የኢንተርኔት አጠቃቀም ነፃነት በኢትዮጵያ መሻሻሉን ፍሪደም ሃውስ አስታወቀ

ፍሪደም ሐዉስ የተሰኘዉ ዓለም አቀፍ ተቋም ሰሞኑን ባወጣዉ ዓመታዊ ዘገባ የ65 ሀገሮችን የኢንተርኔት አጠቃቀም ነፃነት ገምግሟል።ከነዚህም ዉስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ 16ቱ ሀገራት መሻሻል የታየባቸዉ ሲሆን በ33ቱ ሀገራት ግን የኢንተርኔት ነፃነት በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ገልጿል።

በዘንድሮዉ የፍሪደም ሀውስ ጥናት መሰረት ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች የተባለችው ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ተግባራዊ ማድረግ በጀመሩት የለውጥ አጀንዳን ተከትሎ መሻሻሎች መታየታቸውን የተቋሙ ሪፖርት ጠቅሷል። ያምሆኖ  የኢንተርኔት አገልግሎት በየጊዜው ማቋረጡን አሁንም እንደቀጠለ ሪፖርቱ ጠቁሟል። ሆኖም ቀደም ሲል በመላው ሀገሪቱ ይደረግ ከነበረው የኢንተርኔት መዝጋት ጋር ሲነጻጸር የአሁኑ ጊዜያዊ እና የተወሰኑ ቦታዎችን የሸፈነ ነው ብሏል።

DW : ከአፍሪቃ ሀገራት መካከል ሱዳንና ዝምባቤዌ በከፍተኛ ደረጃ የኢንተርኔት ነፃነት ችግር ያለባቸዉ ሀገሮች መሆናቸዉን ዘገባዉ አመልክቷል።የዚምባዉ ጦማሪ ሙኒያ ብሎጎ ይህንን ያረጋግጣል።ብሎጎ እንደሚለዉ የኢንተርኔት ነፃነት በደቡባዊ የአፍሪቃ ሀገሮች ቀስበቀስ እያሽቆለቆለ ነዉ ።የከተማ ባህልና የሲቪል መብቶች ድርጅት ፕሮግራም ዋና ስራ አስኪያጅ ቡሎጎ ለDW እንደገለጸዉ።በሀገሩ ዝምባዌ የኢንተርኔት መዘጋቱ  የተጀመረዉ በጥር ወር ለጥቂት ቀናት ብቻ  ነበር ።ከዚያ ግን ዘዴዉ ተቀየረና ከበይነ መረብ አንቂዎች እስከ ኮሜዲያኖች ድረስ የተለያዩ ድምፆችን ማፈን ተሞከረ ይላል።እንደ ጦማሪ  የኢንተርኔት ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስበት እንደነበረ የሚገልፀዉ ይህ ችግር ከጊዜ ወደ ጌዜ እያደገ መምጣቱን ተናግሯል።

«በ2017 አንድ የማህበራዊ መገናኛ አዉታር ባልደረባችን አንዱ  የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም« በህጋዊ መንገድ የተመረጠን መንግስት ለመጣል ሙከራ ማድረግ»  በሚል ክስ  በቁጥጥር ስር ዉሎ ለአምስት ቀናት በከፍተኛ ጥበቃ ባለበት እስርቤት ታስሮ ነበር።»
ፍሪደም ሀዉስ በዘንድሮዉ የ2019 ዘገባዉም መንግስታት የዜጎቻቸዉን ተቃዉሞ ለማፈን ወደ መኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መዞራቸዉን ገልጿል።በእነዚህ የመገናኛ ብዙሃን አዉታሮች የሚደረገዉ ክትትል  በየበይነ መረቦቹ የሚደረጉ ማህበራዊ ንቅናቄዎችን አደጋ ላይ ይጥላል ሲል አስጠንቅቋል።
የፍሪደም ሃዉስ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሀገሮች የኢንተርኔት ነፃነት ባለሙያ  የሆኑት ኢዛቤል ሊንዜል ለDW እንደገለፁት ይህ ችግር ከሳሃራ በታች ባሉ የአፍሪቃ ሀገሮች የሚታይ ነዉ።

FOTN 2019 - The Global Phenomenon of Digital Election Interference«ይህ ብዙውን ጊዜ ሰው ሰራሽ ብልሃቶችን መጠቀምን ያጠቃልላል። እና በብዙ ጉዳዮች ላይ የደህንነት ኤጀንሲዎች በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ የጅምላ ክትትል ያደርጋሉ።ይህንን በኬንያን፣ደቡብ አፍሪቃን፣አንጎላን፣ ናይጄሪያንና ዩጋንዳን በመሳሰሉ የአፍሪቃ ሀገራት እይተናል።»
እንደ ዚምባዌ ያሉ የአፍሪቃ ሀገራት መንግስታት ዜጎች በበይነ መረብ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመከታተል የሚያስችሉ ህጎች አዉጥተዋል። የዲጂታል መብቶች እና ደህንነት ጥበቃ አሰልጣኝ የሆኑት ናታሻ ሙሶንዛ እንደሚሉት ከህጉ በተጨማሪ መንግስት የራሱን አጀንዳ የሚያስተዋውቅ እና በኢንተርኔት  ላይ የተንሸራሸሩ አስተያየቶችን ና  የተቃዋሚዎችን  ሀሳብ ለማጥፋት  የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃንን  ይጠቀማል ።
«ራሳቸዉን «ቫርካሽ »ብለዉ የሚጠሩ የቲዉተር ተጠቃሚ ቡድኖች አሉ።ይህም ባሻና ቋንቋ ማጥፋት ማለት ነዉ።አዲሱ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ለደጋፊዎቻቸዉ ይደዉሉና ወደ «ሻራካሽ»ይልኳቸዋል።ድንገት በድህረ-ገፅ አዳዲስ ትክክለኛ ስምና እዉነተኛ ገፅታ  የሌላቸዉ ሌሎችን ዒላማ ያደረጉ አድራሻዎች ይከፈታሉ።እናም  እንዲህ አይነት አዝማሚያዎችን እያየን ነዉ።»
ሌላኛዋ  በፍሪደም ሀዉስ  ዘገባ በኢንተርኔት ማሽቆልቆል የተጠቀሰችዉ አፍሪቃዊት ሀገር ሱዳን ስትሆን በሱዳን የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን እንዲወርዱ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አዉታሮችትልቅ ሚና ነበራቸዉ።የዶቼ ቬለ ባልደረባ ሳንሶኒ ኦስማን እንደሚለዉ ፌስቡክ፣ቲዉተርና ዋትስአፕን የመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናና ዘዴዎች ባይኖሩ ኖሮ የሱዳን አብዮት አይታሰብም ነበር ይላል።ያም ሆኖ በአሁኑ ወቅት ኔትፊሊክስን፣ ፔይፓልና አዶቤን የመሳሰሉት የመረጃ መረቦች አሁንም ችግር መኖሩን ገልጿል።
በዘንድሮዉ የፍሪደም ሀውስ ጥናት መሰረት ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች የተባለችው ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ወዲህ ተግባራዊ ማድረግ በጀመሩት የለውጥ አጀንዳን ተከትሎ መሻሻሎች መታየታቸውን የተቋሙ ሪፖርት ጠቅሷል። ያምሆኖ  የኢንተርኔት አገልግሎት በየጊዜው ማቋረጡን አሁንም እንደቀጠለ ሪፖርቱ ጠቁሟል። ሆኖም ቀደም ሲል በመላው ሀገሪቱ ይደረግ ከነበረው የኢንተርኔት መዝጋት ጋር ሲነጻጸር የአሁኑ ጊዜያዊ እና የተወሰኑ ቦታዎችን የሸፈነ ነው ብሏል።

Twitter Logo (Imago Iamges/Zuma/J. Arriens) የመረጃ ነፃነት ባለሙያዋ ሊንዘር እንደሚሉት በሀገራት የኢንተርኔት ነፃነት እንዲኖር ለማድረግ መንግስት ፣የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች፣የሲቪል ማህበራትና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት መስራት አለባቸዉ። ያም ሆኖ  በምርጫ ወቅት ህጎችን ተፈፃሚ ለማድረግና የመናገር ነፃነትን ለመጠበቅ  መንግስታት ቁልፍ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።እንደ ሊንዘር ገለፃ የሲቪል ማህበራትም መንግስት እነዚህን ህጎች እንዲያወጣና ግንዛቤ እንዲያሰፋ  ግፊት በማድረግ  ሊያግዙ ይችላሉ ።

ደቡብ አፍሪቃዉያንን  አንድ ያደርጋል የተባለዉ የራግቢ ድል

የደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ቡድን «ስፕሪንግ ቦክስ» ሶስተኛዉን የዓለም የራግቢ ውድድር ያለፈዉ ዕሁድ አሸንፎ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
ቡድኑ  የብሪታንያ ባላጋራዉን  አሸንፎ  ያለፈዉ ማክሰኞ ሀገሩ ሲገባ በሀገሪቱ የሚገኙ ጥቁሮች፣ነጮች፣ህንዶችና ክልሶች ኦሊቨር ታምቦ ዓለም አቀፍ አዎሮፕላን ጣቢያ  ድረስ ሄደዉ በአንድነትና በደስታ ተቀብለዉታል።በህብረትም ስለ ሀገራቸዉ ዘምረዋል።በዚህ የተነሳ   የቡድኑ ድል በሀገሬዉ ህዝብ ዘንድ አንድነት መፍጠሩም እየተነገረ ነዉ።
የቡድኑ አሰልጣኝ ሲያ ኮሌሲ የቡድኑ ድል የተገኘዉ በአንድነትና ጠንክሮ በመስራት መሆኑን ለደቡብ አፍሪቃዉያን ለመመስከር ጊዜ አላጠፉም።
«እንድ ሀገር ብዙ ተግዳሮቶች አጋጥመዉናል።እናም ሁልጌዜ በአንድላይ ሆነን ይህንን ለማለፍ የሚያስችል መንገድ እናገኛለን።በዚያን ጊዜ በአንድ ላይ ሆነን ለአንድ ነገር መታገል ጀመርን። ልንሸነፍ እንደምንችል እናዉቅ ነበር።ስእያንዳንዱን ጨዋታ መታገል ነበረብን።ስለዚህ የምንችለዉን ሁሉ አደረግን ።»
የስፕሪንግ ቦክስ ደጋፊ የሆኑት ማማሎ ማካ የአሰልጣኙን ሲያ ኮሊሲን ሀሳብ ይጋራሉ።

Japan | Südafrika gewinnt die Rugy Weltmeisterschaft gegen England (Imago Images/Kyodo News) «ቦክ ለደቡብ  አፍሪቃዉያን በሰራዉ እንኮራለን።ምክንያቱም ምናልባት የበለጠ አንድ እንሆናለን።ፍቅር አሳይተዉናልና እርስ በእርሳችን እንዋደዳለን ።የበለጠ እንድንኮራ ካደረጉኝ ነገሮች ደግሞ የቡድኑ አምበል ጥቁር ነዉ።ያንን የበለጠ ወደነዋል።»
በሀገሪቱ የሚታተም አንድ ጋዜጣ እንደፃፈዉ  «ድሉ የፈጠረዉ አንድነት ልክ እንደ  በዓል ችግሮቻችንን አስረስቶናል።» ብሏል።ቡድኑ  በጎርጎሮሳዉያኑ 1995  ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ሲያሸንፍ ሀገሪቱ ከአፓርታይድ ተፅዕኖ ገና መላቀቅዋ ስለነበር በቡድኑ ዉስጥ የነበረዉ አንድ የጥቁር ተጫዋች ብቻ ነበር።
በ2019 ሀገሪቱ የኢኮኖሚ ቀዉስን፣ከፍተኛ የስራ አጥነት ችግርን፣ሙስናን፣የመጤ ጠል ጥቃትን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች ገጥመዋታል። እነዚህና ሌሎች ተግዳሮቶች አሁንም አሉ።ሆኖም የደቡብ አፍሪቃ ተወላጅ የሆኑት ዴቪድ ሆግ እንደሚገልፁት በቡድኑ ዉስጥ የነበሩት አስራ ሶስቱ ጥቁርና ነጭ ተጫዋቾች መካከል የነበረዉ ትብብር የሀገሪቱን ችግር እንዴት መፍታት እንደሚቻል ፍንጭ የሰጠ ነበር።
«እኛ ደቡብ አፍሪቃዉያን ቀስተደመናዎቹ ህዝቦች እንደምታዩት በጣም ኮርተናል በጣምም ተደስተናል። በዚህ የአንድነት መንፈስ ከፊታችን ብሩህ የተስፋ አመት ይጠብቀናል።ብዙ ችግሮች ቢኖሩብንም እነሱን ለመቋቋም ደፋርና ዝግጁ ነን»
ብዙ ደቡብ አፍሪቃዉያን እንደሚሉት አምስት ተጫዋቾቻቸዉና  የቡድኑ አምበል ጥቁር የሆኑበት ቡድኑ  ዋንጫዉን ወደ ሀገሩ ማምጣቱ የሚያፅናና ነዉ።
ሜልት ዋተር የተባለ የመገናኛ ብዙሃን የመረጃ ድርጅት ተመራማሪ  ሲፎ ሄላ እንደሚሉት ስፕሪንግቦክስ ደቡብ አፍሪቃዉያን አንድነታቸዉን የማጠናከር ፍላጎት እንዳሳደራባቸዉ በማህበራዊ መገናኛ አዉታሮች  የተደረጉ ዉይይቶች ማሳየታቸዉን ገለፀዋል።

Japan | Südafrika gewinnt die Rugy Weltmeisterschaft gegen England - Siya Kolisi (Getty Images/D. Rogers) «ሲያ ኮሊሲ የእያንዳንዱን ደቡብ አፍሪቃዉያን ልብ አሸንፈዋል።መመሪያዉ ሲወጣ አባታቸዉ እሳቸዉ ሲጫወቱ ለማየት ለመጀመሪያ ጊዜ የሄዱበት ጊዜ ነበር።እንደማስበዉ በዚያ ቀን ብቻ ከ17 ሺህ በላይ በሆኑ ዉይይቶች እሱ ተጠቅሶ ተወርቷል። ከዓለም ዋንጫዉ ድል በኋላ ብዙዉይይቶችን መጠበቅ ይኖርብናል።»
የሀገሪቱ የስፖርት ሚንስትር ናቲ ማቲሃዋ በበኩላቸዉ  የተከፋፈሉ  ደቡብ አፍሪቃዉያንን ከቡድኑ ድል  ሊማሩ እንደሚገባ አስረድተዋል።
«ደቡብ አፍሪቃዉያን እርስበርሳችን እንድንቀራረብ ረድተዉናል።በማንኛዉም አካል ልንከፋፈል አይገባም።ይህን ልክ  በ1995ቱ ፣በ2007 እና እንደ ዘንድሮ  በ2019  እንዳደረግነዉ ለህዝባችን አንድነት እንደ ጠንካራ መሰረት ልንጠቀምበት ይገባል።»
ድል አድራጊዉን የራግቢ ቡድናቸዉን በደስታ የተቀበሉ ደቡብ አፍሪቃዉያን በሰላምና በአንድነት በፍቅር መንፈስ አብረዉ ዘምረዋል።የተገኘዉን ድል ለመዘከርም በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች አብረዉ ተጉዘዋል።ይህ የአንድነት መንፈስ ከድሉ ክብረ በዓል የሚሻገር መሆኑ ግን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።