የሞጣ ሙስሊሞች ም/ቤት ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ላይ ጥቃት ከመድረሱ በፊት ለከተማው አስተዳደርና ጸጥታ መምሪያ በደብዳቤ አሳውቋል ተባለ

የሞጣ ሙስሊሞች ም/ቤት ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ላይ ጥቃት ከመድረሱ በፊት ለከተማው አስተዳደርና ጸጥታ መምሪያ በደብዳቤ አሳውቋል ተባለ !

የሞጣ ሙስሊሞች ግዴታቸውን ተወጥተዋል!

No photo description available.ከስር የሚገኘው ደብዳቤ የሞጣ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከአንድ ወር በፊት ለአማራ ክልል መንግስት የፃፈው ነው። እስልምና ምክር ቤቱ ከእሱ እውቅና ውጭ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የአካባቢውን ሙስሊሞች ለመከፋፈል ከዚህም ሲያልፍ የእምነት ግጭት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የሚሰባሰቡትም ማር ዘነብ ሆቴል መሆኑን ገልፆአል። እስልምና ምክር ቤቱ ከእውቅናው ውጭ የሆኑ አካላት ኮሚቴ መርጠው ከመስጊድ ውጭ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን፣ ልዩነት ቢኖር እንኳ መስጊዳቸው ውስጥ መነጋገር እየቻሉ ሌላ ቦታ የሚነጋገሩት ችግር ለመፍጠር ነው ሲል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር። ጉዳዩ ወደ ሌላ ችግር ከመሄዱ በፊት የሚመለከተው አካል ክትትል ያድርግ ብለውም ነበር። የሞጣ ሙስሊሞች ግዴታቸውን ተወጥተዋል። ኃላፊነቱን ያልተወጣው የክልሉና የአካባቢው የመንግስት አካል ነው።

ሌላ አላማ ያላቸው አካላት ቤተ ክርስትያንም መስጊድም ቢቃጠል ጉዳያቸው አይደለም። ይህን የሚፈልጉት፣ ከአካባቢው እስልምና ጉዳዮች ውጭ ሌላ ኀይል ያሰማሩት እነ አህመዲን ጀበል ደግሞ ሰርግና ምላሽ ሆኖላቸዋል። ከእነሱ አማራው ክርስትያን ለአማራው ሙስሊም ይቀርባል። ምክንያቱም የእነ አህመዲን ጀበል አለቃ የሆነው ጃዋር አማራ ሙስሊሞችን ከኦሮሚያ ሲያፈናቅል ምንም ብለው አያውቁም። ባለፈው ናዝሬት ላይ ቤተ ክርስትያን እንዳይቃጠል የጣረ ሙስሊም ሲገደል፣ መስጊድ ሲቃጠል ምንም አላሉም።

የሞጣ ሙስሊሞች ከወራት በፊት ግዴታቸውን ተወጥተዋል። አሁን ደግሞ ክርስትያኑ የወደሙትን በመስራትና ሰርጎ ገቦችን በማጋለጥ በማገዝ ግዴታውን መወጣት አለበት። እንዲህ ካልሆነ የሞጣ ሙስሊሞች ቀድመው እንዳሳወቁት ግጭት ለመፍጠር የመጡትን እኩዮች መከላከል አይቻልም።

የሞጣ ሙስሊሞች በእምነት ስም የሚነግዱትን አሳልፈው ለመስጠት ቀድመው እንደሰሩ ሁሉ ክርስትያኑም እነዚህን ሰላማዊና ተምሳሌቶች ተግባር መድገም አለበት። በእምነት ስም ለሚነግዱት መጠቀሚያ የሚሆንን አሳልፎ መስጠት አለበት።

በሞጣ ከተማ በሃይማኖት ተቋማት ላይ በተፈጸመው ድርጊት ማዘኑንና ድርጊቱን እንደሚያወግዝ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ዛሬ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሰኢድ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ትናንት በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመውን የቃጠሎ ድርጊት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ታኅሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አጸያፊ ተግባር መፈጸሙን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በሞጣ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አራት መስጂዶች መቃጠላቸዉንና የሙስሊም ሱቆችና ድርጅቶች ላይ ዝርፊያ መፈጸሙን ገልጸዋል። ‹‹በተፈጸመው ድርጊት የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን፤ አስጸያፊ ድርጊቱንም እናወግዛለን›› ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።

ድርጊቱ ከኢትዮጵያ ባህል ያፈነገጠ ተግባር መሆኑንም አንስተዋል። መንግሥት ድርጊቱን በፈጸሙ አካላት ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድም ሸህ ሰኢድ አሕመድ ጠይቀዋል። ሕዝበ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ተደራጅቶ የሃይማኖት ተቋማቱን እንዲጠብቅም ጥሪ አቅርበዋል። መንግሥት ለሁሉም ቤተ እምነቶች ጥበቃና ከለላ እንዲያደርግም አሳስበዋል። ሕዝቡ ተመሳሳይ ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን ማጋለጥ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።

ከዚህ በፊት የመስጂድ ቃጠሎና ሌሎች የተከሰቱ አደጋዎችን መነሻ በማድረግ በሞጣ ከተማ ጥበቃ እንዲደረግ ለጸጥታ አካሉ አሳውቀው እንደነበርም ሸህ ሰኢድ አሕመድ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ደቡብ ጎንደር እስቴና ምሥራቅ ጎጃም ቢቸና መስጂዶች ተቃጥለዉ ሕጋዊ እርምጃ እንዳልተወሰደም በመግለጫቸው አስታውሰዋል።

‹‹በሞጣ ከተማ የክርስትያኑና የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ግንኙነት የተጠናከረ ነው። ድርጊቱም የሞጣ ከተማ ነዋሪዎችን አይወክልም›› ብለዋል፡፡ ድርጊቱ የክርስቲያኑንና የሙስሊሙን አንድነት ለመበታተን የሚፈልጉ አካላት የፈጽሙት መሆኑንም አስገንዝበዋል።