አማራ እና ደቡብ ጄኔራሎች ጡረታ ሲወጡ ኦሮሞ ጄኔራሎች የጡረታ ጊዜያቸው ተራዘመ

ኦህዴድ መራሹ የብልፅግና መከላከያ ተቋም ጡረታቸው የደረሱ አመራሮችን ሲለይ የኦሮሞ ተወላጆችን የጡረታ ጊዜ በማራዘም በቅርቡ የቀነሳቸው የአማራ እና የደቡብ ተወላጅ ጄኔራል መኮንኖች ዝርዝር:-
1- ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ
የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ ሃላፊ የነበረ
2- ሜጄር ጄኔራል አለሙ አየነ
የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጅስቲክስ ሀላፊ የነበረ
3- ሜጄር ጄኔራል ታገሰ ሌምባቦ
የኮማንዶና አየርወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጅስቲክስ ሀላፊ የነበረ
4- ብርጋዲየር ጄኔራል ማርየ በየነ
የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር አዛዥ የነበረ
5- ብርጋዴር ጄኔራል ሻምበል በየነ
የ31ኛ ክፍለጦር አዛዥ የነበረ
6- ብርጋዴር ጄኔራል ዳዊት ወልደሰንበት
በደቡብ ሱዳን ወታደራዊ አታሼ የነበረ
7- ብርጋዴር ጄኔራል አበበ በየነ
በመከላከያ ኢንስፔክሽን የአደጋ መከላከያ መምሪያ ሀላፊ የነበረ
8- ብርጋዴር ጄኔራል ካሳ ደምሌ
በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የኮር አዛዥ የነበረ
9- ብርጋዴር ጄኔራል ሲሳይ ውብለኔ
የመከላከያ ኢንስፔክሽን የሴፍቲ መምሪያ ሀላፊ የነበረ
ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹ ከ 30 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ናቸው።
በከፍተኛ ህመም የሚሰቃዩ ነገርግን ከመከላከያ ተቋም መውጣት የማይፈልጉ እና እንዳይወጡ የተደረጉ የኦሮሞ ተወላጅ አመራሮች እያሉ እነዚህን ብርቱ ሰራተኛ እና በየአውደግንባሮቹ ዘመናቸውን ሁሉ ዋጋ የከፈሉ አመራሮችን አሰናብቷቸዋል።
የመከላከያ ተቋም ከጄኔራል አበባው ታደሰ ከጄኔራል ባጫ ደበሌ እና ከሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ ጀምሮ በየጊዜው ተሰናብተው የነበሩ አመራርና አባላትን እየጠራ ሚሊተሪ እያለበሰ ቢሆንም አገርና ህዝብ እየተበደለ መሆኑን በየመድረኩ የሚያቀርቡ አመራሮችን ግን ተገቢውን የጄኔራልነት ጥቅማጥቅም ሳያሟላላቸው እያሰናበታቸው ይገኛል።
በሌላ በኩል:-
በትግራዩ ጦርነት በTDF ሀይል በተለያየ ጊዜ ተማርከው የነበሩና በምህረቱ የተለቀቁ የክፍለጦር አዛዦችን መከላከያ ተቀብሎ ለእስር እና ለሹመት ዳርጓቸዋል።
ከእነዚህም መካከል የ11ኛ ክፍለጦርን በመምራት በ2013 ዓ.ም በተምቤን የተማረከው ኮሎኔል ሁሴን መሃመድ መሃመድ የደቡብ ዕዝ ኮር አዛዥ ሲደረግ በ2015 ዓ.ም በራያ ግንባር ቆስሎ የተማረከው የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል መኳንንት ደሴ ደግሞ ህክምና እንኳ ሳይደረግለት ከነቁስሉ በአፋር ክልል በሚገኜው ሱዑላ የጦር እስረኞች ማቆያ ታስሮ ይገኛል።
የብልፅግናው አገዛዝ በአሁኑ ጊዜ በሰራዊቱ እና በአመራሩ ያለው ተቀባይነትም እየተሸረሸረ የሚገኝ ሲሆነሰ ልክ እንደ ህክምና ባለሙያዎች ሁሉ የደሞዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ያቀረቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በመታሰር ላይ ይገኛሉ።