የሶስት ወር አጭር የአማራ ክልል ጦርነት ዘገባ #ግርማካሳ

አብይ አህመድ፣ ብርሃኑ ጁላና የኦሮሙማ ጓዶቻቸው ፣ አንደኛ የነማይክ ሃመርን ድግፍና ከውጭ ገንዘብ ለማግኘት፣ ከህወሃት ጋር በመናበብና በመቀናጀት ፣ ህወሃቶች እነ ወልቃይትን ለመቆጣጠር እንዲያመቻቸው፣ ከወዲሁ ፋኖዎችን ትጥቅ ለማስፈታት፣ ሁለተኛ ፣ “በመሃል አገር ታላቋን ኦሮሚያ እንዳንመሰረት ችግር የሚሆንብን አማራው ስለሆነ፣ አማራውን መሰበር አለብን፡፡ አማራውን ትጥቁን ብቻ ሳይሆን ሱሪዉን እናስፈታለን” በሚል፣ በጥጋብና በጀብደኝነት ጦርነት የከፈቱት፣ ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ/ም ነበር፡፡ ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓ/ምን አለፍን፡፡ ጦርነቱ ሶስት ወራትን ደፍኖ፡፡
በመከላከል ላይ አተኩሮ የነበረው ፋኖ በትንሹም ቢሆን ወደ ማጥቃት የተሸጋገረበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አገዛዙ ከመሃል አገር ወታደር በየብስ የሚያመላልሰው፣ ስንቅና ትጥቅ፣ ሎጂስቲክ የሚያቀርበው፣ በአዋሽ፣ ሚሌ በኩል አድርጎ ነው፡፡ ከሚሌ በካሳጊታ ባቲ አድርጎ ወደ ወሎ ኮምቦልቻ፣ ከሚሌ በጭፍራ፣ ሃራ፣ ጉብዬ አድርጎ ወደ ወልዲያ ባለው መስመር ነው፡፡ ኮምቦቻልቻና ወልዲያ ለአገዛዙ ከሎጂስቲክ አንጻ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ፣ ከመሃል አገር በደጀን በኩል ወደ ጎጃም መሄድ የማይታሰብ ነው፡፡ በድብረ ብርሃኑ፣ ደብረ ሲና በኩል የግል መኮኖች ካልሆኑ ወታደሮችን ማመላለስ አይቻልም፡፡ ከኮምቦልቻ በመካነ ሰላም አድርጎ ወደ ጎጅማ መርጦ ለማሪያም የሚሄደው አይቻልም፡፡ የቀረችው ከወልዲያ በጋሸና በኩል ወደ ደብረ ታቦር፣ ወሮታ አድርጎ ወደ ሰሜን ወደ ጎንደር፣ ወደ ድቡብ ወደ ባህር ዳር የሚወስደው መንገድ ነው፡፡ ይህንን መንገድ አገዛዙ መጠቀም እንዳይችል ተደርጓል፡፡
1ኛ # በሰሜን ወሎ ዞን፣ መስቀለኛና ስትራቲጂክ ቦታ ላይ የምትገኘው፣ ከህወሃት ጋር ጦርነት ሲደረግ ብዙ ጊዜ ስትያዝ፣ ስትለቀቅ ፣ ከፍተኛ ጦርነቶች ሲደረጉባት የነበረችው፣ የጋሸና ከተማ በምስራቅ አማራ ፋኖ ቁጥጥር ስር ሆናለች፡፡ ሙሉ ለሙሉ ከብልጽግና ታጣቂዎች ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓ/ም ነጻ ወጥታለች፡፡ ከጋሸና በተጨማሪ እንደ ደብረደቢጥ፣ መቄት፣ አግሪት በፋኖዎች እይታ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ከላይ እንደገለጽኩት በዚህ ምክንያት ነው የወልዲያ ደብረ ታቦር መንገድ ለአገዛዙ ዝግ የሆነበት፡፡
በተጨማሪ የአምራ ኃይሎች በወሎ በዋድላ፣ ደላንታ፣ መቄት፣ ላስታ፣ ጊዳን፣ ጉቦ ላፍቶ፣ አምባሰል፣ አማራ ሳይንት፣ ወግዲ ወረዳዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ በቆቦ፣ በሮቢት፣ በወልዲያና በኡርጌሳም ከባባድ ውጊያዎች ተድርገዋል፡፡
2# በአማራ ሳይንት አጅባር አጋባቢ ፣ ወደ አካሳታና ወረኢሉ በሚወስደው አቃጣጫ፣ ከደሴ ወደ ጎጃም በሚወስደው መስመር፣ በወግዲ፣ እንዲሁም ከወረኢሊና አቃስት ወደ ስሜን ትንሽ ራቅ ብሎ ባለው በአማራ ሳይንት ወረዳ ከፍተኛ ውጊያዎች ተደርገዋል፤ እየተደረጉም ነው፡፡ከወግዲ ከተማና ከአማራ ሳይንት ዋና ከተማ አጅባር የአገዛዙ ጦር ተሸንፎ ለቆ ወጥቷል፡፡
3#ከደሴ ወደ ጎጃም መርጦ ለማሮያም በሚወስደው መንገድ፣ በወረኢሉና መካነሰላም መካከል ባለችው በገነቴ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ በተወሰደው እርምጃ ፣ በዚያ የነበረው የአገዛዙ ካምፕ እንዳልነበረ ሆኗል፡፡ ከ80 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡ ብዙዎች ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ አገዛዙ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
4# የብልጽግና ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙትን ኢሰብዓዊና ጭቃኒያዊ የሰላማዊ ዜጎች ግድያን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞና ህዝብን ለማዳን በተሰማሩ ፋኖች ትንቅንቅ፣ ጎሮጎራ፣ ቆላ ድባ፣ ጩዋሂትን ጨምሮ አብዛኛው የምስራቅና የምእራብ ደምቢያ ወረዳዎች ከብልጽግና አገዛዝ ነጻ የወጡበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
5# በደቡብ ጎንደር ዞን ከእብናት ጀምሮ እስከ አዲስ ዘመን፣ ከአዲስ ዘመን እነ ማክሰኚት ጨምሮ፣ እስከ ጎንደር ከተማ ጫፍ ያለውም አካባቢ በፋኖዎች ስር ነው፡፡ ስሜን ጎንደር ያው ሰሜን ጎንደር ነው፡፡ በዚያ ያሉ አመራሮች፣ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ያለዓለም ፋንታሁንን ጨምሮ ከህዝብ ወገን ናቸው፡፡ አገዛዙ፣ ከሶስት ወር በፊት ጦርነት ሲከፍት፣ በዚያው በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በአጀሬ/ጃኖራ ነበር ትንኮሳ የጀመረው፡፡ በተከታታይ ሽንፈት ሲደርስበት በሰሜን ጎንደር አርፎ የተቀመጠበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
6# በሰሜን ሸዋ፣ በይፋት በሸዋ ሮቢት አካባቢ ከፍተኛ ጦርነቶች ተደርገዋል፡፡ ሐምሌ 18 ቀን በሸዋ ሮቢትና በደብረ ሲና፣ ሸክላ ሰባሪ፣ የሬፓብሊካን ጋርድ የሚባሉ ቀይ ቦኔቶች ያሉበት፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ኮንቮይ ላይ በተደረገ ደፈጣ ኮንቮዩ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል፡፡ ከሰሳላ በላይ የተገደሉ ሲሆን ብዙዎች ተማርከዋል፡፡ በርካታ ከባባድ መሳሪያዎች ሳይቀር በአማራ ሓይሎች እጅ ውስጥ ገብተዋል፡፡
7# በመርሃቤቴ በዓለም ከተማ አካባቢ፣ በሚገኘው የአገዛዙ ካምፕ ላይ በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት፣ በካምፑ የነበረው የአገዛዙ ጦር ያለቀው አልቆ፣ የቆሰለው ቆስሎ፣ የተማረከው ተማርኮ፣ የቀረው እግር አውጪን ብሎ ተበታትኗል፡፡ ፋኖዎች የአገዛዙ ጦር ሲማረክ ያስረከበውንና ጥሎ የሂደውን በርካታ ከባባድ መሳሪያዎችንና የጥይት ሳጥኖችን ማርከዋል፡፡
8# ምስራቅ ጎጃም፣ ከደብረ ማርቆስ እስከ ደጀን ከተማ ያለው መስመር ብቻ ነው የሚቀረው፡፡ አብዛኛው ምስራቅ ጎጃም፣ በፋኖዎች እይታ ውስጥ ነው ያለው፡፡ በመሃል ጎጃም ያሉ እንድ እደጋ ዳሞት፣ ቋሪትን ጨምሮ፣ በወለጋ መስመር፣ እንዲሁም በሸዋና በወሎ መስመር ያለው የአባይ ሸለቆ በፋኖዎች ቁጥጥር ስር ነው ያለው፡፡ በአዋኢ ዞንና በም እራ ጎጃም፣ ባህር ዳርን ጨምሮ፣ አገዛዙ አሁን በዚያ እየፈነጨ ነው፡፡
በአጠቃላይ ላለፉት 3 ወራት ቢያንስ 56 ከተሞችና አካባቢያቸው ከብልጽግና ወታደሮች ጋር ውጊያ ተደርጓል፤ ወይንም እየተደረገ ነው፡፡ በሁሉም ማለት ይቻላል፣ አገዛዙ ከፍተኛ ሽንፈት ነው የተከናነበው፡፡ ባህር ዳር የሰሜን መራብ እዝ ጀነራሎችና መኮንኖች ባደረጉት ስብሰባ ወይም ግምገማ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ 27 ሺህ የአገዛዙ ታጣቂዎች ቁስለኛ እንደሆኑ ተዘግቧል፡፡ የተገደሉና ፣ አንዋጋም ብለው ጥለው የሄዱ ተመሳሳይ ቁጥር ሊሆን ይችላል ብለን ብንወስድ አገዛዙ 81 ሺህ ወታደሮች አጣ ማለት ይቻላል፡፡
ውጊያ የተደረገባቸው አካባቢዎች፡
ጎጃም ክፍለ ሃገር ==> ፍኖተ ሰላም፣ ደምበጫ፣ አማኑኤል፣ ደብረ ኤሊያስ፣ ጂጋ፣ ፈረስ ሜዳ፣ ቋሪት፣ ደጋ ዳሞት፣ አዴት፣ ሞጣ፣ ግንደ ወይን፣ ቢቸና፣ ደብረወርቅ፣ መርጦ ለማሪያም፣ ሸበል በረንታ፣ እናርጅ ናውጋ
ጎንደር ክፍለ ሃገር ==> ጎንደር ከተማ፣ ጯሂት፣ ቆላድባ፣ ጎርጎራ፣ ማክሰኚት፣ አብርሃጂራ፣ አዲስ ዘመን፣ ወሮታ፣ እብናት፣ አጀሬ/ጃኖራ፣ ዳባት
ወሎ ክፍለ ሃገር ==> ላሊበላ፣ ወልዲያ፣ ቆቦ፣ ተኩለሽ፣ ሙጃ፣ ኡርጌሳ፣ አግሪት፣ ኮኪት፣ ደብረ ደቢጥ፣ ወገልጤና፣ አጅባር(አማራ ሳይንት)፣ ገነቴ፣ ወግዲ፣ መካነሰላም
ሸዋ ክፍለ አህገር ==> ሸዋ ሮቢት፣ ደብረ ሲና፣ ራሳ፣ ማጀቴ፣ አንጾቂያ፣ ገምዛ፣ አጣዬ፣ ቆሪ ሜዳ፣ ካራቆሬ፣ ሚዳ፣ ጃማ፣ ዓለም ከተማ፣ ጉንዶ መስቀል
ብዙዎቻችን ከጅምሩ ህዝብን ማሸነፍ አይቻልም ብለን ስናስጠነቅቅ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ወታደር አልቆባቸውም አሁን እነ አብይ አህመድ ከጥጋባቸው አልሰከኑም፡፡ በጀብደኝነት ማዘዣቸውን የኦነግ መናኸሪያ በሆነው በኦሮኦ ብሄረሰብ ዞን በምትገኘ ከሚሴ አድርጎ፣ ወታደሮች እያከማቹ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ከመተማ አካባቢ ወደ ጭልጋ፣ አባይ ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮችን ወደ ቻግ ኒ አዋኢ ዞን እያመጡ ነው፡፡ በባህር ዳር፣ ኮምቦልቻና ባህር ዳርም በአይሮፕላን ወታደር እያጓጓዙ ነው፡፡ አሁን ሰዎቹ ታውረዋል፡፡ አሁን አገር እናገልግል ብለው የገቡ ዜጎችን ለማስፈጀት ደፍ ደፍ እያሉ ነው፡፡
አሁንም እላለሁ ወደ አማራ ክልል የሚገባ ወታደር፣ መገደል፣ መማረክ ወይንም መቁሰል ነው እድል ፈንታው የሚሆነው፡፡
ይልቅ እነ አብይ አህመድ የማይሰሙ አጁዛዎች ናቸው እንጂ፣ ትንሽ እንኳን የሚሰሟችሁ ሰዎች ካላችሁ፣ ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱና ጦርነቱን እንዲያቆሙ ብታነጋግሯቸው ጥሩ ነው፡፡ እነርሱ በየመናፈሻው ሲዝናኑ፣ በየሪዞርቲ በሬ እያሳረዱ ቁርጥ ሲገጩ፣ ለምንድን ነው ድሃው የትም እንደ ቅጠል የሚረግፈው ??? በአማራ ክልል እየተደረገ ያለው ጦርነት መቆም አለበት !!!!!! አሁኑኑ !!!!!
አገዛዙ አልቆምም ካለ: የሽብር ተግባሩን ካላቆመ የህዝብን ጥያቄ ካላከበረ የህዝብ ሃይል ምርጫ የለውም የህዝብ እሸባሪዎችን ከመመከት ብሎም ከመደምሰስ ውጭ::