በሸዋ ይፋት ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገ ሙከራ ከሸፈ

[addtoany]

በሰሜን ሸዋ፤ ይፋት፤ ቀዎት ወረዳ አርሶ አደሮችን ትጥቅ ለማስፈታት በአገዛዙ ታጣቂዎች የተደረገ ሙከራ በፋኖ እና በሕዝብ ተቃውሞ ሳይሳካ ቀርቷል። የሦስት አርሶ አደሮችን የነፍስ ወከፍ ጠመንጃ በኃይል ነጥቀው የነበረ ቢሆንም ተመልሶላቸዋል።

ሸዋ ሮቢትን ጨምሮ ፋኖዎችንም ትጥቅ የማስፈታት አዝማሚያዎች አሉ። ነገር ግን፣ ድርጊቱ ግልፅ መስመራዊ ጦርነት የሚያስከፍት መሆኑን የተረዳው አገዛዙ፣ ለጊዜው በሕዝቡ እና በፋኖዎች ጥንካሬ በተግባር ወደ ማስፈታት አለመግባቱን የመረጫ ምንጮች አረጋግጠዋል።

የአማራ ፋኖ- በይፋት በማናቸውም ሁኔታዎች የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ሳይመለሱ ትጥቅ እንደማይፈታ አስታውቋል።