‹‹የትህነግ አባላት እንኳ ኢትዮጵያዊነትን በትግራይዋን መካከል እንኳን ልዩነቶችን የሚፈጥሩ ጠባቦች ናቸው፤ ለትህነግ ተመራጩ ዜጋ የአድዋ ተወላጅ የሆነው ሰው ብቻ ነው›› አቶ አገዘው ህዳሩ -የራያራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት
–
• የትህነግ አባላት ኢትዮጵያዊ ሥነልቦና ስለሌላቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለውን በሙሉ ባንዳ ብለው ይፈርጃሉ
• ትህነግ ገና ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያልነበረው ድርጅት ነው። ይህ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መስዋዕትነት ከከፈለው የትግራይ ሕዝብም ሆነ ከራያ ሕዝብ ጋር ፍጹም የተራራቀ ነው።
–
• በትግራይ ክልል ትህነግን የሚቃወሙ በሙሉ ባንዳ የሚል ተቀጽላ ይሰጣቸዋል። ይህን የሚሉት በምክንያት ነው። ትህነግ ሀገር እያ ስተዳደረ፤ ሕዝብ እየጨቆነና እየዘረፈ ባለበት ሰዓት ጭምር እራሳቸውን ከኢትዮጵያዊነት ውጪ ስለሚያደርጉ እና ኢትዮጵያዊነት ስለማይሰማቸው ኢትዮጵያውያንን በሙሉ ባንዳ ብለው የመፈረጅ ዕሳቤ አላቸው።
–
• የትህነግ አባላት ኢትዮጵያዊ ሥነልቦና ስሌላቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት ያለው በሙሉ ለእነሱ ባንዳ ነው። ከትህነግ አስተሳሰብ ውጪ ያለ በሙሉ ለእነሱ ባንዳ ነው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን ባንዳ ብለው ስያሜ የሚሰጡት የሀገርን ጥቅም ለውጭ ጠላት አሳልፎ የሚሰጥ ከሃዲን እንጂ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
• እነዚህ ሃይሎች የትግራይ ሕዝብ እኮ እንደልቡ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እንዳይበላ አድርገውታል። እነሱ በሰሩት ሥራ እንዲሸማቀቅ ፈርደውበታል።
–
• እንገነጥላታለን ብለው ለሚያስቧት የትግራይ ዲፋክቶ ስቴት እንቅፋት የሚሆንን በሙሉ ባንዳ እያሉ ይፈርጁታል። የራያ ራዩማ እንቅስቃሴ ደግሞ ያሰቡትን የዲፋክቶ ስቴት የሚያኮላሽባቸው ዋነኛ እንቅስቃሴ ስለሆነ አምርረው ይጠሉታል።
• ከፍተኛ ችግር የገጠመን ብዙዎች ህወሃት ብለው ከሚጠሩት እኛ ግን ትህነግ ብለን ከምንጠራው ድርጅት ነው። ህወሃት ብለን መጥራት የማንፈልገው ‹‹ወያኔ›› የሚለው ቃል ከራያ ሕዝብ ጋር የተያያዘ የትግል መጠሪያ ነው። ወያኔ የሚለውን የትግል መጠሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት ራያዎች ናቸው። ከሰሜን ሸዋ ጫፍ ጀምሮ ውጅራት ድረስ ለማንነት የተደረገው ትግል ወያኔ የሚል መጠሪያ ነበረው።
–
• ወያኔ የሚለው ታሪክ ከራያ ሕዝብ የተወረሰ ታሪክ ነው። ስለዚህም ወያኔ የሚለው መጠሪያ የራያዎች የትግል መጠሪያ ነው። ስለዚህም አሁን ወያኔ ብለው እራሳቸውን የሚጠሩትን እኛ ትህነግ ነው የምንላቸው።
• ስለዚህም የራያ ማንነት ጥያቄን ስናነሳ ከፍተኛ ተግዳሮት የገጠመን ከትህነግ ነው። የራያ አካባቢ ሰፊና ለም አካባቢ ነው። ለእርሻ በጣም ተስማሚ ነው። ትህነግም ይህንን አካባቢ በግድ በመውሰድ የትግራይን የምግብ ፍላጎት ለማሟላት አቅዶ ሲን ቀሳቀስ ቆይቷል።
–
• የትግራይ አብዛኞቹ አካባቢዎች ደረቅና ለእርሻ ተስማሚ ባለመሆናቸው የራያን አካባቢዎች ዋነኛ የግብርና ምርት ማግኛ አድርገው ተስፋ ጥለውባቸዋል። ትግራይ ትገነጠላለች የሚል አዋጅ የሚጎሰመውም የራያን ለም መሬት በመተማመን ነው።
• ራያን ወደ ትግራይ ለመውሰድ የታቀደው በ1968 ዓ.ም አካባቢ ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል። ስለዚህም እኛ ይህንን ሃቅ መግለጽ ስንጀምር በርካታ ተጽዕኖ ዎች ሲደርሱብን ቆይተዋል። ከማሳደድና መግደል ጀምሮ በራያ ውስጥ በነፃነት እንዳንንቀሳቀስ ተደርገ ናል።
–
• የራያን ኅብረተሰብ የራያራዩማ ዴሞ ክራሲያዊ ፓርቲ ደጋፊዎቻ ናችሁ በማለት የማንገላታትና ኅብረተሰቡም በልዩ ልዩ የማሰቃያ መንገዶች ተማሮ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ እየተደረገ ነው። የራያ ማንነትን የሚያቀነቅኑ ግለሰቦችን አድኖ ከመግደል አንስቶ የማህበረሰቡን ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የመግደልና የማጥፋት ሥራዎችን ሀገሪቱን ማስተዳደር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ሲሰሩ ቆይተዋል።
–
• የራያ ማንነትን የጠየቁ ሰዎች ኮረም ከተማ ላይ በገበያ መሃል ሕዝብ በተሰበ ሰበበት በገሃድ እንዲረሸኑ ተደርገዋል።
• የራያ እንቅስቃሴ በተመሳሳይ መልኩ ከትህነግ ጥቃት እንደሚደርስበት ግልጽ ነው። በአሁኑ ወቅት ባንዳ የሚል ስያሜ በመስጠት ወደ ራያ አካባቢ እንዳንገባ ተደርገናል። የራያ ማንነት ከዳር ለማድረስም ‹‹ስበር›› በሚል መጠሪያ ተደራጅቶ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርገውን ወጣት በገፍ በማሰርም ጥያቄውን ለማፈን ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
–
• ባለፉት ሁለት ዓመታት ስበር ባደረገው እን ቅስቃሴም በመደናገጥ የተለያዩ የኃይል እርምጃዎች ወስደዋል። ከ17 በላይ ወጣቶች ተገድለዋል። ከ2ሺ በላይ ወጣቶች አሁንም ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅትም ምርጫ እናካሂዳለን በሚል ቅስቀሳ ምርጫውን የሚያደናቅፍ ግለስብም ሆነ ቡድን እርምጃ እንደሚወሰድበት በግልጽ እየዛቱ ነው።
–
• ሃጫሉ ከመሞቱ ጥቂት ቀናት በፊት ትህነግ ከፍተኛ መተማመን አዳብሮ ነበር። ‹‹አዲስ አበባ ጀምረን አዲስ አበባ እንጨርሰዋለን›› የሚለው የአቶ ስዩም መስፍን አባባል በሁሉም የትህነግ መዋቅር ውስጥ ገብቶ ነበር። እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ይህ አባባል ሰርጾ ገብቶ ነበር።
–
• የሃጫ ሉን ሞት ትህነግ ሁልጊዜ ለሚያልመው ዳግም ወደ ሥልጣን የመመለስ ወይም ኢትዮጵያን የማፈራረስ ትልም የሃጫሉን ሞት እንደትልቅ ብስራት ነው የቆ ጠሩት። ሆኖም ግን የቀየሱት ዕቅድ ሲመክን በጣም አሸማቋቸዋል።
• ሕዝቡም እንደታዘባቸውና ድጋፉንም እየነፈጋቸው መምጣቱን በመረዳታቸው ሙሉ ለሙሉ ከቁጥጥራቸው ሳይወጣ በአፈና እንዲገዛቸው እያደረጉ ነው።
–
• ህዝቡ ለሚሊሻው ቀለብ እንዲሰፍርና ለሚሊሻው ደመወዝ ጭምር እስከአምስት መቶ ብር ድረስ እንዲያዋጣ ግዴታ እየተጣለበት ይገኛል። ገንዘብ የለኝም ያለ ጤፍና ስንዴ በመስፈር እንዲያስ ረክብ ግዴታ ተጥሎበታል።
• አሁን አሁን የትህነግን ሴራ እና ኢትዮጵያን ጠልነት የተረዱ ወላጆች ‹‹እንዲህ መሆኑን ብናውቅ ልጆቻችንን ባልገበርን›› የሚሉ ድምጾችን እያሰሙ ነው።ገና በረሃ እያሉ ኢትዮጵያዊ ስሜት ያላቸውን ታጋዮች አድነው አጥፍተዋቸዋል።
• የትህነግ ካድሬዎች አጀንዳ እየተሰጣቸው የሚያቃርኑ ጉዳዮችን በመያዝና የጋራ ማንነቶችን ለመበጣጠስ የሚያስችሉ ትርክቶችን በማንገብ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማኮላሸት ሥራዎች በስፋት ሲሰሩ ቆይተዋል።
–
• 2004 ዓ.ም አካባቢ ወደ አዲግራት ለሥራ በሄድኩበት ወቅት አንድ አባት ያሉኝ ትዝ ይለኛል። ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ሥራ እንዴት ነው? ኑሮ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄ አነሳሁላቸው። ‹‹አዬ ልጄ ምን ሥራ አለ ብለህ ነው፤ የገዛ ልጆቻችን ሀገራችንን አጥብበውብን›› የሚል አስገራሚ ምላሽ ሰጡኝ። የሽማግሌው አባባል የአብዛኛውን የትግራ ይን ሕዝብ ስሜት የሚገልጽ ይመስለኛል።
–
• የመቀሌ አካባቢ አርሶ አደር እኮ በአዲስአበባ ዙሪያ ከሚገኘው የኦሮሞ አርሶ አደር ቀጥሎ መሬቱን የተዘረፈና ይህ ነው በማይባል ሽራፊ ሳንቲም ለትህነግ ባለሀብቶችና ባለሥልጣናት ሸጦ ሜዳ ላይ የቀረ ሕዝብ ነው። በአጠቃላይ ትግራይ ሕዝብ እንኳን ሊጠቀም ቀርቶ በብዙ መልኩ ተጎድቷል የሚል እምነት ነው ያለኝ።
–
• ትህነግ ከገጠመው አጣብቂኝ አንጻር ምርጫውን ማካሄዱ አይቀሬ ይመስለኛል። ምርጫውን የሚያካሂደው ለሕገመንግሥቱ ጠበቃ በመሆን፤ ሕግን በማክበር፤ ለኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ በማድረግ ወይም ለትግራይ ሕዝብ በማሰብ ሳይሆን ምርጫውን ከገባበት አጣብቂኝ ውስጥ መወጣጫ ለማድረግ ነው። ትህነግ ሁሉም ፓርቲዎች ከተሳተፉ በምርጫው ተወዳድሮ እንደማያሸንፍ ያውቃል።
• ህወሃት ሕዝቡን እያደናገረባቸው ያሉ አጀንዳዎች አሉ። የመጀመሪያው ህዳሴ ግድብ ነው። የህዳሴ ግድብ ተሸጧል የሚል አሉ ባልታ በመንዛት ሕዝቡ በፌዴራል መንግሥት ላይ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲያሳድር አበክረው ሲሰሩ ቆይተዋል። አሁን መንግሥት የመጀመሪያውን ውሃ ሙሌት ማድረጉን ሲያሳውቅ ነገሩን ማድበስ በስ ጀምረዋል። ሕዝቡም ተራ አሉባልታ መሆኑን ተረድቶ ታዝቦ አልፏቸዋል።
–
• በሌላ በኩል ደግሞ ሀገሪቱ እየፈረሰች ነው የሚል የማስፈራሪያ ወሬ በመንዛት ሕዝቡን ሽብር ውስጥ ለመክተት ሲጥሩ ቆይተዋል። ይህ ከሃጫሉ ሞት ጋር ተያይዞ ዕቅዳቸው ሙሉ ለሙሉ ሲከሽፍ መልሰው ትተውታል።
• በቅርቡ ደግሞ የፌዴራል መንግሥትና ኤርትራ መንግሥት ሊወራችሁ ነው ታጥቃችሁ ጠብቁ የሚሉ ማስፈራሪያዎችን በማሰ ራጨት ወጣቱን በስፋት በማስታጠቅ ላይ ይገኛሉ።
–
• የአብይ መንግሥት ከውጭ ወራሪ ጋር በመሆን ሊወርህ ነው በሚል ሕዝቡ ሌላ ስሜት ውስጥ እን ዲገባ እያደረጉት ነው። በአጠቃላይ ህወሃትን ካልመ ረጥክ አደጋ ውስጥ ትገባለህ የሚል ሰፊ ፕሮፓጋን ዳና ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው።
• ህወሃት በሰራቸው መጥፎ ሥራዎች በርካታ ጠላቶችን አፍር ቷል። የትግራይ ሕዝብም እየተፋው ነው። ሕዝብን አፍኖ ዘላለም መኖር ስለማይቻል ዛሬ የሕ ዝቦች ትግል ፍሬ አፍርቶ ህልውናው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
–
• በትህነግ ውስጥ እራሱ አካሄዱን የሚቃወሙ አካላት ድምጻቸውን ማሰማት ጀምረዋል። በጎ ህሊና ያላቸው አባላቱ አካሄዱን እየተቃወሙት ነው።
• በዚህ ሁኔታም በመደና ገጥም በቅርቡ የካቢኔ ሽግሽግ ለማድረግ እስከማሰብ ደርሷል። በተለይም ያለማንም ከልካይ ሲያጋብሱት የነበረው ገቢ በመቀነሱ እንዳሻው የፈለገውን ለማድረግና በጥቅም ለመደለል እጅ አጥሮታል። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተደማምረው ትህነግ በመቃብር አፋፍ ላይ እንዲገኝ አስገድደውታል።
–
• የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተመሰረተው የካቲት 29 /2012 ዓ.ም ነው። ይህም ሆኖ ግን ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሌሎች አጋር አካላትና ከመንግሥት ጋር በመሆን የሕዝቡን የማነ ንነት ጥያቄ ለማስከበር በኮሚቴ መልክ ስንንቀሳቀስ ቆይተናል። ‹‹የራያ ማንነትና የራስ በራስ አስተዳደር ኮሚቴ›› መስርተን ረጅም እርቀት ከተጓዝን በኋላ በፓርቲ ደረጃ ቢዋቀር የበለጠ ትግሉን ከዳር ለማድረስ ያስችለናል የሚል እምነት ጨበጥን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን መሰረትን።
–
• የራያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በራያ ውስጥ እንዲንቀሳ ቀስ በትህነግ አይፈቀድለትም። የራያ ራዩማ ዴሞክ ራሲያዊ ፓርቲንና ሌሎች ትህነግን የሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ባንዳ የሚል ተቀጽላ በማውጣት የማሸማቀቅ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል።
–
ምንጭ – አዲስ ዘመን