ዶ/ር አብይ ካጠገባቸው ሆነው የሚጎረብጧቸው ሰዎችም ካሉ ይንገሩንና እስከ እቅታ ድረስ አብረን እንታገላቸዋለን – ብፀዕ አቡነ አብርሃም

ኢትዮጵያን እንደ ጠሩ በዚያ እንዲቀጥሉ እንፈላገለን – አቡነ አብርሃም

ብፁህ አቡነ አብርሃም ለዶ/ር አብይ አህመድ አባታዊ ምክር አስተላልፈዋል። ዶ.ር አብይ እስካሁን ለሰሩትን አላደረጉት ያላቸውን ትልቅ ምስጋናና አክብሮት የገለጹት አቡነ አብርሐም፣ ለዶ/ር አብይ ሕዝብ ድግፍና እገዛ እንዲያደርግ ጠቀዋል።

“የጠቅላይ ሚኒስትሩ እገዛ እስከመጨረሻው መዝለቅ አለበት ። ለምን ተቋረጠ!? ። አሁንም አሁንም ኢትዮጵያን እንደጠሩ በዚያ እንዲቀጥሉ እንሻለን ። ካጠገባቸው ሆነው የሚጎረብጧቸው ሰዎችም ካሉ ይንገሩንና እስከ እቅታ ድረስ አብረን እንታገላቸዋለን” ነበር ያሉት።

Image result for abune abraham

ይድረስ ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ
ከብፀዕ አቡነ አብርሃም

ማንም ቤተ ክርስቲያንን በጥፋተኝነት ሊወቅሳት አይችልም ። በየትኛውም ዓለም ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ናት። ክርስቲያኑ ንጉሥ ሙስሊም ወገኖቻችንን ተቀብሎ እንዳስተናገደ የሙስሊም መጻሕፍት ጭምር የመሰከሩት ነው። ለዚህም ነው ተከባብረን እየኖርን ያለነው። አንዳንድ አላዋቂዎች “ቤተ ክርስቲያን ስለ አገር ምን አገባት!” ሲሉ ይደመጣሉ። ይኸ አላዋቂነት ነው። ቤተ ክርስቲያን ስአገር ይገዳታል! ። ቤተ ክርስቲያን ስለ ኢትዮጵያ ትጮኃለች! ። ቤተ ክርስቲያን “እኔን ብቻ ይድላኝ” አትልም ።

ቤተ ክርስቲያን አግላይ አይደለችም። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማንኛውንም ሰው በግድ እና በዱላ እንዲሁም በሰይፍ እና በዛቻ በማስገደድ ወደራሷ በረት አታመጣም! ። እርስት ጉልት እየሰጠች በመደለል ፣ በጋብቻ አስገድዳ ክርስቲያን አታደርግም ። “ክርስቲያን ልሁን” ላለ ማንኛውንም ሰው በፍቅር ስባ ታጠምቃለች ። ይኸንን ያላወቁ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ላይ ክፉ ስራ እየሰሩ ነው ። እሷን እና ምዕመናኖቿን ለማጥፋትና ለመግደል ቢያድቡም ሞት ግን ክርስቲያኖችን አስደንግጦ አያውቅም! ። የማንንም መብት አለመንካት የዘወትር ተግባራችን ነው ።
ኢትዮጵያ የጋራ አገራችን ናት! ።
የእኔ እገሌ ብቻ የምትባል አይደለችም ።

“ኦርቶዶክስን የነፍጠኞች ሃይማኖት ናት!” የሚሉ አሉ። ይኸ ፈጽሞ የተሳሳተ አነጋገር ነው። ኦርቶዶክስ የአማራው የኦሮሞው የአፋሩ የጋምበቤላው የቤንሻንጉሉ የከንባታው … የሁሉም ናት። ነገር ግን በዘመናች በኃይል የሚመኩ! ፣ በነፍጣቸው የሚመኩ ካሉ እራሳቸውን ወደ እግዚአብሔር ዝቅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ቤተ ክርስቲያን ላይ የመከራ ጭንቅን ማድረጋችሁን አቁሙ! ። ክርስትናችን አንገታችንን እንድንደፋ አድርጋን እንጂ ለወኔ ለወኔማ ኦርቶዶክሳዊያን ያውቁበታል።

የሚወዛወዝ እጅ ስለሌለን አይደለም እጃችንን በአጠቁን ሰዎች ላይ የማናነሳው ። አንድ ሰው ከጮኸ ሰላማዊ ነው ። “ኦርቶዶክስ የአማራ ስለሆነች ነው እዚያ አካባቢ የሚጮኸው” የሚሉ ደካማ ሰዎችንም እሰማለሁ ። ተዋህዶ የሁሉም ናት! ። እንኳን የሚያምነው ቀርቶ የማያምንባትም ሙስሊምም ሆነ ፕሮቴስታንት ስለቤተክርስቲያን መከራና ጭንቅ ሊገደው ይገባል ።

ለጠቅላይ ጠቅላይ መኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጀመሪያ ሲነሱ ስለተዋህዶ በየትኛውም ቦታ በሄዱ ቁጥር ሲመሰክሩላት ታይቷል ። እዚያና እዚኸ የነበረውንም አሰታረቀዋል ። የተወሰዱባትን ሕንጻዎችም አስመልሰዋል ። በዚኸ በኩሉ አመሰግጋቸዋለሁ ። ነገር ግን አሁን ላይ ያ! ትጋቸው ተቋርጧል ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ እገዛ እስከመጨረሻው መዝለቅ አለበት ። ለምን ተቋረጠ!? ። አሁንም አሁንም ኢትዮጵያን እንደጠሩ በዚያ እንዲቀጥሉ እንሻለን ። ካጠገባቸው ሆነው የሚጎረብጧቸው ሰዎችም ካሉ ይንገሩንና እስከ እቅታ ድረስ አብረን እንታገላቸዋለን ።

ወጣቶች አደራ የምላችሁ ማንኛውም ነገር ለመስራት ከአባቶቻችን በተዋረድ በመታዘዝ ይሁን ። እነሱን በተዋረድ እንስማ ። ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያዘንን አድርጉ የሚለንን እንከተል ። አንዳንድ ጊዜ ሞቅ የምንል አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የምንበርድ መሆን የለብንም! ። ወታደር ትጥቁን አይፈታም ። ክርስቲያኖችም የጸሎትና የትጋት ትጥቃችሁን አትፍቱ ። አብረን እንሰራለን ። በርቱ ። አብረን እንሮጣለን ። አብረን ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልዕልና እስከ መስዋዕትነትም ድረስ ቢሆን እንሰራለን ።

እንደ ባሕር ዳር ከተማማ የደረሰብን ምንም ነገር የለም ። ቤተ ክርስቲያን ግን አንዲት በመሆኗ እዚያ የተጠቃችው የቤተ ክርስቲያን ጥቃት የእኛም ጥቃት ነው ። ወደፊትም ዛሬም ስለቤተ ክርስቲያናችን እንዲሁም ስለኢትዮጵያ እንጮኃለን ። ጉባኤም እየሰራን አብረን ግንዛ እንጨብጣለን ። በሰላማዊ መንገድ መብታችንን እንጠይቃለን ። በመንፈሳዊነታችሁ በርቱ ። እንደ ዛሬው ሁሉ መስቀል ደርሷልና በደነሸብ አድርገን እንድናከበር ይሁን ።

አባ አብርሃም
ሊቀ ጳጳስ