ጎጃም ደቡብ ሜጫ ወረዳ ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል

በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ ሜጫ ወረዳ የመንግሥት ኃይሎች ከጥቅምት ወር መግቢያ ጀምሮ ፈጸሟቸው በተባሉ ጥቃቶች ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ዓይን እማኞችንና ነዋሪዎችን በመጥቀስ ዘግቧል።

ጥቅምት 1 እኩለ ቀን ላይ በወረዳው ዋና ከተማ ገርጨጭ መሃል ገነት ጤና ጣቢያ ላይ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች፣ አንድ የዘጠኝ ዓመት ሕጻንንና የጤና ባለሙያን ጨምሮ ስምንት ሰዎች እንደተገደሉ ከነዋሪዎች መስማቱን ዘገባው አመልክቷል።

ከጥቃቱ ከሰዓታት በኋላ በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ግጭት መካሄዱንና የመንግሥት ኃይሎች ቤት ለቤትና መንገድ ላይ በርካቶችን “እንደረተሸኑ” መረዳቱንም ዜና ምንጩ ጠቅሷል።

ኢሰመኮ፣ ስለግድያዎቹ ሪፖርቶች ደርሰውት መረጃ እያሰባሰበ እንደኾነ ተናግሯል ተብሏል።