ያልተቋረጠ የከባድ መሳሪያ እና የቦንብ ድብደባ በደብረ ኤልያስ ስላሴ ገዳም ተፈፀመ!

በዛሬው ዕለት ለተከታታይ ሦስት ሰዓታት ያልተቋረጠ የከባድ መሳሪያ እና የቦንብ ድብደባ በደብረ ኤልያስ ስላሴ ገዳም ተፈፀመ!

ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ድብደባው አለመቆሙን የመረጃ መንጮቻችን አረጋግጠዋል።

በርካታ ፀብልተኞች እና መነኮሳት ተገድለዋል።

አሁንም የኦህዴድ/ኦነግ ሠራዊት በኦራል ተጭኖ በገፍ ወደ ገዳሙ እየገባ ነው ሲሉ የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ገልፀዋል።

ገዳሙ ውስጥ ለሚደርሰው የንፁሃን ፀበልተኞች እልቂት ቀዳሚው ተጠያቂ የምስራቅ ጎጃም ዞን የብልፅግና አመራሮች እና የፀጥታ አካላት ናቸው ሲሉ አስረድተዋል።

ገዳሙ ባለፈው ሀሙስ ዕለት ከቀን 17/09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ስድሰት ቀናት በኦህዴድ/ኦነግ ጦር መጠነ ሰፊ ድብደባ እና ጥፋት እየተፈፀመበት ነው።

ከተገደሉት 7 መነኮሳት ባሻገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፀበልተኛ ተጎድቷል።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይዎቅ፤ ዛሬም አልቆመም።ህዝቡ ምን እንደሚጠብቅ አልታወቅም።