የኢራን እና እስራኤል ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል።

የኢራን እና እስራኤል ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል።

ኢራን በእስራኤል ላይ የድሮንና የሚሳኤል ጥቃት ስትፈጽም በዋነኛነት ሃይፋ እንዲሁም ቴላቪቭ ኢላማ ተደርገዋል።

እስራኤል በበኩሏ በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን የሚገኙ ኢላማዎች ላይ ጥቃት እየሰነዘረች መሆኑ ተገልጿል።

በቴህራን የነዳጅ ማከማቻ ኢላማ ያደረገ ጥቃት ተደጽሞ ከፍተኛ እሳት በስፍራው መነሳቱ ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ኢራን በዓለም ትልቁ የጋዝ ማምረቻ በእስራኤል ጥቃት ምክንያት በከፊል ስራ መቆሙን ገልጻለች።