ገዢው ብልጽግና ፓርቲ አገሪቱ “ዘርፈ ብዙ የሌብነት ፈተና ገጥሟታል” አለ

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ዘርፈ ብዙ የሌብነት ፈተና የገጠማት መሆኑን እና ይህም የአገሪቱን “የድህነት ወገብ እያደቀቀ ነው”ሲል ገለጸ። ፓርቲው ለሁለት ቀናት ያደረገውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ አርብ መጋቢት 08/2015 ዓ.ም. ባወጣው ሰፊ መግለጫ ላይ እንዳለው፣ “ኢትዮጵያ ወደ ታላቅ ምዕራፍ በምትሻገርበት ድልድይ ላይ ነች” በማለት አምስት ዋነኛ …