የጎዳና ወሲብና ልመና ሕዝቡን ለማሕበራዊ ቀዉስና ለአደጋ እያጋለጡ ስለሆነ በሕግ ሊታገዱ ነዉ።

DW : የአዲስ አበባ መስተዳድር የጎዳና ዉሎ አዳሪነትን፣ የጎዳና ወሲብና ልመናን በሕግ ሊያግድ ነዉ። መስተዳድሩ ባረቀቀዉ ደንብ እንደሚለዉ የጎዳና ዉሎ አዳሪነት፣ ወሲብና ልመና እየተስፋፉ በመምጣታቸዉ የነዋሪዎች ሰብአዊ መብት እየተጣሰ፣ ሕዝቡን ለማሕበራዊ ቀዉስና ለአደጋ እያጋለጡ ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ዉይይት እየተደረገበት ነዉ።አዲስ አበባ ዉስጥ እስከ መቶ ሺሕ የሚደርሱ የጎዳና ላይ ለማኞችና አዳሪዎች ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል።የመንገድ ላይ ሴተኛ አዳሪዎች ቁጥር ደግሞ በ10 ሺሕ ይቆጠራል።