ሕወሓት ራሱን ችሎ የቆመ “ዲፋክቶ ስቴት” ለመሆን እንደሚሰራ ተናገረ – ዲፋክቶ ስቴት ምን ማለት ነው?

“De facto State of Tigrai”? –Abraha Desta

===================

“De facto” ምን ማለት ነው? ብዙ ግዜ “De facto” ለState ሳይሆን ለGovernment የሚመለከት ነው። “De facto Government” ማለት ሕጋዊ ያልሆነ እና ተቀባይነት (ወይ እውቅና) ያልተሰጠው ግን ባለው ነባራዊ ሁኔታ መሠረት ስልጣን ለመቆጣጠርና እንደመንግስት Act ለማድረግ ዕድል ያገኘ መንግስት ማለት ነው።

No photo description available.“De facto” የሚል ቃል ከGovernment ወደ State ስንወስደው “De facto State” ማለት ሕግ ሳይፈቅድለትና ተቀባይነት ሳያገኝ እንዲሁም እውቅና ሳይኖረው ያለውን ነባራዊ ሁኔታና ግዝያዊ ዓቅም ተጠቅሞ እንደ “State” function የሚያደርግ ሀገር መመስረት ማለት ነው።

በዚሁ መሰረት “De facto State” ሕገ ወጥ ነው። ተቀባይነትና እውቅና የለውም። እንደ ሀገር ለመንቀሳቀስ ዓቅም ግን ያለው ማለት ነው።

አንድ ክልል “De facto State” ለመመስረት ያለው ዓቅም ከሌሎች ክልሎችና ከፌደራል መንግስት በላይ መሆን አለበት፤ እውቅና ሳይኖሮውና ሕጋዊ ድጋፍ ሳያገኝ እንደ ሀገር act ለማድረግ ከሌሎች መብለጥ አለብህ። ሕግ የሚያስከብር ማእከላዊ መንግስት ካለ “ዲፋክቶ ሀገር” መመስረት አይቻልም።

ባሁኑ ሰዓት የDefacto State ምሳሌ ተደርጋ ምትወሰደው የሀገረ ሶማሊያ አንድ “ክልል” የሆነችው SomaliLand ናት። በሀገረ ሶማሊያ ህግ አክብሮ የሚያስከብር effective control ያለው ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ባለመኖሩ Somali Land እንደ State (ሀገር) act ታደርጋለች። ሕገ ወጥ ሀገር ናት። ማንንም እውቅና አልሰጣትም። ግን ሶማሊያ መንግስት አልባ ስለሆነች እንደ ሀገር ብትንቀሳቀስ ማንንም አትጎዳም።

ህወሓትም ምርጫ ካልተካሄደ “Defacto State of Tigrai” እመሰርታለሁ እያለች ነው። ትግራይ ክልል እንደ ሶማሊላንድ Defacto State መሆን ምትችለው ኢትዮጵያ ሀገራችን እንደ ሀገረ ሶማሊያ መንግስት አልባ ከሆነች ብቻ ነው።

“ምርጫ ካልተደረገ”? ህወሓት በ27 ዓመት የስልጣን ዘመኑ እውነተኛ ምርጫ አድርጎ አያውቅም ኮ! ህወሓት ምርጫ አድርጎ ስለማያውቅ አሁን ምርጫ መካሄድ የለበትም አይባልም። ምርጫ መደረግ አለበት፤ ህዝብ መተዳደር ያለበት በህዝብ በተመረጠ መንግስት ብቻ ነውና።

ምርጫ አለማድረግ ግን ዲፋክቶ ስቴት ምስረታ ሚበቃ አይደለም። ምርጫ አለማካሄድ ህገ ወጥ ነው እንበል ዲፋክቶ ስቴት መመስረት ግን የባሰ ህገ ወጥ ነው። “ዲፋክቶ” ማለት በራሱ ትርጉሙ ኮ ህገ ወጥ ማለት ነው። የDefacto State ተቃራኒኮ De Jure State ሊሆን ነው። “De Jure” ማለት ሕጋዊ ማለት ነው። “Defacto” ማለት ደግሞ ሕጋዊ ያልሆነ ነው። ስለዚህ “Defato State እንመሰርታለን” ማለት “ሕጋዊ ያልሆነ፣ ተቀባይነትና እውቅና የሌለው ሀገር እንመሰርታለን” ብሎ መናገር ነው።

“Defacto State እንመሰርታለን” ብሎ መናገር በራሱ አለማወቅ ነው። በምሳሌነት የምንጠቅሳት ሶማሊላንድ እንኳ ራሷ “Defacto State ነኝ” ብላ አታውቅም። ሶማሊላንድ “De Jure State ነኝ፤ ሁሉም ነገር አሟልቻለሁ፤ እውቅና ስጡኝ” ነው ምትለው። ምትፈልገው እውቅና ስላላገኘች ግን በሌሎች “Defacto State” ትባላለች።

ምርጫ ካልተደረገ በህዝብ የተመረጠ ሕጋዊ መንግስት ስለማይኖር “የሽግግር መንግስት ይቋቋም” ብሎ መከራከር ይቻላል። ዲፋክቶ ስቴት ግን በራሱ ሕገ ወጥ ነው።

ሀገር ከስልጣን በላይ ነው። ከስልጣን ስለተባረርክ ሀገር አፈርሳለሁ ማለት ክሽፈት ነው። ህዝብ ከፓርቲ በላይ ነው፤ ህወሓት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተጠላች የትግራይ ህዝብን ዕጣ ፈንታ በአንድ ድርጅት ፍላጎት ለመወሰን መፍጨርጨር ያስተዛዝባል።

የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱ አይደራደርም። ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር ይታገላል እንጂ ለህወሓት ዓላማ ሲባል በደሙና በአጥንቱ የገነባትን ሀገር ጥሎ አይገነጠልም!

ትግራዋይነት ኢትዮጵያዊነት ነው!

Abraha Desta