በራያ ቆቦ ግንባር አንድ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኮሎኔል ሲቆቅል በርካታ ወታደሮች ደግሞ መገደላቸው ተሰማ!

በራያ ቆቦ ግንባር አንድ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኮሎኔል ሲቆቅል በርካታ ወታደሮች ደግሞ መገደላቸው ተሰማ!

በአፋብኃ የቤተ-አማራ ቀጠና ልዩ ዘመቻ አሃድ ኮማንዶዎቹ ራያ ቆቦ ተኩለሽ ዙሪያ አንድ ኮሎኔል በማቁሰል እና በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱን በመደምሰስ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል ሲል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አበበ ፈንታው አስታወቀ።

ምሽግ ለቆ መሃል የገባውን የጠላት ሃይል እንደተለመደው ስንቅና ንብረት እንዳይደርሰው እንዲሁም ተጨማሪ ሃይል እንዳያገኝ ብሎም ወንዝ በመሄድ ውሃ እንዳይቀዳ ጭምር በማድረግ መፈናፈኛ በማሳጣት ከቦ የመምታቱ ተጋድሎ ተጠናክሮ ቀጥሏል::

የቤተ-አማራዎቹ የልዩ ዘመቻ አናብስቶች ዛሬ ግንቦት 26/2017 ዓ.ም ንጋት 1:00 ጀምሮ እስከ ቀን 8:00 በዋለ ከባድ ተጋድሎ ከቆቦ ከተማ ተነስቶ በርካታ እግረኛ ሃይል እና በብረት ለበስና ዙ23 ታጅቦ በሶስት አቅጣጫ ስንቅና ንብረት ሲያጓጉዝ የነበረን የጠላት ሃይል በግድብ በመቀረጫው እና በጠበለት አንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ ኮሎኔል በማቁሰልና በርካታ ሃይሉን በመረምረም ሙትና ቁስለኛውን እንዲታቀፍ አድርገውታል::

በዚህ ተጋድሎ በርካታ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ የተመታበት የጠላት ሃይል ከቆቦ ከተማ አቅራቢያ ሆርማት ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተጠመደ መድፍ ከ20 በላይ ቅምቡላ ንፁሃንን ኢላማ አድርጎ በማስወንጨፍ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አድርሷል::