የአብይ አሕመድ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ስልጣን ለቀዋል

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌቱ በፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ዋዜማ ከኮሚሽኑ ምንጮች ሠምታለች። ተገኘወርቅ የኮሚሽኑ ቆይታ ባንድ ዓመት በተራዘመበት ወቅት ገደማ ከኃላፊነት የለቀቁት፣ ለኮሚሽኑ ቀደም ሲል በተሠጠው የሥራ ጊዜ ማገልገላቸው በቂ መኾኑን በመጥቀስ መኾኑን ምንጮች ጠቁመዋል። ኾኖም ይህ ዘገባ እሰከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ በተገኘወርቅ ምትክ አዲስ ኮሚሽነር አልተተካም። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለምን ተተኪ ኮሚሽነር እንዳልሾመ የጠየቅናቸው የኮሚሽኑ ምንጮች፣ እስካኹን ባለው ኹኔታ አስፈላጊ ነው ተብሎ ስላልታመነበት መኾኑን ጠቁመዋል። በሥራ ላይ ያሉት ኮሚሽነሮችም፣ በተገኘወርቅ ቦታ አዲስ ኮሚሽነር እንዲተካ እምብዛም ፍላጎት አላሳዩም ተብሏል።