ፊላ የደራሼ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ

በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኙ የተለያዩ ብሄረሰቦች ካላቸው ባህላዊ አሴቶች መካከል ነባር የሙዚቃ መሣሪያዎቻቸው ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ ከእነኝህም መካከል ፊላ በመባል የሚታወቀው የደራሼ ብሄር ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ አንዱ ነው ፡፡ ፊላ ከትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያዎች የሚመደብ ነው፡፡ አጨዋወቱም በጋራ ሲሆን የተለየ ህብረ ድምፃዊ ቃናን ይሰጣል፡፡…