“ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ደም አፋሳሽ እልቂት ያመጣል፤ እንዳትሞክሩት” – ፋኖ መ/አለቃ ማስረሻ ሰጤ

“ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ደም አፋሳሽ እልቂት ያመጣል፤ እንዳትሞክሩት” – መ/አለቃ ማስረሻ ሰጤ
የኦሮሞ ፖለቲከኞች ኦሮሚያ ክልልን ለታጠቀው ኦነግ ሸኔ አስረክበው autonomous ቀጠና ቢፈጥሩም፣ ልባቸው ግን በአማራ ክልል የታጠቁ ሃይሎች በሚሏቸው ላይ ነው። ይሄ ለምን ይመስላችሗል?ፋኖ በከበባ ውስጥ ያለው የአማራ ህዝብ መድህን ነው። አማራ በአሸባሪዎቹ ኦነግ ሼኔ እና በህወሃት፣ በኦነግ ብልፅግ እና በብአዴን ብልፅግና እንዲሁም በሱዳን ተስፋፊዎች ከበባ ውስጥ ወድቋል። ይሄ ከበባ የሚሰበረው ደግሞ በፋኖነት ነው።
ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ደም አፋሳሽ እልቂት ያመጣል። ፋኖንም በኦነግ ብልፅግና አለያም በብአዴን ብልፅግና ስር ለማስገባት መጣርም ከፍተኛ ችግር ያስከትላል። እንዳትሞክሩት። “የአማራ ህዝብ እየተከበበ ነው። በወለጋ የጅምላ ግድያ እየተፈፀመባቸው ሲሆን ህወሓት ግን የፖለቲካ አላማው ካልተሳካለት ክልሉን መልሶ ለመውረር እየተዘጋጀ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የጸጥታ አስከባሪዎች ህዝባችንን እየጠበቁ ባለመሆኑ ወጣቱ ፋኖን ተቀላቅሎ እራሱን እንዲከላከል አስፈላጊ አድርጎታል፤ ይህም ስጋቱን ግምት ውስጥ በማስገባት የተፈጥሮ መብታችን ነው ብዬ አምናለሁ” ብሏል ፋኖ ማስረሻ።