የእንግሊዝ ዶክተሮች የ4% የክፍያ ጭማሪ ቢያገኙም አነሰ በሚል ለተቃውሞ ድምፅ እያሰባሰቡ ነው።

የእንግሊዝ ዶክተሮች የ4% የክፍያ ጭማሪ ቢያገኙም አነሰ በሚል ለተቃውሞ ድምፅ እያሰባሰቡ ነው።

ባለፈው ሳምንት እንግሊዝ ለአስተማሪዎች እና ዶክተሮች ጭማሪ መደረጉን ብትገልፅም የብሪትሽ የሃኪሞች ማህበር በቂ ባለመሆኑ ሃኪሞች እንዲያምፁ እየጠየቀ ነው።

ማህበሩ የክፍያ ጭማሪው በቂ ባለመሆኑ የተነሳ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ ለመወሰን እንዲያስችል እስከ መጪው ሐምሌ 7 ድምፅ ይስጡ ብሏል።

በአዲሱ ጭማሪ መሰረት ለሪዝደንት ሃኪሞች 750 ፓውንድ ክፍያ ሲጨመርላቸው የሃኪሞቹ ማህበር ግን ትክክለኛ ገቢያችን ከ2008 ጀምሮ በ23 በመቶ በመቀነሱ የተደረገው ጭማሪ በቂ አይደለም ብሏል።

ማህበሩ ሃኪሞች በአድማው ላይ የይሁንታ ድምፅ ይስጡ ሲል መንግስት ክፍያዎችን ማስተካከል ያለበት ዛሬ ነው ብሏል።

በእንግሊዝ የሬዚደንት ሃኪም ከደሞዙ በተጨማሪ 37 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ለምሽት ስራዎች እና ሌሎችም ጥቅማጥቅሞችን ያገኛል።

በፋውንዴሽን ትሬኒንግ(F1) ያሉ ዶክተሮች መሰረታዊ የሚባል ከ36,616 እስከ 42,008 ፓውንድ በአመት ሲያገኙ የስፔሻሊስት ስልጠና የጀመሩ ደግሞ ከ49,909 እክከ 70,425 ፓውንድ ያገኛሉ።

የስፔሻሊቲ ዶክተር ከ59,175 ፓውንድ እስከ 95,400 ፓውንድ ሲያገኝ ሃኪሞቹ የስራ ጫናችን ባልቀነሰበት ሁኔታ ትክክለኛው ገቢያችን መቀነሱ አሳስቦናል ብለዋል።

በ2023 እና 2024 ዶክተሮቹ ተመሳሳይ ውሳኔ ውስጥ ገብተው የነበረ ቢሆንም በሁለት አመታት ውስጥ ክፍያቸው በ22 በመቶ ይጨምራል ከተባለ በኋላ ውሳኔያቸውን ቀልብሰው ነበር።

በአዲሱ ማሻሻያ የአንድ የሙሉ ሬዚደንት ዶክተር ክፍያ ከ38,800 ፓውንድ የሚጀምር ሲሆን ከ2023 አንፃር የ9500 ፓውንድ ጭማሪ አለው።

ማህበሩ ዶክተሮቹ በቂ ክፍያ ካልተከፈላቸው ከሃገር ወጥተው ይሰራሉ ያለ ሲሆን በ2023 ከ4000 በላይ ዶክተሮች ከሃገር ወጥተው ለመስራት ወስነዋል ወይም ደግሞ ስራቸውን አቋርጠዋል ብሏል።

Source: BBC , Yahoo news