እስከ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. (February 10-12, 2020) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ሆና እየተጾመች ስለምትገኘው ነነዌ ጾም ምክንያት በማድረግ “ኢትዮጵያና ጾመ ነነዌ” በሚል ርዕስ የሰጡትን ትምህርት አቅርበንላችኋል። የነነዌን ህዝብ ከታዘዘ መቅሰፍት ያዳነ እግዚአብሔር አገራችንንም በአሁን ጊዜ እየደረሰባት ካለው መከራና ፍዳ ይገላግላት!
Posted in Ethiopian News

መምህር ታየ ቦታለ በሚገኙበት 124ኛው ዓመት የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያ ዝግጅት በአሜሪካ

The AMAZING Taye Bogale: A Force of Nature on the ... የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ (ኢ/ው/ቅ/ማ/ሰ/አ/) ሁሉንም ኢትዮጵያዊ፣ትወልደ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጆችን የአድዋ ድል በዓልን አስመልከትን በምናደርገው ዓመታዊ ዝግጅት ላይ እንዲገኙልን እንጋብዛለን። በዘንድሮው ዝግጅታችን ላይ ታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ መምህር ታየ ቦጋለ ተገኝተው ትምህርታዊ ገለጻ ይሰጣሉ።  “የተረሳ ታሪክ የተረሳ ጥበብ ነው” ታየ ቦጋለ” የኢ/ው/ቅ/ማ/ሰ/አ/ ከመሠረተ ዓላማዎቹ ውስጥ ዋነኛው የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ትተውልን ያለፉትን ታሪክ በመዘከር ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍና ለተተኪው ትውልድ ትምህር እንዲሰጥ ማድረግ ነው። ካለፉት ታላላቅ አኩሪ ታሪካችን ውስጥ አንዱና ዋነኛው የአድዋ ድል ነው። የአድዋ ድል የዓለም የታሪክ ትርክት አንዲቀየር ያደረገ የአፍሪካና የመላው ጥቁር ህዝቦች ሁሉ መኩሪያና መመኪያ ነው። ኢትዮጵያዊያን ከውጭ የሚመጡባቸውን ማናቸውንም ወራሪዎችንና ከውስጥ የሚነሱ የአገር ጠላቶችን ድባቅ እንደሚያስገቡ ያሳዩበት ገድላቸው ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያዊያን በጀግነነት ጠላቶቻቸውን የሚፋለሙ፣ ለነጻነታቸው ቀናዒ መሆናቸውንም ያስመሰከረ ምንጊዜም የማይረሳ አኩሪ ታሪካችን ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከ124 ዓመታት በፊት አንድነቱን ጠብቆ በታሪክ ሰገነት ላይ ከፍተኛውን ቦታ እንዲይዝ ያስቻለውን የአድዋ ድል አሁንም ባለንበት ዘመን አንድነቱን አጠንክሮ ቢይዝ ተዓምር የሚሰራ ህዝብ ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። የአንድነታችን አኩሪ መገለጫ የሆነውን የአድዋ ድል በዓል ኢትዮጵያዊያን በጋራ ማክበራችን ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊነቱን የኢ/ው/ቅ/ማ/ሰ/አ አበክሮ ያምናል። ቀን፤ ቅዳሜ፣  የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፪   ዓ.ም. Saturday, February 29, 2020 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ 1:30 PM ቦታ፤ 1 Veteran Place in Silver Spring, MD 20910 የበለጠ መረጃ  ለማግኘት ድረ ገጻችንን http://ehsna.org ይጎብኙ። ካስፈለገም አቶ ነጋሽ ገብሬን 410-241-4764 በመደወል
Posted in Ethiopian News

ስለአባይ ወንዝ በመደረግ ላይ ስላለው ድርድር የተሰጠ አስተያየት

ነገር ሳይበላሽ ቶሎ ቢደርስልኝ ሰመረ አለሙ ይህ ጽሁፍ የቃላት ዉበት የሚያስፈልገዉ ሳይሆን ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ በመሆኑ ኢትዮጵያዉያን እንዲመክሩበት ታስቦ የተላከ በመሆኑ ይህን ነገር አንባቢ ትኩረት ሰጥቶ እንዲወያይበት ለመንግስት ቅርበት ያላቸዉም ይህን ታክኮ የችግሩን አሳሳቢነት ለአመራሩ እንዲያቀርቡ የታሰበ አስቸኳይ መልእክት ነዉ። ኢትዮጵያ በታሪኳ ከደረሰችባቸዉ ታላላቅ ስምምነቶች መካከል ዋናዉ በአስተዋዩ መሪያችን በዳግማዊ አጼ ምንሊክ አማካይነት በደም ማህተም አደዋ ላይ ማስተካከያ የተደረገበት የዉጫሌዉ ዉል ሲሆን ቀሪዉ ግን እስከ አሁን ህልዉናችን ላይ ተጋርጦ ለተከታዩ ትዉልድ መፍትሄ እንዲፈልግለት የተተወ  የሀገር እዳ ሁኖ ትዉልድ ሲቀባበለዉ እዚህ ደርሷል። ኢትዮጵያ ስምምነት ተበላሺቶባት ዋጋ ከከፈለችባቸዉ ጉዳዮች መሀከል የወደፊቱ ከግምት ሳይገባ አገር የሚያህል ቦታ በኤምባሲዎች መያዙ ኤርትራ ከእናት አገሯ ተገንጥላ ስትሄድ በወያኔዎች መንግስት ያደረገዉ አሳፋሪ ስምምነትና አሁንም በወያኔዎች መንግስት ስምምነት ለሻቢያ የተሰጠዉ በወያኔዎች መሬትና የባህር በራችን ዋና ዋና ጉዳይ ሁኖ በቅርቡ ደግሞ የኢትዮጵያ ተስፋ የሆነዉ አባይን ኢትዮጵያዊ ወይም ግብጻዊ ለማድረግ የሚደረገዉ ፍትጊያ ነዉ። ከግብጽ በኩል የግብጽ ህዝብ፤ ምሁራን፤ ጋዜጦች የሞት የሺረት ትግል አድርገዉ ይህንን ጉዳይ ወጥረዉ ሲይዙ በኢትዮጵያ በኩል የዶ/ር አብይ መንግስት አያገባችሁም በሚል መልኩ ጉዳዩን ከዜጎች ሳይመክር በዝግ ስብሰባ ነገሩን ለመቋጨት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስተሩን ወደ ልእለ ሀያሉ አገር አሜሪካ ልኳል። በዚህ ጉዳይ አልሲሲ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ተጉዞ፤ አረብን አሳምጾ፤ አሜሪካንን ለምኖ፤ ከምሁራንና ከጦር ሰዎች መክሮ፤ትላልቅ የገንዘብ ተቋማትን ከጎኑ ሲያደርግ በተራዉ የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በሩን አስረክቦ፤ መሬቷን በሀይል የቀሙትን ሀይሎች
Posted in Ethiopian News

የጥምቀት በዓል ለኢትዮጵያ ምንድን ነው?በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የጥምቀት በዓል ለኢትዮጵያ ምንድን ነው? የጥምቀት በዓል ለኢትዮጵያ የመንፈስና የሥጋ ነጻነት መከላክያ ነፍጥ።  የመዋጊያ ሰይፍ ትጥቅ፤ የማድፈጫ ሸለቆና ሸንተር፤ የሩቅና የቅርብ ወዳጅና ጠላት መቃኛ ተራራና  ኮርብታ፤   የክተት ሠራዊት አዋጅ መጥሪያ ነጋሪት፤  የዘመናትን መመልከቻ መነጸር። ሌባ የማይሰርቀው፤ ምስጥ የማያበላሸው በህዝብ ህሊና ላይ የተጻፈ መጽሐፍ ነው። ካብነት አባቶች እንደሰማሁት የጥምቀት በዓል  ከነገረ መለኮቱ  መለኮቱ በመጀመር የገለጽኳቸው ለጥንታዊት ኢትዮጵያ ሁለንተና እንደሆነ  በጽሑፍም በዩትብም  በያመቱ ደጋግሜ ገልጫለሁ ። የበዓሉ መሠረት የክርስቶስ መጠመቅ ነው። ክርስቶስ በዮርዳኖስ  ወንዝ በዮሐንስ መጠመቁን  መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብ ሁሉ ያውቀዋል። ክርስቲያናዊ ትርጉሙንም በተቀራራቢ መንገድ ይሳተፈዋል።   ቢሆንም “የጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ” እያለ እንደኛ የሚያከብረው የለም። የጥምቀት በዓል ኢትዮጵያዊ ሁለንተና መሆኑን ፤  ከ 6 ዓመት በፊት በዩትብም በጽሑፍም በተደጋጋሚ ባቀረብኴቸው ዝግጅቶች  ብሄራዊ ሁለንተና እንደሆነ፤ በ13 ገጾች በተለይም ከገጽ 5 ጀምሮ እስከ መጨረሻ ባለው ክፍል መግለጼን ያነበባችሁ እንደምታስታውሱት ተስፋ አደርጋለሁ። ይልቁንም በ3 ኛው አንቀጽ ከፊደል ሀ እስከ ፊደል መ  ላይ የሰፈሩት  የጥምቀት በዓልን ኢትዮጵያዊ ሁለንተናነት በከፊል ገልጾታል። በጥልቅ መገንዘብ ለሚፈልግ በመጀመሪያ የቀረበውን ማንበብ ይችላል። በዚህ ዓመት ያዘጋጀኌት ይህች ጦማር ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ለቀረበው መንደርደሪያ ሆና ዘንድሮ የተደረበው ክስተት ለማስታቀፍ እንጅ በመሰረታዊ ይዘቷ ላይ በዚህ ዓመቱ ከተከሰቱት ክስተቶች በቀር የሚጨመር ነገር የለም። ይህን ስል የኔን ውሱኑነት ለመግለጽ እንጅ፤ በሚሊዮን የሚቆጠር አድናቂ፤ በ50 ሚሊዮን በላይ ልጆችን በብዙ የሚቆጠሩ ሊቃውንት ያሏትን የቤተ ክርስቲያናችንን ስፋትና ጥልቀት ለመወሰን አይደለም።
Posted in Ethiopian News

የቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ሊደመጥ የሚገባው ወቅታዊ ትምህርት ወንጌል

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ሊደመጥ የሚገባው ወቅታዊ ትምህርት ወንጌል ሰጥተዋል። ተከታተሉት።
Posted in Ethiopian News

“ከሰሜን አሜሪካ ካህናት ማህበር” የተላለፈ የእርዳታ ጥሪ

ከዚህ በታች ያለው መልዕክት የተላለፈው “ከሰሜን አሜሪካ ካህናት ማህበር“ ነው። እራሱ አስረጅ የሆነውን   ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች ሙሉ ቃሉን አቅርበናል። https://www.gofundme.com/f/support-faithful-and-churches-in-rural-eotc?utm_source=customer-andr&utm_campaign=p_cp+share-sheet&utm_medium=sms በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ይህን የእርዳታ ገጽ የሚያስተባብረው የሰሜን አሜሪካ ካህናት ማኅበር ነው:: የሚለገሰው ስጦታ (donation) በማኅበሩ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ሆኖ እና በኦዲት ተመዝግቦ ለተጎዶ ወገኖች እና በቤተክርስቲያን ተጠልለው ላሉ የሀገራችን ሕዝቦች እንዲደርስ ይደረጋል:: በሰሜን አሜሪካ ካሉ ሀገረ ስብከቶች፣ በኢትዮጵያ ካለው ቤተክህነት፣ የተለያዩ በጎ አድራጊ ማኅበራት፣ እና ቀይ መስቀል ጋርም በጋራ በመስራት አስቸኳይ እርዳታ እናደርጋለን:: For more info – Contact: Finance & Treasury – (206) 834 – 5278 Secretary Office – (571) 501 – 9984 This page is organized and lead by Ethiopian Orthodox Tewahedo Clergy association in North America (and lead by Finance & treasurer department heads, as they also submitted their full Information on registration.) This fund will go to the bank account, for accountability and auditing, then it will be released to the peoples directly with our assigned Executives, who are currently in Ethiopia. We are also working with North America all Dioceses and Arch Bishops, EOTC main office in Addis Ababa, Other associations, and The Red Cross, for Urgent support and humanitarian assistance. 42996788_1572312482643974_r.jpeg ማኅብረ ካህናት ዘሰሜን አሜሪካ: በኢትዮጵያ በሃይማኖታቸው ምክንያት አካላዊ
Posted in Ethiopian News

ለፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተለከ መልዕክት

ጥቅምት 29 ቀን 2ሽ 11 ዓ/ም ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ፦ የአኩስም ሊቀ ጳጳስ እና የደብረ ሊባኖስ እጨጌ፦ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ብጹዕ ወቅዱስ ሆይ! ቋሚ ሰው ለሞተ ወገኑ “በረደህ ላልብስህ፡ ዘቀዘቀህ ላንተርስህ፤ ራበህ ላጉርስህ፤  አይልም። የሚሰጠው እንባ ብቻ ነው። በመንበረዎ ተቀምጠው በአረመኔወች ለታረዱ ልጆቼዎ የሰጧቸውን እንባ ተመለከትኩ። ከቅኔው ቆጠራ ብንን ብየ ራቡ ሲሰማኝ፤ ከደጃፍ ቁሜ በእንተ ስማ ለማርያም ስል ድምጼን ሰምታ ደረቷን እየደቃች እኔን ይራበኝ እያለች ከልጆቿ ሳትለይ ያስተማረችኝ ርኅሪት እናት መታረዷን ስሰማ፤ ከመንደር እስክወጣ ድረስ ተናካሽ ውሻውን እየተከላከለልኝ “ተሜ አይዞህ በርትተህ ተማር” እያለ ያስተማረኝ አባ ወራ ጭንቀቱን መከራውን  ከባህር ማዶ ሆኜ ስሰማ እኔም ቅዱስነተዎ ያነቡትን እንባ ተጋራሁ። ለቅዱስነተዎ  አላቃሽም አነጋጋሪም አጽናኝም ብጹአን አቡኖች በአካባቢዎ  አሉሉዎ። ከውቅያኖስ ማዶ ላለሁት ለኔ ግን በደስታም ሆነ ይህን በመሰለ አሰቃቂ ዘመን በመጻህፍቶቻቸው አማካይነት የከበቡኝ አማካሪወቼና የሚያጽናኑኝ እነ ቅዱስ ጳውሎስ፤ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ እነ ቅዱስ ቄርሎስና በዝክረ ሊቃውንት መጽሐፋቸው እነ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ብቻ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ ብትኖሩ ምን ትሉ፡ ምንስ ታደረጉ ነበር?ብየ ከላይ የጠቀስኳቸውን አባቶች በመጻሕፍቶቻቸው አማካይነት ጠየኩ።  ከሰፊው ምክራቸው  የመረዳት አቅሜ የፈቀደለኝን ጨልፌ ከዚህ በታች እገልጻለሁ። ቅዱስ ጳውሎስ ፋታ ሳይሰጥ የቀጠለውን መከራ “ወኢረከብነ ወኢአሐተኒ ዕረፍተ ለነፍስነ ወበኩሉ አኅመመነ በአፍአኒ ቀትል ወበውስጥኒ ፍርሀት“ (2 ቆሮ 7፦5) እያለ ከዘረዘረ በኋላ፤ መልእክቱን እንዲጽፍ የተገደደበትን ምክንያት ”ወዘኒ ዘጸሀፍኩ ለክሙ አኮ
Posted in Ethiopian News

አህያዬን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊዬ ሲሆን  አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ?በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

አህያዬን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊ ሲሆን  አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ?ይህ አባባል ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብሎሽ እየተሻገሩ ዘመን ካቌረጡት ከብዙ ክስተቶች አንዱ እንደሆነ አበው ይናገራሉ። እኛ የኦርቶዶክስ ይማኖት መምህራን፤ “ለትውልደ ትውልድ ዘኢየኀልቅ ለዓለም ዓለም” ብሎ በሚደመድመው በየመንፈቀ ሌሊት በምናደርሰው  ጸሎተ ኪዳናችን  ትንሹንና ትልቁን ህዳጡንና መንጋውን ህብረተሰቡን አጠናቅሮ  በመምራት ላይ ያለውን ተወራራሽ  ምድራዊ መንግሥት እንቃኝበታለን። በአመጽም ሆነ በሰላም ቅብብሎሽ እየተፈራረቀ ከትውልድ ወደ ትውልድ በመሻገር ላይ ያለው ምድራዊና ጊዜአዊ መንግሥትም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥት እንደሚዋጥ እናስተምራለን። ኢትዮጵያውያን መተርጉማን ይህን ሐረግ ከመሳሰሉት ምንባባት በመነሳት፤ እንደ እኛ በቅኝ ግዛት ሳይወረር በኖረ  ሕብረተ ሰብ የሚነገሩት በብራና ባይጻፉም ተረቶች ወይም ፈጠራዎች አይደሉም። ባንድ ትውልድና ዘመን ተከስተው ዘመናትን  እየተሻገሩ በቅብብሎሽ የመጡ ናቸው“ እያሉ ነግረውናል። ”አህያየን የሰረቃት ሌባ፤ ራሱ ደብቆ አፈላላጊየ ሲሆን  አህያየን እንዴት ላገኛት እችላለሁ?የሚለው ክስተት  በጽሑፍ ባይቀረጽም በቃል ንግግር ቅብብሎሽ በየትውልዱ የሚደርስ ነው። ይህን የመሳሰሉ ክስተቶች ከረዥም ዘመን በኋላ ባዲሱ ትውልድ ላይ ሲወድቁ፤ አዲሱ ትውልድ ለመቀበል  እየከበደው ተረት ይመስሉታል።  ግን ቅርጻቸውን፤ ይዘታቸውንና ትርጉማቸውን እየቀያየሩ በየትውልዱ የሚከሰቱ አማናውያን ናቸው ይላሉ።  “ለትውልደ ትውልድ ዘኢየኀልቅ ለዓለም ዓለም” በሚለው ምንባብ ላይ የተመሰረተው ሐተታ እንደሚጠቁመን፤  ቀዳማዊው መንግሥት በደሀራዊው መንግስት እየተዋጠ በሚሻገር እንደ ኢትዮጵያ በመሰለ ኅብረተሰብ የሚነገሩ አፈታሪኮች ካለፈው ትውልድ አካል ጋራ አይቀበሩም።  ከማይቀበረው  ታሪክ ጋራ በትኩረት ሊጠኑንና ሊመረመሩ የሚገባቸው ናቸው። የቀደሙ አባቶቻችን በግል አካላቸው በመቃብር ቢወሰኑም፤ ባወረሱን አካላቸውና በሰሩት ታሪካቸው በነገሩን ትንግርታቸው
Posted in Ethiopian News

“መስተጻምር” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ማስታወሻ፣ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ “መስተጻምር” በሚል ርዕስ ያዘጋጇት መጣጥፍ ኢትዮጵያ እንዴት የረዥም ዓመታት ሉዓላዊነቷንና አንድነቷን ጠብቃ እንደኖረችና የቀደሙ አባቶች በምን ዘዴና ብልሃት አገሪቱን በአንድነት አስተባብረው እንዳስተዳደሩ የምታሳይ ሲሆን ጊዜያችሁን ወስዳችሁ ብታነቧት ትልቅ ቁም ነገር እንደምታገኙበት በማመን ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል። ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ የቀደሙ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አባቶች የመደመርን ጽንሰ ሀሳብ እንዴት ይመለከቱት ነበር? ተብሎ በድያስፖራው ለተነሳው ጥያቄ ከሞላ ጎደል ለመመለስ መጀመሪያ ጳጉሜ  2ሽ 10 ዓ/ም በኢትዮጵያ ኢማባሲ ዋሽንግተን ዲሲ  አዳራሽ  ይህች ጦማር ቀረበች ። እንደገና ታህሳስ 11 ቀን 2011 ዓ/ ም አዲስ አበባ ላይ በተደረገው ስብሰባ ቀረበች። ለቤተ ክርስቲያናችንም ሊቃውንት ጉባዔና ለሚመለከታቸው ተቋማትም ቀርባለች። “የመደመር ጽንሰ ሀሳብ ባባቶቻችን ግንዛቤ ምን እንደነበረ ወጣቶች ሰምተውት ስለማያውቁ፤ የዘመናችን ልሂቃንም በማወቅም ባለማወቅም  እየናቁና እያጣጣሉ ከውጭ በወረሱት አፍራሽ ሀሳብ ህብረተ ሰቡን ግራ እያጋቡት ነው።  ኢትዮጵያውያን እንዲነጋገሩባት፤  በያቅራቢያቸውም ላለው ወጣት እንዲያሿግሯት እንደገና ትቅረብ” ብለው የዲያስፖራው ጉባዔ በባህር ዳር ከተማ በሰኔ ወር መደረጉን የሰሙ ወገኖች ደጋግመው ጠየቁኝ። ስለዚህ እንደገና እንድትቀርብ የተገፋፋሁበትን ምክንያት የምገልጽበትን እንደ መቅድም በመጠቀም፤ ይዘቷንና ቅርጿን ለመግለጽ መግቢያም አዘጋጂቸላት፤ ከዚህ ቀደም ካቀረብኩባት መንገድ ለየት በማድረግ በትንሽ መጽሐፍ መልክ  አቅርቢያታለሁ። በመቅድሟ ልጀምር። መቅድም ከኛ በፊት የነበሩት ሊቃውንት ኢትዮጵያን የጠበቁባቸውን መስተጻምራት  በቃልም በተግባርም ባለማሳየታችን፤ ይልቁንም የግል ክብርና  ድሎት አሳዳጆች ሆነን በመታየታችን፤  በኛ በዘመኑ ቄሶች ድካም፤ የቀደሙ ሊቃውንት ቀሳውስት አባቶቻችንና ቤተ ክርስቲያናችን ባዲሱ ትውልድ ሲነቀፉና
Posted in Ethiopian News

አብይ እህመድ እስክንድር ነጋ ላይ “ግልጽ ወደ ሆነ ጦርነት ውስጥ እንገባለን” ያለው ዛቻ ሊተገብረው እንደሆነ ውስጥ አወቆች አጋለጡ

ህወሃት ጉያ ውስጥ የክፋትና የመሰሪነት ጡጦ ሲጠባ ያደገው አብይ አህመድ በህዝባዊ አመጽና ለረዥም ዓመታት በተደረገ ሰላማዊ ትግል የሥልጣን ማማ ላይ ከተፈናጠጠ በኋላ በአፈ ጮሌነትና በማጭበርበር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን እንዳደነዘዘና እንዳፈዘዘ ይታወቃል። ብዙ ሽህ ቁጥር ያለውን የፌዴራል መንግስትን ጦር ሰራዊት፣ ታንኩን፣ የጦሩን አውሮፕላኑና መድፉን በእጁ ቢያስገባም የህወሃትን ወንጀለኞች እንደ ጌታቸው አሰፋ አይነቶቹን ለፍርድ ለማቅረብ ወኔው የከዳውና የተልፈሰፈሰው አብይ አህመድ በሰላማዊ መንገድ የህዝብን ጥያቄ አንስቶ የተገፋውንና የተረገጠውን የአዲስ አባባ ህዝብ ብሶት በማሰማቱ ምክንያት ከአስኪሪቢቶና ወረቀት ሌላ ምንም የሌለውንና በሰላማዊ ትግልና በጋዜጠኛነቱ ዓለም የተመሰከረለትን እስክንድር ነጋን የወገንቡ ቅማል ሆኖበት አላስቀምጥ አላስቆም ብሎት እንደ አህያ እንዲያናፋ አስገድዶታል። እስክንድር ነጋ ለበርካታ ዓመታት ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለአንድነት መስፈን በህወሃት እስር ቤት ሲሰቃይ በነበረበት ጊዜ አብይ አህመድ የህወሃትን ሹመት ተቀብሎ የስለላ መስሪያ ቤት በመምራት ንጹሃንን እየሰለለ ለመከራ አሳልፎ ይሰጣቸው እንደነበር እራሱም ቢሆን የሚክደው ሃቅ አይደለም። በነዚያ የአፈናና የስቃይ ዓመታት እስክንድር ነጋ ህጻን ልጁንና ባለቤቱን ለመከራ አጋልጦ እሱ እስር ቤት ውስጥ እድሜውን አጋምሶታል። አብይ አህመድ ይሉኝታ የሌለውና በጭብጨባ ብዛት ናላውን የሳተ በመሆኑ ነው እንጅ እስክንድር ነጋ ላይ አፉን የሚከፍትበት የሞራልም ሆነ የግብረገብ ብቃት የለውም። አብይ አህመድ ሰኔ 16, 2010 አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በደረሰበት የግድያ ሙከራ የህይወት መስዋዕትነት የከፈለለትንና አሁን ለመጣው ለውጥ ለብዙ ዓመታት  ምርጫ 97ን ጭምር ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነትን የከፈለውን የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ክህደት ፈጽሟል። የአዲስ
Posted in Ethiopian News

በእስክንድር ነጋ ላይ እየደረሰ ያለው አፈና የአብይ አህመድን አገዛዝ እውነተኛ ማንነት ያሳያል ተባለ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለት ጊዜ የእስክንድር ነጋ የጋዜጣ መግለጫ መርኃ ግብር በፖሊስ እንዲበተን ተደርጓል፣ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በገዥዎች ፍላጎት የሚሰጥና የሚከለከል እንጅ የዜጎች መብት አለመሆኑ አየታየ ነው፣ አሁንም በሥልጣን ላይ ያሉት የሚፈልጉት አጨብጫቢዎችንና አሽቃባጮችን መሆኑ እየተረጋገጠ ነው፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ማሕበር አቋቁመው በከተማዋ ውስጥ አለን የሚሉትን መብት ለማስከበር በነጻነት ሲንቀሳቀሱ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ስብስብ ግን በጠላትነት ተፈርጆ እንዳይነቀሳቀስ የተለያዩ አፈናዎችና ጋሬጣዎች ተደቅነውበታል፣ በእስክንድር ነጋ ላይ እየደረሰ ያለው አፈና ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ምርጫ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ እንደማይካሄድና ከገዥዎች ያለወገነ አስተሳሰብ እንደሚጨፈለቅ አመልካች ነው፣ ጋዜጠኛ አበበ በለው በዚህ ጉዳይ ላይ ያቀረበውን ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ውይይት ተከታተሉ።
Posted in Ethiopian News

ከመበላት ለማያመልጥ በግ መጠበቅ ምን ይጠቅመዋል?  በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ከመበላት ለማያመልጥ በግ መጠበቅ ምን ይጠቅመዋል? ምንት ውእቱ ረባሁ ለበግዕ ዘይትዐቀብ ይህች ጦማር ለኢትዮጵያውያን ትድረስ ከ40 ዘመን በውጭ ቆይታየ በኋላ ወደ ውድ አገራችን ኢትዮጵያ ሄጄ ከታህሳስ 13 እስከ ሚያዝያ 25 ቀን ድረስ ቆየሁ። 4 ወራት ከ12 ቀናት ማለት ነው።  የተማርኩባቸውን በገጠር ያሉትን አድባራትና ገዳማት ለማየት ከተለየሁባቸው ጥቂት ቀናት በቀር፤ ብዙውን ጊዜ ካሳለፍኩባቸው ቦታወች አንዷ የነእስክንድር ነጋ ቢሮ ናት። የአዲስ አበባ ወጣቶች የሚገቡባትና የሚወጡባት ያች ቢሮ ስለ ኢትዮጵያና በውስጧ ስለሚኖሩ ዜጎች ብቻ የሚወያዩባት፤ ብር የማይቆጥሩባት፤  በህይወት ያሉና የሌሉ የጀግኖች አበው ስንክሳር በተግባር የሚያነቡባት፤  የእርስ በርስ ፍቅር የሚመነጭባት  በከተማ ያለች ገዳም ናት። አራት ኪሎ ላይ ባለችው በዚህች ገዳም፣ የገደሙ ወጣቶችም ባለቤቱ ቢፈልግ አርዶ በሚበላው፤ ወይም ባለቤቱ ለሌላ በላተኛ በሚሸጠው በግ  የሚገለጹ ናቸው። ከነሱ ጋራ ተቀምጨ የሚናበቡትን በሰማሁባት ቅጽበት ሁሉ፤  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባት ሆይ የሰማይና የምድር ጌታ ይህንን ከጥበበኞችና ካስተዋዮች ሰውረህ ለሕጻናት ስለ ገለጽክላቸው አመሰግንሀለሁ”(ማቴ 11።25)ብሎ በአንክሮ ያቀረባት ምስግና ትዝ ትለኝ ነበር። በየአድባራቱ ካሉት ሁሉ ሰዎች ይህችን ጥበብ ሰውረህ፤ በዚህች ቢሮ ለሚሰበሰቡት ወጣቶች ይህችን ጥበብ የገለጽክላቸው አምላክ ተመስገን እል ነበር። ካስተዋዮቾ ከጥበበኞች ተሰውራ ለህጻናት የተገለጸችው ይህች ጥበብ  ምን ትሆን?ምናልባትም ደመወዝ የምንጠይቅባቸው ቅዳሴ ማህሌትና ስብከት የሚመስለን እንኖር ይሆናል።  “በብዙ መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል“(የሐ 14፡22  )እያሉ  ሐዋርያት ደጋግመው የተናገሩት፤ ለህዝብ ደህነት ሲባል እነ እስክንድር እንደሚያርጉት ከገዥወች ጋራ በእምነትና በቆራጥነት የሚደረገውን ትግል
Posted in Ethiopian News

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ምንት ውእቱ ረባሁ ለበግዕ ዘይትዐቀብ ከመበላት ለማያመልጥ በግ መጠበቅ ምን ይጠቅመዋል?   ይህች ጦማር ለኢትዮጵያውያን ትድረስ   ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ [email protected] ግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ/ም   ከ40 ዘመን በውጭ ቆይታየ በኋላ ወደ ውድ አገራችን ኢትዮጵያ ሄጄ ከታህሳስ 13 እስከ ሚያዝያ 25 ቀን ድረስ ቆየሁ። 4 ወራት ከ12 ቀናት ማለት ነው።  የተማርኩባቸውን በገጠር ያሉትን አድባራትና ገዳማት ለማየት ከተለየሁባቸው ጥቂት ቀናት በቀር፤ ብዙውን ጊዜ ካሳለፍኩባቸው ቦታወች አንዷ የነእስክንድር ነጋ ቢሮ ናት።   የአዲስ አበባ ወጣቶች የሚገቡባትና የሚወጡባት ያች ቢሮ ስለ ኢትዮጵያና በውስጧ ስለሚኖሩ ዜጎች ብቻ የሚወያዩባት፤ ብር የማይቆጥሩባት፤  በህይወት ያሉና የሌሉ የጀግኖች አበው ስንክሳር በተግባር የሚያነቡባት፤  የእርስ በርስ ፍቅር የሚመነጭባት  በከተማ ያለች ገዳም ናት። አራት ኪሎ ላይ ባለችው በዚህች ገዳም፣ የገደሙ ወጣቶችም ባለቤቱ ቢፈልግ አርዶ በሚበላው፤ ወይም ባለቤቱ ለሌላ በላተኛ በሚሸጠው በግ  የሚገለጹ ናቸው።   ከነሱ ጋራ ተቀምጨ የሚናበቡትን በሰማሁባት ቅጽበት ሁሉ፤  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “አባት ሆይ የሰማይና የምድር ጌታ ይህንን ከጥበበኞችና ካስተዋዮች ሰውረህ ለሕጻናት ስለ ገለጽክላቸው አመሰግንሀለሁ”(ማቴ 11።25)ብሎ በአንክሮ ያቀረባት ምስግና ትዝ ትለኝ ነበር። በየአድባራቱ ካሉት ሁሉ ሰዎች ይህችን ጥበብ ሰውረህ፤ በዚህች ቢሮ ለሚሰበሰቡት ወጣቶች ይህችን ጥበብ የገለጽክላቸው አምላክ ተመስገን እል ነበር።   ካስተዋዮቾ ከጥበበኞች ተሰውራ ለህጻናት የተገለጸችው ይህች ጥበብ  ምን ትሆን?ምናልባትም ደመወዝ የምንጠይቅባቸው ቅዳሴ ማህሌትና ስብከት የሚመስለን እንኖር ይሆናል።  “በብዙ መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል“(የሐ 14፡22  )እያሉ  ሐዋርያት
Posted in Ethiopian News

በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚከሰቱት የወቅቱ  አሳሳቢ ሁኔታዎች በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል የተሰጠ መግለጫ

በሀገራችን ኢትዮጵያ የክልል ልዩነትን  መሠረት ያደረጉ ግጭቶች መበራከታቸውና  በዚህ ምክንያት የሕይወት መጥፋት፣ የህዝብ ጉስቁልናና  መፈናቀል  እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ለድርጅታችን ለኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW ) በእጅጉ አሳሳቢ ሆኗል።። ላለፉት በርካታ ወራት ያለመማቋረጥ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው ክልል ተኮር  የእርስ በእርስ ጥቃት የሀገሪቱን አንድነት እየተፈታተኑት ይገኛል። ለሰሚና ለታዛቢም የሥነ ልቦናና የህሊና ጭንቀት ሆኗል። አሁን በቅርቡ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሕግ እናስከብራለን ስም ሆን ብለው በለገጣፎ ነዋሪዎቹ ላይ ቤት  በማፍረስ በሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን፣ ሕፃናትን አረጋውያንንና ሴቶችን ያለመጠጊያ ማስቀረት እጅግ የከፋ ግፍና ኢሰብአዊ ድርጊት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። ከዚህ ቀደም ሲል በሱማሌ፣ በጉራጌ፣ በጋምቤላ፣ በአማራ፣ በቤንሻጉል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች በቅርቡ በአዋሳ፣ በጌዶ እየተካሄደ  ያለው ከቤት ንብረቱ የተፈናቀለው የህዝብ 2ሚሊዮን በላይ መድረሱን ሕዝብ ለተባበሩት መንግሥታት ገልፅዋል። ይህ መፈናቀል በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በሕዝባችን ላይ የሚደርሰው እልቂትና መከራ ሥጋታችንን በጣም ከፍ አድርጎታል። ይህ ብሔር ተኮር ግጭት ሕዝቡን እርስ በእርሱ እንዲፈራራ ፣ እንዳይተማመን ከማደረጉም በላይ ሀገሪቷ ለጀመረችው ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንቅፋት ሆኗል። ስላም ሲደፈርስ ፣ ድህነት፣ በሽታ፣ ድንቁርና በሀገሪቱ ላይ ይንሰራፋል። ከማሳቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፕ  ውስጥ በረሃብ የሚሰቃዩት የጌዶ ወገኖቻችን ሁኔታ ለዚህ ዓይነተኛ ምስሌ ነው። አሁን በቅርቡ የመንግሥት ድርጅት መገለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ ከ8ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የረሃብ አደጋ ውስጥ እንደሚገኝ ይጠቁማል። በዚህ ሁሉ አለመረጋጋትና ቀውስ  የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች ሴቶች፣ ሕፅናት፣ ወጣቶችና አረጋውያን መሆናቸው በተግባር እያየነው ነው። አንድ ዓመት ያልሞላው
Posted in Ethiopian News

የአድዋ ድል በዓል ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በክብር እንግድነት በሚገኙበት ይከበራል

Posted in Ethiopian News

“የሲኖዶሱ ዕርቅ ብቻውን ችግሩን አልፈታውም…የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አሁንም አደጋ ውስጥ ነች” አባ ወልደተንሳዔ አባተ

“የሲኖዶሱ ዕርቅ ብቻውን ችግሩን አልፈታውም…የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አሁንም አደጋ ውስጥ ነች” ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደተንሳዔ አባተ እድሜና ጤና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይሁንላቸውና ማንም ያላሰበውንና ያላለመውን በፖለቲካ ውሳኔ ለሁለት የተከፈለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን (የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) አንድ ማድረጋቸውና በስደት ሲጉላሉ የነበሩትን ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ መርቆሪዎስን ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ማድረጋቸው ይታወቃል። የቤተክርስቲያኒቷ በአንድ ሲኖዶስ ሥር መሆኗ ለቤተክርስቲያኒቷና በአጠቃላይም ለአገሪቷ አንድነት እጅግ ታላቅ ጠቀሜታ ያለው ነው። ላለፉት 27 ዓመታት በተደራጀና በዕዝ ሰንሰለት በሚመራ መዋቅር የሰው ኃይል ተመድቦለት ቤተክርስቲያኒቷ ላይ ዝርፊያ፣ የአስተዳደር በደልና የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች በሌሎች ላይ እጅግ የሚያሳዝን ግፍና በደል ሲያደርሱ ኖረዋል። ምንም እንኳን በአገሪቱ ላይ ታላላቅ ለውጦች በመካሄድ ላይ ቢሆኑም፣ በቤተክርስቲያኒቷ ላይ ለረዥም ዓመታት የተንሰራፋው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ምንም ዓይነት መሻሻል አላሳየም። እንደውም አንዳንዳ አባቶች እንደሚሉት እየተባባሰ በመሄድ ላይ ይገኛል። ለዚህም ዋናው ምክንያት ማንኛውንም ኃይማኖታዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋም ውጤታማና ትክክለኛ ሥራ እንዲሰራ የሚያደርገው በኃላፊነት ላይ የሚመደቡ ሰዎች ለሥራው ያላቸው ታማኝነትና ብቃት ነው። ሆኖም ለቤተክርስቲያኒቷ ቀናዒነትና ተጠሪነት የሌላቸው ለህዋሃት አገልጋይነትና ጆሮ ጠቢነት በቤተክርስቲያኒቷ ላይ የተሰገሰጉት አሜከላዎች እስከ አሁን ድረስ ስላልተነቀሉ የሚያደርሱት ጉዳት እንደቀጠለ ነው። በአሁኑ ጊዜ አገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያለው መንግሥት ለህዝብ የሰጠውን መብት በመጠቀም በተለይም ምዕመናን በሌብነትና በአስተዳደር ብልሹነት የተዘፈቁትንና ኃይማኖት ሳይኖራቸው ምዕመናንን እምነታቸውን እንዲጠሉና እንዲጠየፉ የሚያደርጉትን ጳጳሳት፣የደብር አስተዳዳሪዎችንና ካህናትን በወረንጦ ለቅሞ በማውጣት ቤተክርስቲያኒቷን ማጽዳት ይኖርበታል። ይህ ኃላፊነት
Posted in Ethiopian News

አቡነ ማትያስ ከዛሬ 31 ዓመት በፊት አቡነ ተክለሃይማኖትን እየተሳደቡ የሰጧቸው መግለጫዎች

ባለፈው ሳምንት ለቀንደኛው ህወሃት ለደብረጽዮን የማይገባውን አክሊል በታላቁ በዓል አክሱም ጽዮን ላይ ያጠለቁለት አቡነ ማቲያስ ማን እንደነበሩና ለሚሰሩት የክህደት ስራ ታሪካቸውን በጥቂቲም ቢሆን ለመቃኘት ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ። በደብረጽዮን የሚመራዊ ህወሃት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ደበኛ ጠላቷ ስለሆነ ከደደቢት በረሃ ከተነሳበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ  ከ40 ዓመታት በላይ እየተናነቃት፣ እየገዘገዛትና እያዳከማት ይገኛል። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ለደብረ ጽዮን አክሊል መድፋት ማለት የይሁዳዊያን ጸሎት ቤት ለሂትለር ክብር ሰጠች እንደማለት ሊታሰብና ሊደረግ የማይቻል ፌዝ ነው።
Posted in Ethiopian News

የአማራ ክልል የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የልዑካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝት ያደርጋል

በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ የአማራ ክልል የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የልዑካን ቡድን በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር ለመወያያት ሕዝባዊ ስብሰባ ያደርጋል። ቀን፤ ዕሁድ፣ ዲሴምበር 2 ቀን 2018 ሰዓት፤ 1:30 pm ቦታ፤ Hilton Mark Center 5000 Seminary Road Alexandria, VA 22311  
Posted in Ethiopian News

“ይህንን ጉድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምን ብዬ እነግረዋለሁ”

ከላይ የተመለከተዉ የጠቅላይ ሚኒስትር የዶ/ር አብይ አህመድ አባባል በወያኔ  ፋሽስቶች የተሰራዉን ወንጀልና ሌብነት ደፍረዉ እንዳለ ለማቅረብ መቸገራቸዉን የሚያሳይ የጭንቀት  አባባል ነበር ። ጥፍር የነቀሉት፤ የወንድና የሴት ብልት ላይ በአስነዋሪ ሁኔታ የቀለዱት፤ ዜጋን አካለ ጎደሎ ያደረጉት፤የገደሉት፤ ያሳደዱት፤ልጅን ገድለዉ እናትን እሬሳዉ ላይ ያስቀመጡት፤ወጣት ዜጋን ገድለዉ አንበሳ እንደገደሉ ሁሉ አጠገቡ በፎርም ተመቻችተዉ ከአስከሬኑ ጋር ሳይቀፋቸዉ  ፎቶ ስለሚነሱት ፋሺስቶች ሳይሸማቀቁ ገለጻ መስጠት በእነሱ ሞራል ልክ መዉረድን ይጠይቃል። የሰዎቹ ዘረፋ መጀመሪያ ማስረጃ  የሚሰባሰብበት ሳይሆን እነሱ ተሰብስበዉ ቃልቲ ወርደዉ ማስረጃዉ ሳይደለዝ፤ ሳይፋቅ ሳይጠፋ፤ የዘረፉት ንብረት ባለቤትነቱ  ሳይተላለፍ፤ሀገር ቤት ያለዉ  ገንዘብ በትስስራቸዉ ከሀገር ሳይለቅ፤ሳይታጠብ (money laundry)  ምርመራዉ እንዲደረግ ያሳሰበን ዜጎች አመላክተን ነበር። በመሰረቱ አንድ ትግሬ ብድግ ብሎ ባለ ምናምን ሚሊዮን ብር ቤት ህንጻ ሰራ ሲባል የንግድ ድርጅት ሲያቋቁም ማስረጃ ስላልተገኘ  አትጠየቅም ማለት ትንሽ ፈገግ ያሰኛል። ስድስት ወር እንደ ህወአት በሌብነት  ለተካነ ድርጅት መረጃን ለማጥፋት  ከሚያስፈልገዉ ጊዜ በላይ በመሆኑ ሀገር ተሻግሮ የወጣ የሀገርን ሀብት ማስመለሱ የማይታሰብ ይሆናል።  ለዚህም ነበር ወንጀለኞቹ ቢሊየነሮች ደፍረዉ ገንዘብ የለንም መንግሰት ጠበቃ ያቁምልን ብለዉ ያሾፉት? ወገኖች በስልጣን ላይ የሚገኝ ዜጋ በከፍተኛ የሞራል ልእልና ላይ መገኘት ያስፈልገዋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር መጥቀስ ያስፈልጋል። ታላቋ ብሪታንያ በነበርኩበት ጊዜ  ጀፈሪ ሮቢንሰን  የተባሉ ባለሀብት በጠ/ሚኒስቴር ቶኒ ብሌር በጅሮንድ ሁነዉ ተሹመዉ ነበር። እኝህ ባለሀብት ፒተር ማንድልሰን ለተባለ የካቢኔ አባል  የመንግስትን ሳይሆን የራሳቸዉን ገንዘብ አበድረዉት ፒተር ማንድልሰን መኖሪያ ቤት ይገዛል።
Posted in Ethiopian News

እርቅን ማውረድ የጠንካሮች ፤ እርቅን ማጨናገፍ የደካሞች ባህርይ ነው!

እርቅን ማውረድ የጠንካሮች ፤ እርቅን ማጨናገፍ የደካሞች ባህርይ ነው! እርቅ ሲርቅ ፤ ቀልብ ይሰርቅ በግልጽ እንደሚታወቀው በዋሽንግተን ዲሲ የርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ውስጥ የዛሬ ሶስት አመት የተቀሰቀሰው ግጭትና ያስከተለው የርስበርስ ያለመግባባት ችግር እጅግ የሚያሳዝንና  ቤተክርስቲያናችንንና መላው ምእመናንን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈለና እያስከፈለ ያለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን መፍትሄው ከሰማይ እርቆ ሳይሆን ቅንነተ በመጥፋቱ ብቻ እየቀጠለ ያለ በእጅጉ የሚያስቆጭ ድርጊት ሆኖ ይገኛል። ይሁንና ዛሬም እንደትናንቱ የችግሩን መንሰኤ አንስቶ ጉንጭ አልፋ ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት የዚህ ጽሁፍ አላማ አለመሆኑን አስቀድመን ለመግለጽ እንወዳለን። አሁን ይህን ጉዳይ በዚህ ስዓት ማንሳትና መመለስ የምንፈልገው ለምንድነው ቢባል የተፈጠረውን አለምግባባት እስከዛሬ በእርቅና በውይይት መፍታት ያልተቻለው ለምንድን ነው የሚለው አብይ ጥያቄ መልስ ማግኘት ስላለበት ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ይረዳ ዘንድ ከዚህ በፊት ጥቂት የተሞከሩና ጨንግፈው የቀሩ የእርቅ ሂደቶችን እንጠቃቅስና ዛሬ የምንገኝበትን ታሪካዊ ሁኔታ እንቃኛለን። የመጀመሪያው እርቅ መፍረስ: የቤተክርስቲያናችን ችግር ከሰባት አመት በላይ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ቆይቶ የዛሬ ሶስት አመት ፈንድቶ ያን የመሰለ አሳፋሪ ጉዳይ ሲከሰት ብዙ ሰዎችን በማሳዘኑና አልፎም በማስጨነቁ ችግሩ የተፈጠረ ሰሞን የተለያዩ ወገኖቻችን ችግሩ ሳይባባስ በእንጭጩ ለመቅጨት ይቻል ዘንድ የማስታረቅ ሙከራ ለማድረግ ላይ ታች ቢሉም የትም ሊደርስ ሳይችል ሲቅር በስተመጨረሻ ሁሉም ተቆርቋሪዎች በአንድነት ጠንከር ብለው የጅመሩት የማስታረቅ ጅምር እራሳቸው አስታራቂዎቹ እርስ በርሳቸው መግባባት ባለመቻላቸውና እነርሱን የሚሸመግል ሌላ አስታራቂ በመጥፋቱ የእርቁ ጥረት ተጭናገፈፎ በጅምር ቀረ:: ትንሽ ሰነባብቶ እንደሰማነው የችግሩ
Posted in Ethiopian News

የኢህአዴግ 11ኛ ጉባኤ ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀ መንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ሊቀ መንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ

በዛሬው ዕለት በተደረገው ምርጫ ዶ/ር አብይ አህመድ ያለተወዳዳሪ የሊቀመንበርነቱንና የጠቅላይ ሚኒስርነቱን ቦታ አሸንፈዋል። አቶ ደመቀ መኮንን በምክትል ሊቀመንበርነት እንዳይመረጡ ህወሃት የሸረበው ሴራ ከሽፏል። ይህም የሆነው ወ/ሮ ሙፍሪያት ከማል እራሳቸውን ከውድድር በማውጣታቸው ነው። በዚህም መሠረት አቶ ደመቀ መኮንን ከ178 ድምፅ 149 በማግኘት ምክትል ሊቀመንበርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲመረጡ ከሳቸው ጋር የተወዳደሩት ዶ/ር ደብረጽዮን ደግሞ 15 ድምፅ ብቻ አግኝተው ተሸንፈዋል።
Posted in Ethiopian News

“ቀንድ እንጅ ጅራት አትሁን” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ ትምህርት

“ቀንድ እንጅ ጅራት አትሁን” በ2011 ዓ.ም. የደመራ በዓል ላይ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ ትምህርት
Posted in Ethiopian News

“ደመራ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

የደመራን በዓል የምናከብረው እሌኒ ዕጣን ደምራ መስቀሉን ፈልጋ ያገኘችበት መታሰቢያ እየተባለ ከመስማት ባሻገር ወደ ከሀገራችን ተሻግሮ ከታሪክና ከባህል ጋራ ተደምሮ የሚከበርበትን ጥልቅ ምክንያት ሰምተነው በማናውቀው መንገድ በመጀመሪያ የሰማነው ከአራት አመታት ወዲህ ከከንሳስ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ነው። ለአራት አመታት በተከታታይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ውለታ እንድናይ በማድረጋችሁ የከንሳስ መድኃኔዓለም ምእመናን እንኳን ደሳላችሁ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን፤  ያብነት ትምህርት ቤትና  መምህራን ውለታቸውንና ጥረታቸውን  እንድናይ የረዳን ፈጣሪ ክብር ምስጋና ይገባዋል። “ከኦርቶዶክስ ውጭ ኢትዮጵያ የለችም” እያሉ  ለዛሪይቱ ኢትዮጵያ እንደመርን መርሆ አድርገው ለመመራት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓቢይን  ያዘጋጀ  ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን። ደጋግመን ያቀረብናት ደመራ የድርጅት መሪዎችና አርቲስቶች ሁሉ  እየተቀባበሉ በተለያዩ አንደበታቸው፤ ጣእመ ዝማሬና፤  ድምጻቸው  በማቅረበችን እጅግ በጣም ደስ ብሎናል። በመጨረሻ ቀን በተለያዩ ሙያ የበለጸጉት ሊቃውንት መስከረም ስምንት በዒምባሲው አዳራሽ በተደረገው ጉባዔ ላይ መነጋገሪያ ሆና መቅረቧ  ሌላ ተአምር ሆኖብናል፤ በያመቱ  ደጋግመን በጦማርና በቃል  ለህዝብ ላቀረብነው  ሆና ዘንድሮ በኤምባሲው አዳራሽ መደምደሚያ ሆና የቀረበችውን ጥናታዊ ሰንድ ከዚህ በታች አቀረብንላችሁ። ************************************************************************ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤማባሲ ኣዳራሽ  ስለኢትዮጵያ፤ የውዪዪትና፤ መፍትሔ፤ መድረክ በተደረገው ኮንፈረንስ  ደመራ በምንላት  ኃይለ ቃል  የጥንት  ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የኢትዮጵያን ኅብረተ ሰብ እንዴት ይገልጹት ነበር? በሚል መስከረም ስምንት ለጥናት የቀረበ። በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ” በማለት  ጀምረው በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያለውን ኅብረተ-ሰባዊ-ትድምርት በአራት አዕማድ፤ በዘጠኝ መራኁተ– ኃይላተ– ቃላት ይተነትኑታል።  
Posted in Ethiopian News

“የኢትዮጵያ ታሪክ ትናንትናና ዛሬ” አጭር ጥናታዊ ቪዲዮ

የኢትዮጵያ ጀግኖች የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት ለማስከበር የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚያሳይ ጥናታዊ ቪዲዮ አቅርበንላችኋል። ቪዲዮው  በኢትዮጵያ የቅርብ ታሪክ ውስጥ የምድር ጦር (እግረኛ)፣ የባሕር ኃይልና የአየር ኃይል የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያበረከቱትን አስተዋጽኦዎች አጠር ባለ ሁኔታ ያሳያል። ቪዲዮው በተለይም ለመካከለኛና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ ትምህርት በዋቤነት ሊቀርብ የሚችልና የተሟላ መረጃዎችን አካቶ የያዘ ነው። ቪዲዮውን ያዘጋጀው ወጣት አማኑኤል ገበየሁ ሲሆን በአሁን ጊዜ ጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲ ውስጥ በኮምፒውተር ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዓመት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ይገኛል። ስለ ቪዲዮው ያለዎትን አስተያየት ለመስጠት በዚህ ኢሜል ይላኩለት። [email protected]  
Posted in Ethiopian News

“ፍልሰታ፣ እኛም ማየት አለብን” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ክቡር ጠቅላይ ምኒስቴር ዓቢይ አህመድ “ከኦርቶዶክስ ውጭ ኢትዮጵያ የለችም” እንዳሉት፤ ቀሲስ አስተርአየም በኢትዮጵያ ውስጥ ኦርቶዶክስን፤ በኦርቶዶክስ ውስጥ ኢትዮጵያን ሳያሳዩ የጻፏቸው ጦማሮች የለም። በዚህ ጥረታቸው ኢትዮጵያ እንዳትረሳ ሲያደርጉ። ቤተ ክርስቲያናቸው ለኢትዮጵያ ያደረገችውን ጥረት ለማሳየት ሞ ክረዋል። ከጻፏቸው ብዙ ጦማሮች አንዱ “እኛም ማየት አለብን” በሚል ርእስ ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት ነሀሴ 2003 ዓ.ም. ያቀረቧት ናት። በፍልሰታ ጾም የምትዘራው ትንሿ የጤፍ ፍሬ ተዘርታ ፈርሳ በስብሳ በቅላ አፍርታ እንደገና በዝታ ታጭዳ ተወቅታ በውስጧ የተሸከመችውን ሕይወት ሁሉ ውጣ ውረድ አልፋ፤ እሷነቷን ለሚቀጥለው ዘሯ ለማቀበል በምታልፍበት አንጻር፥ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የፍልሰታ ሰሞን ከናቶቻችን ማሕጸን ከወጣንባት ደቂቃ ጀምሮ እንደ ጤፏ ቅንጣት እየወደቅን እየተነሳን አድገን፥ እኛነታችንን ለሚቀጥለው ዘሮቻችን ለማቀበል በዚህ ምድር ላይ መዘራታችንን የምንመረምርበት የጥሞና ወቅታችን ናት:: ሐዋርያት “እኛም ማየት አለብን” ብለው የፍልሰታን ጾም እንደጾሙ እኛም መንፈሳችን ከሥጋዊ ስሜትና ፍላጎት ገተን፤ ያጣነውን እኛነታችንን ፈልገን ለማግኘት ይህች የፍልሰታ ሰሞን የምንጥርባት ወቅት ናት:: የጥንት ኢትዮጵያዊያን በጤፏ ቅንጣት ምሳሌነት በፍልሰታ ሱባዔ ለህጻናቱ የሚስተምሩትን የሕይወት ምሥጢር በዓለም ዙሪያ የተበተነው ሁሉ ወጣት ረስቶ Fast Food Nation ሆኖ እንዳይቀር፥ እንደ ጤፏ ቅንጣት የመበተኑ፥ የመዘራቱ፥ የመታጨዱና የመወቃቱ መከር አልፎ የመሰብሰቡ ወቅት አሁን እንደሆነ የማስተማርና የማስጨበጥ አቅሙና ችሎታው የሚፈቅደለት ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኀላፊነት አለበት:: በማለት ከሰባት አመት በፊት ያቀረቧትን ጦማር ወቅቱ ስለሆነ አቀረብንላችሁ። እኛም ማየት አለብን የመንፈስና የሞራል መምሕርነታቸውንና ምሳሌነታቸውን እየገለጹ በኅብረተ ሰቡ መካከል የሚኖሩ አያቶችና ቅድመ አያቶች
Posted in Ethiopian News

“ደምረነ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ደምረነ” “እንደመር” በሚል መርሆ ኢትዮጵያን በመምራት ላይ ያለው የዶክተር ዓቢይ አህመድ መንግሥት አማካይነት፤  በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል በተፈጸመው እርቅ አምላክን ለማመስገን  ሐምሌ 29 ቀን 2010 ዓ/ ም በዋሸንግተን ዲሲ ለተደረገው ጉባኤ የቀረበ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አምልኮት ክብር ውዳሴና ስግደት የባህርዩ ለሆነው አንድ አምላክ አብ ወልድ ለመንፈስ ቅዱስ “አብጽሀነ ለዛቲ ሰአት” እያለን ምስጋና እናቀርባለን። ዛሬ በዚህ ቦታ የተሰበሰብነው ያለፍንበትን የመከራ ዘመን እንዴት እንደጀመርነውና እንዳቋረጥነው በመቃኘት ለአምላካችን ካቀረብነው ምስጋና ቀጥለን፤  በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያችን ጉዳይ ሁሉ በሀሳብ በቃል በጽሁፍ በተግባር የተሳተፉትንም ሁሉ እያመሰገን፤ እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ስርአት፤  የጠቅላይ ቤተ ክህነት የዜና ቤተ ክርስቲያን ዋና አዘጋጅ በመጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሂ ቅኔ የተደመደመውን ሁሉ ስነ ጽሁፍ ባጭሩ ለመቃኘትም ጭምር ነው። በሩቅና በቅርብ ሆናችሁ የምትሰሙኝ፦ ብጹአን አባቶች ካህናት አበው ወንድሞቼ ዲያቆናት ምእመናን ወገኖቼ ዛሬ ይህችን መልእክት ይዥ በፊታችሁ ስቀርብ ደስታየ ፍጽም ነው። የዘመናችን ሊቃውንት ይህን የመሳሰሉትን ህዝባውያን ክስተቶች ለመቃኘት የሚያስችሉ Prologue እና Epilogue የሚሏቸው ዘዴዎች አሏቸው። Prologue መሰረታዊ ይዘታቸውን የሚቃኝ ሲሆን። Epilogue መደምደሚያውን የሚቃኝ ነው። “ይወድስከ አፈ ነኪር ወአኮ አፈ ዚአከ” እንደተባለው፦ በዚህ ቅኝታችን በቤተ ክርስቲያናችን የተፈጸመውን መነሻ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ታሪከውነትና ያበረከተችውን ሁሉም እየተናገረው ነውና እዚያ ውስጥ አልገባም። ዛሬ ከፊታችሁ የቆምኩት ለዚህ ያበቃንን አምላክን በማስቀደም፤ ከቅድስት አገራችን ውጭ ያለነውን  ሀሳብና ቃል እያፈለቁ  እንድናፈልቅ፤ እየጻፉ እንድንጽፍ፤  ያደረጉንን የአቡጊዳ፤ የኢትዮሚዲያ፤   የቋጠሮ፤ የአባይሚዲያ፤ 
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ ቀድሞ መንበራቸው እንዲመለሱ ሲኖዶሶቹ እንዲዋሀዱ ተወሰነ።

በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ድርድር ዓላማውን በማሳካት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወደ ቀድሞው መንበራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ እንዳስተላለፈ ተገልጾልናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውና በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ ከአሁን በኋላ አንድ ውህድ ሲኖዶስ ሆነው መቀላቀላቸው ተጠቁሟል።በስብሰባው ላይ የነበሩ በሙሉ በጋራ በአንድ ድምፅ ውሳኔውን በጭብጨባ ደግፈውታል ። ይህ ታላቅ ዜና ከሁለት ሽህ ዓመታት በላይ ላስቆጠረችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አማኞችና በአጠቃላይም ለኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ አስደሳች ዜና ነው። ይህ ስምምነት ሊገኝ የቻለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባደረጉት ጠንካራ ጥረትና ድጋፍና እንደሆነ የሚታወቅ ነው። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን ።
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰበር ዜና፤ በሁለቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶሶች መካከል የሚካሄደው የዕርቀ፟ ሳላም መክፈቻ የጸሎት ዛሬ ተካሄደ

ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰን መረጃ መረጃ መሠረት በዛሬው ዕለት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ውስጥ ከኢትዮጵያ ለእርቀ ሰላም ድርድር የመጡት የልዑካን ቡደን አባላት ጳጳሳትና ከውጭው ሲኖዶስ የተመደቡት ጳጳሳት በአንድ ላይ ጸሎት አድርሰዋል። ይህም እነዚህ ሁለት ሲኖዶሶች በውግዘት ከተለያዩ ጊዜ  አንስቶ የመጀመሪያውና ታላቅ ትርጉም ያለው መሆኑ ተገልጾልናል። ከኢትዮጵያ ሲኖዶስ የተላኩት አቡነ ቀውስጦስ፣ አቡነ ጎርጎሬዎስና አቡነ አብርሃም ሲሆኑ ከውጭው ሲኖዶስ ደግሞ አቡነ ኤሊያስና አቡነ ሚካኤል ናቸው። በጸሎቱ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ ምዕመናንና ካህናት በእልልታና በዝማሬ ጳጳሳትን  ተቀብለዋል። በሁለቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስች መካከል ስምምነት እንዲፈጠርና ቤተክርስቲያኗ በአንድ ሲኖዶስ እንድትተዳደር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውና ከኢትዮጵያ ለመጡት የልዕካን ቡድን የተሳካ ውይይት በማድረግ በውጭ ያሉ አባቶችን ወደ አገር ቤት ይዘው እንዲመለሱ መክረዋል። ድርደሩ በይፋ በነገው ዕለት እንደሚጀመር ታውቋል። ስለደርድሩ አካሄድ የምናገኘውን መረጃ በየጊዜው እንዘግባለን።      
Posted in Ethiopian News

የእንጅባራ ዮኒቨርሲቲ አስተማሪው ተሰማ ካሳው ብአዴኖችን የነገራቸው ትንታግ መልክት

ሊደመጥ የሚገባው በአማራ ላይ በህወሃት የደረሰውን እሮሮና ብሶት በትክክል ቅልብጭ ባሉ ዓረፍተነገሮች ያስቀመጠ ማብራሪያ። ተተኪው ትውልድ ከአሁን በኋላ በህወሃት እባቦቦች እየተነደፈ እንደማይኖርና የራሱን እድል በራሱ እንደሚወስን በማያወላዳ ሁኔታ አረጋግጧል። (ከፌስ ቡክ የተገኘ)  
Posted in Ethiopian News

በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኢምባሲ የመሸጉ የቀን ጅቦች የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የአሜሪካ ጉብኝት ላይ ሸፍጥ እያሴሩ ነው

በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመደረግ ላይ ያለው እሻጥር ካልቆመ በስተቀር የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጉብኝት በሌላ ጊዜ ቢደረግ ይሻላል የሚል አስተያየት በስፋት እየተሰጠ ነው ተቃዋሚውንና ለውጡ የመጣለትን ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ሊያስተናግዱ የሚችሉ “በመደመር” መንፈስ የሚያምኑ አዳዳስ ዲፕሎማቶች ዋሽንግተን ውስጥ በአስቸኳይ መመደብ ይኖርባቸዋል። የህወሃት አጀንዳ አራማጅ የኢምባሲ ዝንቦች እንደ መስፍን በዙ፣ ንጉሴ ቢራቱና አሉላ ሰለሞንን የመሳሳሉት ደላሎችን ዲያስፖራው ማየት አይፈልግም የአማራ ህዝብ እንዲወገድለት በሰልፍ ላይ የጠየቀው ስራ ላይ በማዋል ካሳ ተክለብርሃን በአስቸኳይ ከአምባሳደርነት እንዲነሳ ዲያስፖራው እያሳሰበ ነው በቅርቡ ወደ አሜሪካ በመምጣት ከኢትዮጵያዊያን ጋር ወይይት ያደርጋሉ ተብለው በታላቅ ጉጉት የሚጠበቁትን የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጉብኝት ለማደናቀፍና ለማበላሸት በህወሀት አንጋቾች  ካሳ ተክለብርሃንና ረታ ዓለሙ የሚመራው ኢምባሲ ከፍተኛ አሻጥር በመሸረብ ላይ መሆናቸውን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በወልቂጤ፣ በአርባ ምንጭ፣ በመተከል፣ በእንጅባራና ሌሎችም ከተሞች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በነቂስ አደባባይ ወጥተው ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን በመግለጻቸው እጅግ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የወደቁቱና በቅናት የደበኑት ወያኔዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ሙከራ ማድረጋቸው ይታወቃል። በውጭ የሚገኙ የህወሃት አሸርጋጆችም አገሩ ባይመቻቸውም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት አደገኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አያዳግትም። በአጭር ጊዜ ውስጥ ታላላቅ ለውጦችን እያመጡ ለሚገኙት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአገሪቱ ማዕዘናት የሚኘው ህዝብ ድጋፉን እንዳይሰጥ የተለያየ መሰናክሎችን በመፍጠር ላይ የሚገኙት ወያኔዎች አስቀድመው በየኢምባሲው ውስጥ በሰገሰጓቸው ካድሬዎቻቸው አማካይነት ህዝብ ላይ የሚሰሩትን ወንጀል አሁንም ቀጥለውበታል። ወያኔዎች ህዝብ ያስተላለፈው “በቃችሁ ተውን”
Posted in Ethiopian News

ቆራጡና ጽኑው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ታላቅ የምስጋና ዝግጅት ተካሄደለት

ከህወሃት የሚደርሰበት እስር፣ሰቆቃና መከራ ሳይበግረው ለኢትዮጵያ ህዝብ የገባውን ቃል አክብሮ በጽናት፣በትጋትና በቁርጠኝነት የጋዜጠኝነት ሙያውን በመወጣቱ ምክንያት ለበርካታ ዓመታት በእስር ሲሰቃይ የነበረውና በቅርቡ የተለቀቀው እስክንደር ነጋን የማመስገኛ ዝግጅት በዛሬው ዕለት አሌክሳንደሪያ፣ ቨርጂኒያ ውስጥ ተካሄዷል። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊን ከመሳተፋቸውም በላይ ዝግጅቱ የተካሄደበት አዳራሽ ከአፍ እስከገድፉ በመሙላቱ ሳይሳተፉ የተመለሱም በርካቶች ናቸው።ዝግጅቱ እጅግ ያማረና የሰመረ እንዲሁም የሞቀና የደመቀ ነበር።ከዚህም በተጨማሪ የአሌክሳንደሪያ ከተማ ከንቲባና የጋዜጠኞች መብት አስከባሪ ድርጅቶች ተወካዮችም ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። ስለዝግጅቱ የተጠናቀረ ዝርዝር ዘገባ እናስከትላለን።  
Posted in Ethiopian News

አሳዛኝ ዜና!! የእውቁ ወልቃይቴ ቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ ተገደለ

ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. (June 1, 2018) ለውጥ በየት በኩል እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም?! ዐማራ አሁን ባለችውና የቲፎዞ ፖለቲካው እንድትቀጥል በሚፈልጋት ኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ የለውም። እቅጩን ስንነጋገር ይህን ይመስላል። አሳዛኝ ዜና!! የእውቁ ወልቃይቴ ቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጅ በትግሬዎች ተገደለ፡፡ ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. (June 1, 2018) ሳንጃሙሴ ባንብ ላይ አቶ ግዛቸው አዳነ በወያኔ ቅጥረኞችና በትግራይ ልዮ ሀይል አባላት በተከፈተበት ተኩስ በ9 ጥይት ተደብድቦ ተገድሏል፡፡ የጀግናው የወልቃይት አስተዳዳሪ የቢተወደድ አዳነ መኮነን ልጂ በወልቃይት ጉዳይ እየተንቀሳቀሰ ይገኝ ነበር፡፡ ታላላቅ ሰዎችን በመግደል የወልቃይት ጉዳይን እናዳፍናለን ብለው ከላይ ታች እየባዘኑ ነው፡፡ ግዛቸው ወደ ጎንደር እያመራ ነበር፡፡ ነብስህን ይማር!! አንድ በአንድ ከማለቃችን በፊት በዐማራዊ አንድነት እንቁም! ማስታወሻ፤ ዘወትር የሞት ዜና አታብስሩን ለምትሉን ገዳዮቻችን ገድለን ሞትን ድል እስክናደርግ ድረስ እውነቱን መዘገባችን አናቆምም! (ከፌስቡክ የተገኘ)
Posted in Ethiopian News

“ቃል ወድቀን የነበርነውን እኛን ለማንሳት እንደወረደ፣ መንፈስ ቅዱስም ሕሊናችንን ለመውቀስ ለፍርድ ወረደ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ወቅቱን አስመልክተው በንሳስ ደብረ ሳዕል መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አውደ ምህረት ላይ ለምዕመናኑ ያቀረቡት ትምህርት ሁሉም ቢሰማው የየራሱን ግንዛቤና ትዝብት እንዲወስድ ይረዳል ብለን ስላመን ከዚህ በታች አቀረብንላችሁ።  
Posted in Ethiopian News

በስደት የሚገኘው ሕጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ አወጣ

በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራው ሕጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ የመምህር እንደሥራቸው አድማሴ መኮንን ያለፍርድ ለ24 ዓመታት መታሰራቸውን አስመልክቶ የሰጠውን መግለጫ ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
Posted in Ethiopian News

በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል እርቅ እንዳይደረግ የሚፈልጉ ጥቅመኞች የጋረጡት ችግር፤ በቀሲስ አስተርዓየ (ቪዲዮ)

“ግርግር ለሌባ ያመቻል” እንደሚባለው ወያኔ  በደንቆሮ ዋሻ መሽጎ ከነበረበት ከ1970ዎቹ ዓመታት አንስቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን በደበኛ ጠላትነት ፈርጆ እየገዘገዛትና እያደማት ይገኛል። ወያኔ በተለይም የስልጣን ማማ ላይ ከተቆናጠጠበት ካለፉት 27 ዓመታት አንስቶ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ በተጠናከረ ሁኔታ በመዝመት መነኮሳትን ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ ውስጥ ሳይቀር በጥይት እየቆላ (ባሕታዊ ፈቃደሥላሴ በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን  ውስጥ በአባ ገብረመድህን ‘አቡነ ጳውሎስ’ ትዕዛዝ የተገደሉት) ገዳማትን እያፈረሰና እያጋየ የጥፋትና የውድመት እኩይ አላማውን ቀጥሎበታል። ከዚህም በተጨማሪም ህጋዊውን ፓትርያርክ ከመንበራቸው በጉልበት በማውረድና የአገር ቤቱን ሲኖዶስ በመቆጣጠር ለአላማው መጠቀሚያ አድርጎታል። ይህንን የተቃወሙ አባቶች በስደት ህጋዊውን ፓትርያርክ ይዘው ሲኖዶስ አቋቋመው በውጭ የሚገኘውን ህዝብ እያገለገሉ ይገኛሉ። ይህ በአገዛዙ ምክንያት የተፈጠረው መከፋፈል ለአንዳንድ ወስላቶች አመቺ ሁኔታ በመፍጠር ከተጠያቂነት እንዲያመልጡና “ለያዥ ለገራዥ” እንዲያስቸግሩ ረድቷቸዋል። ለምሳሌ በዝሙት ምክንያት ስልጣነ ክህነቱን የተገፈፈው አቶ ታደሰ ሲሳይ ተጠሪነት ያለው ሲኖዶስ ከበላዩ ስሌለ በዝሙት ተጨማልቆ ቤተክርስቲያንን እያረከሰ ይገኛል። ታደሰ ሲሳይን የመሰሉ ወንበዴዎች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ እንዴት በሲኖዶሶች መካከል የሚካሄድ እርቅን እንደሚያደናቅፉ ቀሲስ አስተርዓየ ሁኔታውን ተንትነው የሰጡትን ትምህርት አቅርበንላቸኋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በስደት ላለው ሲኖዶስ ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተላለፈ መልዕክት

እፌኑ ለክሙ ዛተ ጦማረ “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ” በአትህቶ ርእስየ እንዘ እትሜነይ “አምላክነ ከመ ይዕቀባ ለዛቲ ሃይማኖት ርትዕት ዲበ ዛቲ ኰኵሕ ዘእንበለ ኅልፈት፡ እስከ ፍጻሜሃ ለዛቲ ዓለም ከመ ተሀሉ እንዘ ትገብር  ባቲ በቃለ ጽድቅ  ዘከመ ቀኖናሃ ለቤተ ክርስቲያን  ወምክረ ተአማንያን በንባብ ርትዕት እንተ ኢኮነት ርስሕት” ይህች ጽሁፍ አድራሻዋ በውጭ ላለው ሲኖዶስ ቢሆንም፤ በቤተ ክርስቲያናችን የተጠመቀ ገለልተኛ ነኝ የሚለውንም ሁሉ ይመለከተዋልና ለሁሉም ትድረሰው። ወያኔ ኢትዮጵያን በታትኖ ለማጥፋት በዘረጋው መመሪያ መንቀሳቀስ ጀምሮ ኢትዮጵያን በተቆጣጠረበት ዘመን ዓላማው አድርጎ እስካሁ ያለው፤ በመጀመሪያ የጥቃት ተቀዳሚ ዓላመው አድርጎ የተነሳባቸውን እስካሁንም ያላረፈላቸውን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንና አማራውን ህብረተ ሰብ እንደሆነ ራሱ ወያኔ ደጋግሞ የተነገረውና እየፈጸመ ያለው ምስክር ነው። ወያኔ እየነጣጠለ ሁሉንም ተራ በተራ ለማጥቃት በዘረጋው እቅዱ፤ “ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር የሚያደርግና፤ አማራውም መጥፋት አለበት ብሎ የተነሳውን የኦሮሞውን ህብረተ ሰብ ባይነ ቁራኛ ተመልከቱት” እያለ  ከዘመተበት ከራሱ ከኦሮሞው ጉያ ቄሮወች “ኢትዮጵያውን ነን” እያሉ ብቅ ሲሉ፤ በጎንደር ያሉ አማሮችም “ኦሮሞው የሥጋየ ክፍያ ያጥንቴ ፍላጭና ደሜ ነውና ሲነካ ያመናል” ሲል የወያኔ ቀልብ ተገፈፈ። በውጭ የሚኖሩ ዜጎችም  ከሀሩርና ከቁር ጋራ እየታገሉ፤ እየታሰሩ እየተፈቱ ሳያሰልሱ የፈጸሙት ተጋድሎ ተደምሮ ፤  አቶ ለማ መገርሳን ከወያኔ ሰንሰለት አላቆ በማስፈንጠር “ኢትዮጵያ ማለት ሱስ ነው” እያሉ በመላ ኢትዮጵያውያን ፊት እንዲቆሙ አደረጋቸው። የወያኔ ጥላውም ቆዳውም ተገፈፈ። ዶ ክተር ዓቢይ መሀመድ ደግሞ “ኢትዮጵያ በረዥም ታሪኳ የደመረችን፤ ስንኖር ኢትዮጵያውያን
Posted in Ethiopian News

ወያኔ በላስ ቬጋስ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ላይ አዲስ ጥቃት ከፈተ

በዛሬው እለት በደረሰን መረጃ መሠረት ላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን በህጋዊው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደረውን ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከምዕመናን ነጥቆ ለወያኔ የማስረከብ ሂደት በስውር ሲካሄድ ቆይቶ አሁን አንድ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጾልናል። በዚህም መሠረት ሲሳይ ኪዳኔ በተባለ የወያኔ ተላላኪ አጋፋሪነትና በጥቅም በተገዛው ተሻገር ከልካይ ግብር-አበርነት የቤተክርስቲያኑንን የጎደሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት ለማሟላት በተደረገው ምርጫ ለቤተክርስቲያኑ ለበርካታ ዓመታ በተቆርቋሪነት ሲደክሙ የነበሩ ምዕመናን እንዳይመረጡ የማጥላላትና ስም የማጥፋት ዘመቻ እንደተካሄደባቸው ተገልጾልናል። የወያኔው ወሬ አቀባይ ሲሳይ ከዳኔ ከምርጫው አንድ ቀን አስቀድሞ ከተሻገር ከልካይ ጋር ባካሄደው ህግ ወጥ የቴሌኮንፍረንስ ምዕመናንን በማስፈራራት፣ የውሸት መረጃ በመስጠትና በጎሰኝነት በማሸማቀቅ ድብቅ አጀንዳውን እውን ለማድረግ አንድ እርከን ወደፊት ለመሄድ ችሏል ተብሏል። በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ እንዲያገለግሉ በምዕመናን የተመረጡት ሲሳይ ከዳኔና ተሻገር ከልካይ በመተዳዳሪያው ደንብ መሠረት ምዕመናን እንዲያገለግሏቸው የጠቆሟቸውን ተወዳዳሪዎች በገለልተኛነት የምርጫውን ሂደት ማካሄድ ሲገባቸው “እከሌን ምረጡ፣ እከሌን አትምረጡ” እያሉ ህገወጥ ቅስቀሳ በቴሌኮንፍረስ ማካሄዳቸው ተግልጾልናል። በዚህም ድርጊታቸው ከአባላት የተሰጣቸውን አደራ በመብላት የግል ፍላጎታቸው እንዲሳካ አድርገዋል።ምርጫው በገለልተኛና በነጻ አስመራጭ ኮሚቴ ስላልተካሄደና በድምፅ ቆጠራውም ላይ የማጭበርበር ድርጊት ተፈጽሞ ሊሆን ስለሚችል አዲስ ምርጫ በቤተክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ነጻና ገለለተኛ በሆኑ አዲስ አስመራጭ ኮሚቴ አባላት እንደገና መካሄድ አለበት የሚሉ ነባር ምዕመን ቁጥራቸው ቀላል እንዳልሆነ ታውቋል። የሲሳይ ኪዳኔ አላማ ብጥብጥ መፍጠርና ምዕመናን በመከፋፋልና በተለያየ ጎራ በማሰለፍ በሚፈጠረው ክፍተትና ግርግር ቤተክርስቲያኑን ለወያኔ አሳልፎ ለመስጠት ነው። ይህም የወያኔ
Posted in Ethiopian News

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ስለ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አስመልክተው በሆሳዕና በዓል ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

አርባ አመት መጀመሪያ ላይ የሚገኘው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የመጽሐፍንና የጥበብን ጥቅም ስለተረዳ ለአገሪቱ ህልውና አርበኛ ሆኖ ማገልገል ይገባዋል። ቀሲስ አስተርአየ በተለመደው አቀራረባቸው፤  የዓመቱን የሆሳዕና በዓል ዳሰው፤ በዘንድሮው ሆሳዕና በዓል ላይ ተደርቦ እያነጋገረ ያለውን በአቶ ኃይለ ማርያምና በዶክተር ዓቢይ መካከል የተፈጸመውን ቅብብሎሽ የጎሪጥ አይተው አላለፉትም። ቀሲስ ወደ ዋናው ወቅታዊው ትምህርት ከመግባታቸው በፊት ህዝቡን በሰፊው ከሚያወያዩ መንግስት ነክ ነገሮች መናገር መመስከር ፖለቲካ መግባት  ነውና ለቀሳውስት ከክህነታዊ ተልእኮ ውጭ መሆን ነውና ትክክል አይደለም የሚሉ ሰዎች ቤተ ክርስቲያናችንን ወረዋታል። ይህ አባባል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የገባ እንጅ፤ ህዝባውያን ነገሮች በቅኔያችን ሳይዳሰሱ ማለፍ ተገቢ አልነበረም።በከተማና በገጠር ከህዝብ ጋራ እየተጋፉ ልብስና ምግብ እየተሻሙ የሚሳተፉ ሰዎች ይቅርና መንነና ሞተናል ብለው ራሳቸውን ከህዝብ ለይተው በገዳም የሚኖሩ መነኮሳት፤ ከህዝብ የሚለዩት ለስጋቸው ከሚጠቅሙ ቆሳቁሶች እንጅ ህዝቡን አስጨንቀውና አንቀው ከያዙ ቢናገሯቸው በራስ ህይወት ላይ አደጋ ከሚያስከትሉ ነገሮች ራስን መደበቅ አይደለም። ብለው ከመጽሐፈ መነኮሳት የሚከተሉትን ጠቅሰዋል። ”በከመ ቀደመ መሬት እምነ ነፍስ እንተ ተነፍሀት ውስተ ገጹ ለአዳም፤ ግብር ሥጋዊ ይቀድሞ ለነፍሳዊ“(ማር 1)የሰው ቁሳዊ ሰውነቱ ከረቂቋ ነፍሱ ቀድሞ ተገኝቷል። ቀድሞ የተፈጠረው ቁሳዊ ሰውነት በሚጠይቀው ኃላፊነት ጉድለት እንዳይከሰትብህ ተጠንቀቅ። “ከመ ለሊከ ባህቲትከ ዘትሜግብ ርእሰከ ህየንቴሁ ናሁ ኮንከ ህርቱመ እምኩሉ ሰብእ”( ምዕ 5)። ብቻህን በምናኔ ብትኖርም፤ ከሰው በመለየትህ በህዝቡ ላይ ከሚደርሰው መከራ ራስህን አሽሽተህ፤ የራስህን ሰላም በመጠብቅ በገዳም ራስህን ደብቀህ የህዝቡን መከራ የማትሳተፍ ከሆንክ ከሰባዊነት ወደክ። “ቁሳዊ
Posted in Ethiopian News

“በኢትዮጵያ በህዝቦች መካከል ግጭት መፍጠር የመንግስታዊ ሽብርተኝነት ተግባር ነው!”

ወቅታዊውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ከኣፋር ነጻነት ግንባር ፓርቲና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተሰጠ የጋራ መግለጫ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የሕወሃት/ኢሕኣዴግ ስርዓት ፍጻሜው የተቃረበውን ኣገዛዙን እስትስፋስ ለማቆየት የተለያዩ ከንቱ ጥረቶችን ተያይዟል። ህዝቦች ለነጻነትና ለዲሞክራሲ እያካሄዱ ባሉት ተግል መሰረቱ የተነቀነቀውን የቡድኑን የበላይነት የማስጠበቅ ስርዓት መልሶ እንዲያንሰራራ ለማድረግ የተቻለለትን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል። በኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ከለላ የስርዓቱ የታጠቁ ሃይሎች ንጹሃን ዜጎችን መግደል፣ ኣፍነው መሰወርና ለከፋ ሰቆቃ መዳረጋቸውን ቀጥለዋል። ይህ ኣምባገነን ቡድን የህዝቦችን የትኩረት ኣቅጣጫ ሃገሪቷን እያመሰቃቀለ ካለው ቀውስ ለማስቀየርና ህዝቦችን በኣገዛዙ ላይ ያለማቋረጥ እያካሄዱት ካለው ተቃውሞና ፍልሚያ ለመግታት በማለም ለዘመናት በሰላም፣ በመከባበርና በመፈቃቀር ኣብረው በኖሩ ህዝቦች መካከል የመጠራጠርና የጥላቻ መርዝ ለመርጨት እየሰራ ነው። በዚህም የሕወሃት/ኢሕኣዴግ ቡድን በኦሮሞና በኦጋዴን-ሶማሌ ህዝቦች መካከል የፈጠረው ግጭት የኣያሌ ዜጎችን ህይወት መቅጠፉና ከሁለቱም ወገን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀዬኣቸው መፈናቀላቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ስርዓቱ ይህን መሰል ጥፋት በህዝቦች ላይ ፈጽሟል፥ ይህን እኩይ ዓላማውን ኣሁንም በመቀጠል በየዕለቱ የሰብዓዊ ወንጀል እየፈጸመ ነው። የኣፋር ነጻነት ግንባር ፓርቲና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የኢሕኣዴግ ሃይሎች እራሳቸውን በመደበቅ በምስራቅና ሰሜን-ምስራቅ የኦሮሚያና የኣፋር ክልል ኣዋሳኝ ድንበር ላይ በሰላማዊ መንገድ ኑሮኣቸውን ሲመሩ በነበሩ ሲቪሎች ላይ በሁለቱም ወገን ጥቃት ሊያደርሱ መሞከራቸውን ኣረጋግጠዋል። ይህ ሰሞኑን የተፈጸመውና በኣካባቢው ነዋሪዎች የተረጋገጠው የወያኔ/ኢሕኣዴግ ድርጊት ስርዓቱ በመላው ሃገሪቷ ስርዓቱ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ለማናቆር ሲፈጽመው የነበረው ተመሳሳይ ድራማ መሆኑ ግልጽ ነው። ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ስርዓት በሃገሪቷ
Posted in Ethiopian News

“ኒቆዲሞስ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በከንሳስ መድኃኔ ዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አውደ ምህረት ላይ በተከታታይ በሚያቀርቧቸው ትምህርቶች በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተከሰቱትን ወቅታዊ ችግሮች ሳይዳስሱና መፍትሄ ሳይጠቁሙ ያለፉበት ወቅት የለም። ባለፈው ሳምንት ሳያከስር ዋናውን ቢመልስም፣ ባለማትረፉ ብቻ ቅጣት ከደረሰበት፤ ዋናውን ባከሰርን በዚህ ዘመን ባለን ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርስብን ፍርድ ምን ያህል የከፋ እንደሚሆን አሳይተውን ነበር። በዚህ ሳምንት ደግሞ ጌታችንና መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ የገለጸውን ምሥጢረ ጥምቀት በመጠኑ ገልጸው በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተከሰቱትን ችግሮች የዳሰሱበትን ትምህርት አቅርበንላችኋል።
Posted in Ethiopian News

“ትንፋሽ የሌለው ሰው የሞተ እንደሆነ ሁሉ፣ የማትናገር ቤተክርስቲያንም የሞተች ነች” – አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ

በዋልድባ መነኮሳት ላይ በወያኔ እየደረሰባቸው ስላለው ግፍና መከራ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዝም ማለቷን አስመልክተው አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ የሰጡትን ልብ የሚመስጥ ትምህርተ ወንጌል አቅርበንላችኋል። የዋልድባ መነኮሳት ላይ በወያኔ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ ማለትም በኤሌክትሪክ መጠበሳቸው፣ ተዘቅዝቀው መገረፋቸው፣ በአንድ ልብስ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየታቸው፣መዋረዳቸውና ገዳማቸው ለፋብሪካነት መፈራረሱ በአጠቃላይ በተዋህዶ ምዕመና ላይ የተከፈጠ ጦርነት ነው። በዋልድባ ገዳም በሚገኙ ሴት መነኮሳት ላይ በትግራይ ሚሊሻዎች መደፈር እንደሚፈጸምባቸው ቢነገርም አቡነ ማቲያስና ሲኖዶሳቸው እንዲሁም የወቅቱ መምህራን ነን ባዮች ምንም አልመሰላቸውም። ድንግላዊያን፣ ገዳማዊያን፣ መናንያንና በአጠቃላይም ቤተክርስቲያኒቱ ስትጠፋና ስትዋረድ የምዕመናን በስፋት አለመቃወምና በአንድነት አለመንቀሳቀስ ይህንን ትውልድ በታሪክ ሲያስወቅስ የሚኖር ጉዳይ ነው።  አገር ቤት ያለችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስለ እስረኞች መፈታት ምንም ስትናገር አልተሰማችም በጠራራ ቀን በአደባባይ ላይ ንጹሃን በጥይት ረፍርፎ እንደ ተራ ነገር “በስህተት ነው የተገደሉት” ማለት በወያኔ ህይወት እንዴት እንደረከሰች ማረጋገጫ ሲሆን አእጅግ አስደንጋጭ የሆነ የወንጀል ድርጊት ነው። በአባ ማቲያስ የሚመራው ሲኖዶስ ከአገዛዙ የሚለየው በዓርማ እንጅ በዓላማ አይደለም። በተለያዩ የቤተክርስቲያንና የአገር ጉዳይ ላይ አዘውትረው ለምዕመናን መልዕክት የሚያስተላልፉት ታላቁ አባት ቀሲስ አስተር አየ ጽጌ የዋልድባ መነኮሳትን አስመልክተው በቅርቡ ያስተላለፉትን መልዕክት ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ አቅርበንላችኋል። መምህር ዘበነ ለማ እንደ ቀሲስ አስተርአየና አባ መዓዛ በቤተክርስቲያንና በአገር ላይ ወያኔ የሚፈጽመውን ወንጀል ማውገዝና ማጋለጥ ሲገባው “ፖለቲካ ውስጥ አልገባም” እያለ ማጭበርበሩና በዚህም ለአገዝዙ ድጋፍ መስጠቱ በተደጋጋሚ ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል። በቅርቡም የዋልድባ መነኮሳት ይፈቱ በማለት ግልጽና ጠንካራ መልዕክት
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልንሰማው የሚገባን ዓመታዊ የገብርሄር ትምህርት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

“ይህን የማይረባ አገልጋይ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት”። (ማቴ 25፡30)። ዋናውን ሳያከስር አለማትረፉ ብቻ ጥርስ ማፋጨትና ልቅሶ ወዳለበት የቅጣት ቦታ የሚከት ከሆነ ዋናውን ማክሰርማ የሚያደርሰው ቅጣት ምን ያህል የከፋ እንደሚሆን ሁላችንም እራሳችንን እንድናይበት ቀሲስ አስተርአየ በከንሳስ ደብረ ሣህል መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዓውደ ምህረትላይ ያቀረቡትን ዓመታዊ ትምህርት ቪዲዮ አቅርበንላችኋል።
Posted in Ethiopian News

የናሽቪል ቴኔሲ ደብረ ቀራንዮ መድኃኔ ዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ ንብረት “ሸጦ ለመካፈል” የሚመስል እንቅስቃሴ ተጀመረ

በሽያጩ ላይ ዋና አቀንቃኞች አቶ ሳሙኤል ልዑል ሰገድና የሱ ተባባሪዎች (አብዛኛው የወያኔ ደጋፊዎች) የቤተክርስቲያኗን 214 Welch Road ላይ የሚገኘውን ንብረት ለመሸጥ ነው። በአሁኑ ሰዓት 5 ኤከር የማያንስ መሬት ሲሆን በላዩ ላይ የሚከራዩ ቤቶችና የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን የነበረውን ጭምር ነው። (በወር  $5,000 ያህል እንደሚያገኝ ይገመታል)። ይህ ንብረት ሲከራይ የገንዘብ አሰባሰቡ ግልፅ አይደለም። ሌሎችም ችግሮች አሉ ወደፊት እንዘረዝራለን። ይህንን “ሸጦ መካፈል” የሚመስለው እንቅስቃሴ በናሽቪል የሚገኙትን የኦርቶዶክስ አማኞች በሙሉ ማነጋገር ጀምሯል።  የደብረ ቀራንዮ መድሐኒዓለም የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ስለነበረ አሁን ከቤተክርስትያኑ በተለያየ ምክንያት የወጡና ሌላም ቤተክስርስቲያን የመሰረቱ እንደ ሐማረ ኖህ ኪዳነምሕረትና ደብረ ብርሀን ቅድስት ስላሴ  ቤተክርስቲያንና ሌሎችም አኩርፈው በየቤታቸው ያሉት ሁሉ ጉዳዩን መጠየቅና ጠበቃም ማነጋገር ጀምረዋል። ምንም እንኳን የቀድሞ አባሎች ተለይተው ቢወጡም አሁን ያለው ክፍፍል አንድ በሚሆንበት ጊዜ ንብረቱ የኦርቶዶክስ አማኙ ሁሉ መገልገያ እንደሚሆን ይገመታል። ነገር ግን ንብረት ሸጦ ለጥቂት ተፅኖ ለሚያደርጉ የወያኔ ደጋፊዎች ለማስረከብ የሚሯሯጡ በመገኘታቸው ሁሉንም እያነጋገረ ነው። ዝርዝሩን ሰሞኑን ይዘን እንደምንቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።  
Posted in Ethiopian News

መምህር ዘበነ ለማ ስለዋልድባ መነኮሳት መፈታት መጮህ ትቶ አልባሌ ጉዳይ ውስጥ ገባ

ፓስተር ወዳጄነህ የተባለ ግለሰብ ጴንጤዎች እያደረጉት የመጡትን እጅግ አሳፋሪና አስደንጋጭ አምልኮ ማጋለጡና መተቸቱ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተለምዶ መናፍቃን ከሚሰነዝሩት ስድብ ወጣ ባለ መልኩ አንዳንድ ገንቢ ነጥቦችን ማንሳቱን ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ከተለቀቁ ቪዲዮዎች ለመረዳት ይቻላል። ከታዋቂ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የወቅቱ መምህራን መካከል አንዱ የሆነው መምህር ዘበነ ለማ ለፓስተር ወዳጄነህ ማበረታቻ መሰል መልእክት በፍጥነት በቪዲዮ ለቋል። ፓስተር ወዳጄነህ የኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያን አስመልቶ የሰነዘራቸው መልዕክቶች ገና ትኩስ ከመሆናቸው አኳያ መምህር ዘበነ ለማ የሰጠው ምላሽ ሌላ ታላቅ ጉዳይ ላይ ጥያቄ እንዲነሳ ምክንያት ሆኗል።ይኽውም ለረዥም ዓመታት አለወንጀላቸው ከገዳማቸው ታፍነውና ተዋርደው በእስር ስለሚማቅቁት የዋልድባ መነኮሳት እንዲፈቱ የሚጠይቅ ማንኛውም ዓይነት ቪዲዮም ሆነ የጽሁፍ መልዕክት መምህር ዘበነ አላስተላለፈም። የዋልድባ መነኮሳት ጨለማ ቤት ተቆልፎባቸው እየተደበደቡ ልብሳቸውን ሳይቀይሩ በአንድ ልብስ ብቻ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ቤት ሲሰቃዩ መምህር ዘበነ ስማቸውን እንኳ  አንስቶ የተናገረው አንዳችም ነገር የለም። ህዝብ ማወቅና እርምጃ መውሰድ ያለበት አንገብጋቢው ጉዳይ በእስር ቤት በመማቅቅ ላይ የሚገኙ መነኮሳት ወይንስ የአንድ ግለሰብ ጉዳይ። የዋልድባ መነኮሳትና መንንያን የአገርና የትወልድ ቅርስ የሆነውን ታሪካዊውን የዋልድባ ገዳም በወያኔ ለስኳር ፋብሪካነት በግሬደር ሲፈርስና ለዘመናት ተከብሮ የነበረው የመነኮሳቱ መካነ መቃብር በትራክተር ሲታረስ በመቃወማቸው ለእስር እንደተዳረጉ ይታወቃል። መምህር ዘበነና እንዲሁም የአቡነ ማቲያስ ሲኖዶስና ተከታዮቻቸው አሳራቸውን በመቁጠር ላይ ስለሚገኙት መነኮሳት ስለነአባ ገብረሥላሴ ወልደኅይማኖትና ስለነአባ ገብረየሱስ ኪዳነማርያምና ሌሎች ከእስር መፈታት መጮህ ዋጋ የሚያስከፍላቸውና ከወያኔ ጋር የዘረጉትን የጥቅም ገመድ
Posted in Ethiopian News

ኢትዮጵያውያን ሁሉ ልንሰማው የሚገባን ዓመታዊ ትምህርት፤ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ዘመናችን እንዳፈራቸው ሰባኪዎች ከድርጅት ትርፍ ከሰው ምስግና ለማግኘት የፖለቲካውን ዝንባሌ እያነበቡ፤ የህዝብ ስሜት ሲግል እየጋሉ፤ ሲበርድ እየበረዱ እንደ ጠፍ ጨረቅ በዓውደ ምህረት ላይ ብቅ የሚሉ ሰባኪ አይደሉም። እራሳቸውና ጥቅማቸው የማይናከበትን መንገድ እየመረጡ የህዝቡን ወቅታዊ ስሜት እያከኩ  በመስበክ ሴቱን እልል በሉ፤ ወንዱን አስጨበጭቡ ሲሉ ተሰምተው አያውቁም። በከንሳስ መድኃኔዓለም አውደ ምህረት ላይና፤ በሌሎችም መገናኛ መስመሮች  ያለማቋረጥ ያቀረቧቸው መልእክቶች በቤተ ክርስቲያናችን በአገራችን ላይ የሚደረገውን ግፍ እየገለጹ ህሊናውን ረስቶ ለሆዱ ተገዥ የሆነውን ሁሉ የሚገርፉ ናቸው። የሚያቀረቧቸው መልእክቶች የቀደሙ ሊቃውንት አበው ይጠሩባቸውን የነበሩትን የእውቀት የሞራልና የእምነት ስሞች ደራርበው በመሸከም ህዝብ የሚያታልሉትን አስመሳዮች  እያጋለጡ፤  የቀደሙ ሊቃውንት አበው ይለብሷቸው የነበሩትን የክብር ካባዎች ደራርበው የለበሱትን እየገፈፉ በህዝብ ፊት ራቁታቸውን የሚያቆማቸው ሁሉ የሚወረወሩባቸው ዘለፋ ሳይበግሯቸው፤ መከራን ከመከራ፤ ዘመንን ከዘምን፤ ትውልድን ከትውልድ፤ የቀደሙ ካህናትን ከዘመኑ ካህናት ጋራ እያነጻጸሩ ስለ አገራችንና ቤተ ክርስቲያንችን የታያቸውን  ገልጸው ሳይናገሩ ያለፉበት ወቅት የለም። በመከራው ዘመን በያመቱ ለሚታሰበው ደብረ ዘይትን የኢየሱስ መፈክር  ወይም ፍካሬ ኢየሱ በሚል ርእስ በጽሁፍም በቪዲዮም አቅርበዋል።  ራእይ የማያሳይና  ወደ ተግባር የማይመራ ከጾም ጋራ ተያያዞ የሚደረግ ሱባዔም ከማታልያና መስመሩን ስቶ ህዝብ ከማሳት የራቀ መሆኑን ለማሳየት  የዘንዶ ሱባዔ በማለት አቅርበውልን ነበር።  የበለጠ ማወቅ ከፈለጉ  https://ecadforum.com/Amharic/wp-content/uploads/2014/08/yezendow-subae.pdf?x46017 የሚለውን ቢጫኑ የዘንዶውን ሰባዔ ሊረዱ ይችላሉ። የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ይፈቱ ብለው እንዲጮኹ በሚያስገድደው በመንበረ ፓትርያርክ ላይ የተቀመጡት አባ ማትያስ፤ መነኮሳቱ መታሰራቸው እንዳነገር ከማፈናቸው ባሻገር፤ ገዳሙን ለመዘበረው መነኮሳቱን
Posted in Ethiopian News

የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትና አገራዊ ጉዳዮች

የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኞች በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው በአገዛዙ ካድሬዎች እየተፈፀሙ ያሉ ተግባራትና መሰል ጉዳዮች ላይ በኢሳት የተደረገ ውይይት ተከታተሉ።
Posted in Ethiopian News

በአጋዚ ሚሊሻዎች መንዲ ከተማ ውስጥ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፓስተር ተገደሉ፤ እንዲሁም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ወጣቶች በሌሊት እየታፈሱ ነው

በዛሬው ዕለት በደረሰን መረጃ መሠረት የአጋዚ ሚሊሻዎች በተለያየ የኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ወራራ በማድረግ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ወጣቶችን “የቄሮ አባላት ናችው” በማለት በራቸውን በሌሊት ሰብረው በመግባት ከመኝታቸው ላይ እርቃናቸውን አስነስተው እያዳፉና እየገፈታተሩ በጭነት መኪና ላይ እየወረውሩ አፍሰዋቸው ወደአልታወቀ ስፍራ እንደወሰዷቸው ታውቋል። የኦሮምኛ ቋንቋን አቀላጥፈው በሚናገሩና ማንነታቸውንና የህወሃት አባል መሆናቸውን ደብቀው አሮሞ መስለው፣ ኦሮሞ አክለው፣ ኦሮሞው መሃል የኖሩና ኦሮሞው አብልቶና አጠጥቶ ባሳደጋደው ጡት ነካሾች ጠቋሚነትና መንገድ መሪነት ህዝቡን በማጅራቱ እያረዱት ነው። በአማራው ክልልም ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ የህወሃት አባላት ሆነው አማራው መሀል ተሰግስገውና ተመሳስለው በመኖር የሚሰጣቸውን መመሪያ ጊዜ ይጠብቁ የነበሩ ሰላዮች በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ ደብረማርቆስ፣ ወልዲያ፣ ደሴ፣ ቆቦ ከተሞችም ውስጥ የንጹሃን ደም እንዳፈሰሱ ይታወቃል። ህዝብ በባዶ እጁ የሚያደርገውን ተጋድሎ አጠናክሮ ቀጥሎበታል። አገርን ከወያኔ ነጻ የማውጣት ህዝባዊ እንቅስቃሴና እምቢተኝተንት በዛሬው ዕለት ነጆ፣ ግምቢ፣ ጊንጪ፣ሻምቡ ከተሞችንና እንዲሁም አርሲ፣ባሌ-ሮቢ፣ ሐረር፣ በደሌ ከተሞች በመፋፋም ላይ ይገኛል። መረጃው እንዳይወጣ ለማድረግ ወያኔ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጧል። በወያኔ ቴሌቬዥን ላይ እየወጡ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ በሚገኙ ቄሮዎች፣ፋኖዎችና ዘርማዎች ላይ የሚያላግጡ ሰዎች ከዚህ አስከፊ ድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ተሰትቷቸዋል።
Posted in Ethiopian News

“የፖለቲካ መሪዎች፣ወታደሮችና ካህናት ነጋዴዎች ሆነው የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደ ጅብ በሉት” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በጾመ ሁዳዴ ውስጥ ያለውን ሶስተኛውን ሳምንት ምኩራብን አስመልክተው በአገራችን ውስጥ የመንግሥት ባላሥልጣኖች፣የወታደሮችና የካህናት በንግድ ሥራ መሰማራት በአገርና በህዝብ ጥቅም ላይ  ያስከተለውን ቀውስና መዘዝ አብራርተው ጥልቅ ይዘት ያለው ትምህርት ሰጥተዋል። ካነሷቸው አበይት ነጥቦች መካካል የሚከተሉት ይገኙበታል። “በአሁን ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ንግድን የሚያካሂደው ማነው? መንግሥት የወታደር ትርፉ ህዝብን መጠበቅ ነው።ጄኔራሉና ኮሮኔሉ ህዝብን መጠበቅ ትቶ ንግድ ውስጥ ከገባ ጥይቱ ከትርፉ ጋር የሚሄደው።ትርፉን የሚሻማውን ሁሉ መብላት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ጠቅላላ ንግዱን የያዘው ማነው? እነማናቸው ነጋዴዎች? ጄኔራሎችና ወታደሮች። ጄኔራሎች የሚነግዱት ከማን ጋር ነው፣ ከፖለቲካ ሰዎች ጋር የተቆራኘ ነገር ነው። የዘመኑ የቤተክርስቲያን መሪዎችን እዛ ውስጥ ነው የገቡት። ወታደር ነጋዴ ከሆነ ድንበር ማነው የሚጠብቀው? አገርን ማነው የሚጠብቀው? የፖለቲካ ሰው ነጋዴ ከሆነ የተራበው፣የተጠማውን የታረዘውን ወደ ራሱ ኪስ ያመጣዋል እንጅ ንግድ ፈላጊ ስለሆነ፣ ትርፍ ፈላጊ ስለሆነ በደሃው ጭንቅላት እየተረማመደ ትርፍ መሰብሰብ ነው። “እንደዚህ ዓይነት ማህበረሰብ በጅብ ተበላ”። እነዚህንና ተዛማች ጉዳዮችን የዳሰሱበትን ትምህርተ ወንጌል ሙሉ ቃል ጠቃሚነቱን ስላመንን አቅርበንላችኋል።  
Posted in Ethiopian News