Blog Archives

የዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በፋኖ ላይ ዘመቻ ለምን? / ከዐብይና ከኮ/ል ደመቀ ማንን ይመርጣል?

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

አዳነች አቤቤ የጣራና ግድግዳ ግብርን በተመለከተ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ተዘባብተው የሕግ የበላይነትን ደፍጥጠዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ ስልጣን ያለው መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ ፤ በፍርድ ቤት በተያዘው ጉዳይ ላይ መዘባበታቸው የሕግ የበላይነት መደፍጠጡ ምስክር ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ያለው ሲሆን፣ ይህን ግብር ከመሰብሰብ የሚከለክል ምንም አይነት ህጋዊ አካል እንደሌለ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል። ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እየተካሄደ ባለበት ወቅት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። ከንቲባዋ የጣራና የግድግዳ ግብርን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ የጣራና የግድግዳ ግብር አዋጅ በ1968 ዓ.ም የወጣ አዋጅ መሆኑን አስታውሰዋል። በወቅቱ የነበረው አሰራር አሁንም እንደቀጠለ ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ ነገር ግን የተለወጠው ወቅቱን ያገናዘበ የዋጋ ተመን ብቻ ነው ብለዋል። በተጨማሪም አዋጁ ሲወጣ የነበረው የኪራይ ዋጋ እና አሁን ያለው የኪራይ ዋጋ እኩል ባለመሆኑ አሁን የጨመረው ኪራዩ መሆኑን ጠቁመዋል። የከተማ አስተዳደሩ የሚያስከፍለው ግብር ግን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን ለመኖሪያ ቤት የዋጋውን ግማሽ እንዲሁም ለንግድ ቤቶች 75 በመቶ ብቻ እንደሆነ ከንቲባዋ አብራርተዋል። በከተማዋ በግብር ስርዓት ውስጥ ያልነበሩ በርካታ ነዋሪዎች እንደነበሩ ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች፣ በከተማዋ ካሉ 800 ሺህ ህንጻዎችና ቤቶች ግብር ይከፍሉ የነበሩት 120 ሺህ ብቻ እንደነበሩ ገልጸዋል። ይህ የፍርድ ቤት ጉዳይን በመጣስ ስልጣናቸውን ተጠቅመው የደነፉት ከንቲባ የሕግ የበላይነት እንዳሌለ አስመስክረዋል።  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲስ አበባ ሰሞኑን የተከሰቱት ምንድን ናቸው?

አዲስ አበባ ሰሞኑን የተከሰቱት ምንድን ናቸው? https://mereja.com/amharic-v3/794
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News, Video

በሜታ ወልቂጤ በአንዲት ታዳጊ ህጻን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ

በሜታ ወልቂጤ በአንዲት ታዳጊ ህጻን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስቅሷል። “በኛ የደረሰ በማንም አይድረስ” የሚሉት የተጎጂ ቤተሰብ በታዳጊ ልጃቸው ላይ ለደረሰው ቀሰቃቂ ወንጀል ፍትህ እንሻለለን ብለዋል። ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች፡፡ የስምንት (😎 ዓመት ታዳጊ ህጻን ናት፡፡ የአንደኛ ክፍል ተማሪ፡፡ በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት ባለፈ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ተመልሳ ምሳ እንደበላች ከመኖሪያ ቤቷ የደረሰችበት ሳይታወቅ ቀርቷል ፡፡ በዕለቱ ፍለጋ የወጣው ቤተሰብ ታዳጊዋን ከነሙሉ ጤንነትና በህይወት ለማግኘት ግን አልታደሉም፡፡ ሮጣ ያልጠገበች ታዳጊዋ ለአዕምሮም በሚከብድ ሁኔታ ከተደፈረች በኋላ “እንዳትናገር በሚል” ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ በቅርብ ርቀት ላይ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን አንድ የቤተሰቧ አባል ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ታዳጊዋ ከተገደለች በኋላ ተሰቅላ መገኘቷን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ “ጫማዋን ያወለቁባትና የሰቀሏት ቦታ አንድ አይደለም የ50 ሜትር ገደማ ርቀት አለው” ብለዋል። በወረዳው የኤላ ከተማ በታዳጊዋ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አባት የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸው እና በስራ ቦታ መሆናቸው እንዲሁም እናት የ2 ወር እመጫት በመሆናቸው አጋጣሚውን በመጠቀም እንደነበር የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል። የተጎጂ ቤተሰብ አባል የሆኑት አስተያየት ሰጪ ቀጥለው፤ “የታዳጊዋ ቤተሰብ ቤት በፊት ለፊት በኩል ሆቴል በመሆኑ የሚገባውና የሚወታው ብዙ ነው፡፡ በጓሮ በኩል ፑል መጫወቻም አለ፡፡ ደፋሪዎችም በዚያው በጀርባ በር እንደወሰዷት ነው የቤተሰብ ስጋት” ያሉን አስተያየት ሰጪው፤ 2009 ዓ.ም. የተወለደችው ታዳጊዋ ሲምቦ ገና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) አዳዲስ ምልምል ሰራዊት አስመረቀ!

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) አዳዲስ ምልምል ሰራዊት አስመረቀ! የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ልጅ እያሱ ኮር ቤተ-አምሓራ ክፍለጦር በሚንቀሳቀስበት ቀጠና ለበርካታ ወራቶች ያሰለጠናቸዉን ፋኖዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ::Image ቤተ-አምሓራ ክፍለጦር በሞያቸው የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች ከእግረኛ እስከ መካናይዝድ ለወራቶች ያሰለጠናቸዉን በርካታ ምልምል ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል:: ተመራቂ ፋኖዎችም የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማስከበር በቅንነትና በታማኝነት እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ እንደሚፋለሙ ቃል እየገቡ ወደ ግንባር ገብተዋል:: የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማስከበር በሚደረገው የፖለቲካ ትጥቅ ትግል በርካታ ዉጤቶች እየተመዘገበ ያለ ሲሆን ይህንን ዉጤት ለማስቀጠልና ትግሉን ለድል ለማብቃት ሰራዊቱን በሰው ሃይል ማጠናከርና ማብቃት ወሳኝ በመሆኑ ስልጠናዎችን አጠናክረን እናስቀጥላለን። በመጨረሻም ይህንን የተሳካ ስልጠና እንድናደርግ ገንዘብ ብሎም ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደረጋችሁልን በዉጭም በዉስጥም ያላችሁ ወገኖቻችን በአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ልጅ እያሱ ኮር ስም እናመሰግናለን:: “ሰልጥነን እንዋጋለን፣ እየተዋጋን እንሰለጥናለን!” “ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን” የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ልጅ እያሱ ኮር ቤተ-አምሓራ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ጥር 24/2017 ዓ.ም. Image Image Image Image  
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብን በቀጣዩ ምርጫ የመሳተፍ አቅም አይኖረውም

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) 300 የሚደርሱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹ በሥራ ላይ ባለመኾናቸው በቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ የመሳተፍ አቅም አይኖረውም ሲሉ አንዳንድ አባላቶቹ ለዋዜማ ተናግረዋል። ከፓርቲው አባላት የተወሰኑት መንግሥትን ለመግልበጥ ሙከራ አያደረጋችኋል ተብለው ለ6 ወራት ከታሠሩ በኋላ፣ ባለፈው ሳምንት እንደተፈቱም በዘገባው ተመላክቷል። አብን መጋቢት 11 ቀን፣ 2014 ዓ፣ም በባሕርዳር ከተማ ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ጉባኤው በድጋሚ እንዲካሄድ ቦርዱ ቢያዝም፣ እስካኹን ድረስ ፓርቲው ጉባኤውን ማካሄድ አልቻለም። የፓርቲው አመራሮች ከምርጫ ቦርድ ጋር ያላቸው ንግግር በግልጽ የማይታወቅ መኾኑ፣ የፓርቲውን ሕልውና አሳሳቢ እንዳደረገው አባላቱ ገልጸዋል። የአብን አባላት በፓርቲው ወቅታዊ ቁመና ዙሪያ ላነሱት ቅሬታ፣ የፓርቲው አመራሮች ምላሽ እንዲሠጡ ዋዜማ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካም አስታውቋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እንደማይሳተፉ ገለፁ

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ እንደማይሳተፉ ለዋዜማ ገልጸዋል። ፓርቲዎቹ በሂደቱ ላለመሳተፍ የወሰኑት፣ ኮሚሽኑ ገልጽነትና ገለልተኝነት ይጎድለዋል፤ ክልሉም ከድኅረ-ጦርነት ቀውስ ገና አልወጣም በማለት ነው። ሳልሳዊ ወያነ፣ የትግራይ ግዛቶች በሌሎች የታጠቁ አካላት እንደተያዙ መኾኑን ገልጦ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩም በሂደቱ ይሳተፋል ብሎ እንደማያምን አስታውቋል። ባይቶና እና አረና፣ አገራዊ ምክክሩ እስካኹን ባለው አካሄድ የአገሪቱን ችግር ይፈታል ብለው እንደማያምኑ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ሳልሳዊ፣ አረናና ባይቶና፣ እስካኹን ከኮሚሽኑ የደረሳቸው የተሳትፎ ጥሪ እንደሌለ ጠቁመዋል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሂደቱ ይሳተፍ እንደኾን ዋዜማ ለማረጋገጥ ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ተመድ አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ለርዕደ መሬት ጉዳት የተጋለጡ 85 ሺሕ ሰዎች ወደሌሎች አካባቢዎች አዛወርኩ አለ

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በአፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ለርዕደ መሬት ጉዳት የተጋለጡ 85 ሺሕ ሰዎች ወደሌሎች አካባቢዎች እየተዛወሩ መኾኑን አስታውቋል። ከተነሺዎቹ መካከል 55 ሺሕ ያህሉ ከአፋር ክልል ሲኾኑ፣ 30 ሺሕ ያህሉ ከኦሮሚያ ክልል እንደኾኑ ቢሮው ጠቅሷል። ቢሮው፣ በኹለቱ ክልሎች በጠቅላላው 90 ሺሕ ሰዎች ለርዕደ መሬት ጉዳት ተጋላጭ እንደኾኑ ጠቅሷል። በአፋር ክልል፣ ለተነሺዎች የተመረጡ የሠፈራ ቦታዎች እንዲቀየሩና ከስጋት ነጻ የኾኑ አዳዲስ የሠፈራ ቦታዎች እንዲለዩ የሠመራና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ እንደሠጡና ተነሺዎችም ወደ አዲሶቹ ሠፈራ ጣቢያዎች እንደሚጓጓዙ ተገልጧል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሱማሊያ ምን ይዞ እንደሚመጣ አላውቅም የሱማሊያው ፕሬዝዳንት

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሱማሊያ ምን ይዞ እንደሚመጣ ርግጠኛ መኾን እንደማይችሉ ከዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ኾኖም በፕሬዝዳንት ትራምፕ ዙሪያ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች አሜሪካ ለሶማሌላንድ የአገርነት እውቅና እንድትሠጥ እንደሚፈልጉ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ የአፍሪካ አገራት ድንበሮች የሚቀየሩ ከኾነ ትልቅ ችግር ይፈጠራል በማለት አስጠንቅቀዋል። ከአልሸባብ ጋር የሚደረገው ውጊያ አኹንም አስቸጋሪ እንደኾነ ያመኑት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን በድጋሚ የሱማሊያ ወታደሮችን ለማሠልጠን የተሠማሩትን የአሜሪካ ወታደሮች እንዳያስወጡ ጠይቀዋል። ይልቁንም በፕሬዝዳንት ትራምፕ የሥልጣን ዘመን አልሸባብን ለማሸነፍ አሜሪካ የወታደሮቿን ቁጥር እንድትጨምር እንደሚፈልጉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ገጣሚ እና የጦቢያ ግጥም በጃዝ ፕሮግራም አዘጋጅ ምስራቅ ተረፈ ለእስር ተዳረገች

ገጣሚ እና የጦቢያ ግጥም በጃዝ ፕሮግራም አዘጋጅ ምስራቅ ተረፈ ትናንት ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በፖሊስ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ ተብላ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደተወሰደች ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደጠቆሙት ምስራቅ ዛሬ ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ፖሊስ ምርመራ ለማጣራት ጊዜ እንዲሰጠው ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቅርቧት ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ምርመራውን አጣርቶ እንዲያቀርብ 7 ቀን በመስጠት ለጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ሰቷል፣ ምስራቅ ተረፈ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተመልሳለች። ምስራቅ የኪነጥበብ ምሽቶችን በሀገር ውስጥ እንዲሁም በውጭ ሀገራት በማዘጋጀት እንዲሁም የራሷን ግጥሞች በማቅረብ በብዛት ትታወቃለች። እንደ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ እና ገጣሚ ትእግስት ማሞ ያሉ የደመቁባቸውን ዝግጅቶች በማሰናዳት የምትታወቀው ግለሰቧ ግጥም፣ መነባንብ፣ ዲስኩር እንዲሁም ጥበብ እና ጥበብ ነክ ስራዎች ይበልጥ እንዲለመዱ እንደለፋች ብዙዎች ይናገራሉ። ገጣሚ ምስራቅ አሁን ላይ የታሰረችበት ምክንያት ምን እንደሆነ ግልፅ እንዳልሆነ ታውቋል። (መሠረት ሚድያ) Image
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአፋር ክልል በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በርካቶች ተገደሉ

🚨“ የሟቾች ቁጥር 8 ነው። ቁስለኞች ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ” – ነዋሪዎች ➡️ “ ጥቃቱ የድሮን ጥቃት ነው፡፡ የሟቾች ”ቁጥር እስካሁን ባለኝ መረጃ  ስምንት ነው” – ኤሊዳዓር ወረዳ በአፋር ክልል ኤሊዳዓር ወረዳ ሲያሩ ቀበሌ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት በአርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ ህፃናት  ሞትና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎችና ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ በሰጡን ቃል፣“ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 በላይ ደግሞ ቆስለው ዱብቲ ሆስፒታል ገብተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው ከወደ ጅቡቲ አቅጣጫ በመጣ ድሮን ነው ” ብለዋል። መረጃ አቀባይ ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ? “ ትላንት ሌሊት አካባቢ መጀመሪያ ሦስት ሰዎች ተገደሉ። ሦስቱንም ዱሮን ነው ያጠቃቸው። ከዚያ ዛሬ ጠዋት ሟቾቹን ሊቀብሩ የነበሩ ሰዎችን ዱሮን እንደገና መጥቶ ነው ያጠቃቸው። መጀመሪያ ሦስት ወንዶች የሞቱ ሲሆን፣ እንደገና መጥቶ ሦስት ጊዜ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ሦስቱ ከተገደሉ በኋላ ድሮን መጥቶ ሴቶችና ህጻናትን አታክ ተደረጉ። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ስምንት ነው። ቁስለኞች ደግሞ ከ10 በላይ ናቸው። ቁስለኞች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ዱብቲ ሆስፒታል ገብተው ነው የሚገኙት። ጥቃት የተፈጸመበት አካባቢ ድንበር ነው ለጅቡቲ። ድሮኑ በየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ይታውቃል። ይታያል ማለት ነው ከጅቡቲ እንደመጣ ይታወቃል። ‘ ጅቡቲን የሚቃወሙ ታጣቂ ኃይሎች አሉ ’ ብለው ነው ጥቃቱን የሚፈጽሙት። ከቁስለኞቹ ውስጥ የአስር አመት ህጻናት አሉ። ሴቶች አሉ። ዱብቲ ሆስፒታል እግሯና እጇ የተቆረጠች ልጅ አለች ” ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ “ የድሮን ጥቃት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ600 በላይ ቋሚ ሠራተኞቹ ጋር የገባውን ውል በማፍረስ በተናቸው

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ፣ ከ600 በላይ ቋሚ ሠራተኞቹ ጋር የገባውን ውል በማፍረስ ሠራተኞቹን በሌሎች አራት ስኳር ፋብሪካዎች ተበተኑ ። ሠራተኞቹ የተበተኑት፣ ፋብሪካው ያቋረጠውን ምርት በዚህ ዓመትም እንደማይጀምር ከተነገራቸው በኋላ እንደኾነ  ተናግረዋል። ሠራተኞቹ የተበተኑት፣ ወደ ወንጂ፣ መተሐራ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ኹለትና ቁጥር ሦስት ፋብሪካዎች ሲኾን፣ በፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የተመደቡት ግን በጸጥታ ስጋት ሳቢያ እንዳልሄዱ ተነግሯል። በዝቅተኛ እርከን የሚገኙ ሠራተኞች ደሞ የአራት ወር ውዝፍ ደምወዝ፣ የሥራ ማፈላለጊያና ጥቅማጥቅም ተሰጥቷቸው ተሰናብተዋል ተብሏል። በሌሎች ፋብሪካዎች ለተመደቡ ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው 6 ሺሕ ብር በብድር መልክ ክፍያ እንደተሠጠም ምንጮች ገልጸዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ለባርነት ጨረታ” ቀርባ የነበረችው ኢትዮጵያዊት 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናገረች

ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሊቢያ “ለባርነት ጨረታ ቀርባ” የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ነሒማ ጀማል ለአጋቾቿ 700 ሺህ ብር ተከፍሎ ነጻ መውጣቷን ተናገረች። በፎቶዎች እና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታይ የነበረችው ነሒማ በቤተሰቧ አማካይነት ገንዘብ ከኢትዮጵያ ተሰባስቦ ከተላከ በኋላ ከሁለት ቀናት በፊት አጋቾቿ ወደ ከተማ አምጥተው እንደለቀቋቸው አስረድታለች። ታግታ ከነበረችበት ስፍራ እሷን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቢኖሩም የተለቀቁት ገንዘብ የተከፈለላቸው “ውስን ሰዎች ነበሩ” ማለቷን ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ ገልጻለች፡፡ እንዱሁም በአሁኑ ወቅት በሊቢያ እንደምትገኛና “ከዚህ በኋላ ምን እንደሚፈጠር አላውቅም” ስትል ጭንቀት ላይ እንደሆነች ተናግራለች። ተማሪ የነበረችው ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ፣ በአዲስ አበባ በኩል ወደ በጎንደር በማምራት ከኢትዮጵያ በመውጣት ነበር ስራ አለ ተብላ ወደ ሊቢያ ያቀናችው። አዲስ አበባ የተዋወቃቻቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ወንዶች በሰሃራ በረሃ በውሃ ጥም ሕይወታቸው አልፏል ብላለች። ለሌሎች ስደትን አማራጭ ለሚያደርጉ “አገራቸው ውስጥ ቢቀመጡ ይሻላቸዋል፣ መንገድ ላይ በሽታ አለ፣ ሞት አለ፤ ብዙ ጓደኞቼ መንገድ ላይ ሞተዋል” ስትል መክራለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የገለልተኝነት ጥያቄ የተነሳባቸው አዲሱን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሹመት አስመልክቶ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባላት ምን አሉ?

አዲሱን የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሹመት አስመልክቶ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባላት ምን አሉ? የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሐሙስ ጥር 22፤ 2017 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዲስ ዋና ኮሚሽነር ሾሟል። ብሔራዊውን የሰብአዊ መብት ተቋም እንዲመሩ ስለ ተሾሙት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የፓርላማ አባላት አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል። 🔴 የአብኑ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እና የኢዜማው ዶ/ር አብርሃም በርታ የሰጡትን አስተያየት እና የአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ምላሽ ይህን ሊንክ ተጭነው https://youtu.be/tDX2wcAcfDA ያድምጡ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የነበረው ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙ እያነጋገረ ነው

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የነበረው ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙ እያነጋገረ ነው …. ” ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን እያስታወስኩ መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ ” – ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል። ኢሰመኮ ፥ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ?መሆኑን ከእነዚህም መካከል ፦ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፣ የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንደነበሩ አስታውሷል። ተቋሙን በተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፥ ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውሳዋል። የኢሰመኮን ኮሚሽነሮች እና ባልደረባዎች በመወከል ለዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከወዲሁ “ መልካም የሥራ ዘመን እመኝላቸዋለሁ ” ብለዋል። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የነበረው ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙ እያነጋገረ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጥበቃ የተነሳባቸው አካባቢዎች እና በአሜሪካ ያሉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ማድረግ ያለባቸው ግዴታዎች ( ጠበቃ ሙሉአለም ጌታቸው )

ጥበቃ የተነሳባቸው አካባቢዎች እና በአሜሪካ ያሉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ማድረግ ያለባቸው ግዴታዎች ( ጠበቃ ሙሉአለም ጌታቸው )በቅርብ የትራምፕ አስተዳደር ለስደተኞች እንደ መጠለያነት ያገለግላሉ የተባሉትን ቦታዎችን ማለትም እንደ ትምህርት ቤቶች፣ ቤተ ክርስቲያናት እና ሆስፒታሎች የመሳሰሉትን ለሠላሳ ዓመታት የህግ ከላለ የተሰጣቸውን አከባቢዎች የህግ ጥበቃቸውን የሚያነሳ ህግ አውጥቷል፡፡ ይሄ ውሳኔ በስደተኞች ማህበረሰብ ላይ ከባድ አንድምታ አለው። ቀደም ሲል እነዚህ ቦታዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ ቦታዎች ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡ ይህም ICE በእነዚህ ቦታዎች ላይ የፖሊስ እርምጃዎችን እንዳይወስድ የሚከላከል ነበር።እነዚህ ጥበቃዎች ከሌሉ ደግሞ ስደተኞች አሁን እንደ ሕክምና፣ ትምህርት እና ማህበራዊ ድጋፍ ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሊፈሩ ይችላሉ። በዚህ የስደተኞች ፖሊስ ለውጥ ምክንያት ግለሰቦች ከሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና መጠለያዎች ሊርቁ ስለሚችሉ ይህ ለውጥ ደግሞ የህዝብን ጤና እና ደህንነት ይጎዳል።ይሁን እንጂ ፖሊሲው የተሻረ ቢሆንም፣ ህጋዊ መብቶች በቦታቸው ይቆያሉ። ሁሉም ግለሰቦች፣ የስደት ሁኔታቸው ምንም ይሁን፣ አሁንም በአራተኛው እና አምስተኛው ማሻሻያ ህጎች የተጠበቁ ናቸው፡፡ ይህም ከህገ-ወጥ ፍተሻዎች ጥበቃ እና ያለመናገር መብትን ያረጋግጣል። ሆኖም የማስፈጸሚያ እርምጃዎች ቀደም ሲል ጥበቃ ወደ ተደረገላቸው ቦታዎች ሊራዘም ይችላል፡፡ እናም ከU.S. ድንበር 100 ማይል ርቀት ላይ የጉምሩክ እና ድንበር ጥበቃ CBP (ሲ.ቢ.ፒ) ተጨማሪ የመፈለጊያ/ፍተሻ ስልጣን አለው። ICE የግል ቦታዎችን ለመግባት የፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚያስፈልገው ቢሆንም ነገር ግን በህዝብ ቦታዎች ላይ እንደ ሎቢዎች፣ የመኪና ማቆሚያዎች እና የጥበቃ ክፍሎች ውስጥ የመግባት እና ሕጋዊ ያልሆኑ ስደተኞችን መያዝ ይችላል።የዚህ የፖሊሲ ለውጥ
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

የነዳጅ ዋጋ ካለበት እንዲጨምር አይ ኤም ኤፍ ለአብይ አሕመድ ምክረ ሃሳብ አቀረበ

የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ኹለተኛውን የኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ግምገማ በማጠናቀቅ ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ትናንት ተጨማሪ 248 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል። ድርጅቱ ለኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ባለፈው ሐምሌ ካጸደቀ ወዲህ፣ እስከ ትናንት የለቀቀው ብድር 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። መንግሥት ለማኅበራዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብሮች የሚሠጠው ድጎማ ከተጠበቀው በታች መኾኑን በግምገማ ሪፖርቱ የገለጠው ድርጅቱ፣ ለጉዳት ተጋላጭ ለኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሴፍቲ ኔት ድጋፎችን ማጎልበት ያስፈልጋል በማለት መክሯል። ድርጅቱ፣ የነዳጅ ዋጋ የመንግሥትን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊመልስ በሚችል ደረጃ መስተካከል እንዳለበትም ምክረ ሃሳቡን ለግሷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፌደራል መንግሥቱ ከሕወሓት ጋር ወደ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ድርድር እንዲገባ እንታገላለን

ሰሞኑን በመቀሌ የተዘጋጀው ሕዝባዊ ኮንፈረንስ፣ ፌደራል መንግሥቱ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት መሠረት ከሕወሓት ጋር ወደ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ድርድር እንዲገባ ለመታገል መወሰኑን ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመሩት የሕወሓት ክንፍ ኦ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በጦርነቱ በትግራይ ሕዝብ ላይ የደረሰውን ጉዳት በሽግግር ፍትሕ ስም የመሸፋፈን አካሄድ ሰፍኗል ያለው ኮንፈረንሱ፣ የሕግ ተጠያቂነት እንዲሠፍን ለመታገል እንደወሰነም ተገልጧል። የታጠቁ ኃይሎች ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ሳይወጡ፣ የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን የመበተን አካሄድ እንዲቆም በጽናት ለመታገል ኮንፈረንሱ ከመግባባት ላይ መድረሱንም መግለጫው ጠቅሷል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ አማካሪ ምክር ቤት በማቋቋም ሽፋን ሥልጣን ለመጠቅለል ያደርገዋል ያለውን ሙከራ እንደማይቀበልና ይልቁንም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከሥልጣኑ እንዲወርድ ኮንፈረንሱ የጋራ ውሳኔ ላይ እንደደረሰም መግለጫው አመልክቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጌታቸው ረዳ የሚመሩትን ጊዜያዊ አስተዳደር ከሥልጣን ለማንሳት ምቹ መደላድል ተፈጥሯል

በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ሕወሓት፣ ጌታቸው ረዳ የሚመሩትን ጊዜያዊ አስተዳደር ከሥልጣን ለማንሳት ምቹ መደላድል ተፈጥሯል ማለቱን ሪፖርተር ዘግቧል። የቡድኑ ከፍተኛ አመራር ፈትለወርቅ ገብረ እግዚያብሄር፣ ቡድኑ የክልሉ ጸጥታ አመራሮች በጊዜያዊ አስተዳደሩ ዙሪያ መግለጫ ከማውጣታቸው በፊት ከአመራሮቹ ጋር ለቀናት የዘለቀ ውይይት ማድርጉን ትናንት ባንድ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ጌታቸው የሚመሩት ቡድን በትግራይ ላይ ከፍተኛ ክህደት እየፈጸመ ነው በማለት በድጋሚ የከሰሱት ፈትለወርቅ፣ ጌታቸው ከሥልጣን ሊያነሳቸው የሚችለው ፌደራል መንግሥቱ ብቻ እንደሆነ በመግለጽ ላይ ናቸው በማለት ወቅሰዋል ተብሏል። ፈትለወርቅ ቡድናቸው በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን የያዙ አመራሮችን በራሱ ሹሞች የመተካት እንጂ ጊዜያዊ አስተዳደሩን የማፍረስ ዓላማ እንደሌለው መግለጣቸውንም ጋዜጣው ጠቅሷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብይ አሕመድ በመብት ተሟጋች በሲቪል ማኅበራት ላይ የጣለውን እገዳ እንዲያነሳ ውትወታው ቀጥሏል

ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን ጨምሮ በመብት ተሟጋች በሲቪል ማኅበራት ላይ በቅርቡ የጣለውን እገዳ እንዲያነሳና ሲቪል ማኅበራትን ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠብ ጠይቋል። መንግሥት በሲቪል ማኅበራቱ ላይ የወሰደው ርምጃ ከሲቪል ማኅበራት አዋጁ ጋር እንደማይጣጣም የገለጠው ድርጅቱ፣ ርምጃው መንግሥት የዘፈቀድ እስሮችን ጨምሮ ትችትን ለማፈን ሲያደርጋቸው የቆዩ ጥረቶች አንድ አካል ነው ብሏል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ መንግሥት የመብት ተሟጋቾችን ዒላማ ማድረጉን በአጽንዖት እንዲቃወሙትና የኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች በተለይም አሜሪካና ፈረንሳይ ሲቪል ማኅበራት በአገሪቱ ላላቸው ሚና ድጋፋቸውን እንዲገልጡና እገዳዎቹን እንዲያወግዙም ድርጅቱ ጥሪ አድርጓል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትራምፕ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል የሚሰጠው የተመጣጠነ የምግብ ድጋፍ እንዲቋረጥ አደረገ

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦቶች እንዲቋረጡ ማዘዙን ተከትሎ፣ ዓለማቀፉ የረድኤት ድርጅት አክሽን አጌነስት ሃንገር በጋምቤላ ክልል በስደተኞች መጠለያዎች ለሚገኙ ስደተኞች የሚሰጠውን የተመጣጠነ የምግብ ድጋፍ ማቋረጡን ሮይተርስ ዘግቧል። ድርጅቱ ፕሮግራሞቹን እንዲያቆም ዓርብ’ለት ትዕዛዝ እንደደረሰውና ትዕዛዙን ተከትሎ፣ በሳምንቱ መጨረሻ እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለኾኑ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ሕጻናትና እናቶች የተመጣጠነ ምግብ የሚያቀርብባቸውን ማዕከላቱን ለመዝጋት ዝግጅት እያደረገ እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። ረድኤት ድርጅቱ እስካለፈው ታኅሳስ በነበረው የፈረንጆች ዓመት በከፍተኛ የምግብ እጥረት ለየተጎዱ በጋምቤላ በስደተኛ መጠለያዎች ለ3 ሺሕ ሕጻናት የተመጣጠነ የምግብ ድጋፍ አድርጎ እንደነበር. የዜና ምንጩ አውስቷል። የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የውጭ ዕርዳታ ለ90 ቀናት የማቆም ትዕዛዝ አስቸኳይ የምግብ ድጋፍን እንደማይጨምር የተገለጠ ቢኾንም፣ የትኞቹ አሜሪካ የምትሠጣቸው ድጋፎች በአስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ሥር እንደሚካተቱ ግን እስካኹን ግልጽ አልተደረገም።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላን እና የወታደራዊ ሂሊኮፕተር በአየር ላይ ተላትመው ተከሰከሱ።

በአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላን እና የወታደራዊ ሂሊኮፕተር በአየር ላይ ተላትመው ተከሰከሱ። አደጋው ያጋጠመው በዋሽንግቶን ዲሲ በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 3:00 ላይ ነው። የፒኤስኤ ንብረት የሆነው የበረራ ቁጥሩ 5342 የሆነና 60 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘው አውሮፕላን ሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ ኤርፖርት ለማረፍ በተቃረበበት ሰዓት ነው 3 የአሜሪካ ጦር አባላትን ከያዘ ወታደራዊ ሂሊኮፕተር (ብላክ ሀውክ) ጋር የተላተመው። አውሮፕላኑ እና ሂሊኮፕተሩ ‘ ፖቶማክ ወንዝ ‘ ላይ ነው የተከሰከሱት። አደጋውን ተከትሎ የነፍስ አንድ ስራ እየተሰራ ሲሆን የሬገን ኤርፖርት ለጊዜው የአውሮፕላን በረራ ማድተናገድ አቁሟል። የዲሲ ፖሊስ እስካሁን ስለ ሞቱ ሰዎች የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለና የነፍስ አድን ስራ ላይ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል። የአይን እማኞች ግጭቱ ሲፈጠር ከፍተኛ ብርሃን በአካባቢያቸው ታይቶ እነበር ጠቁመዋል። የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ” አሰቃቂ አደጋ ” ሲሉ ገልጸው የተሰማቸውን ሀዘን አካፍለዋል። ምክትል ፕሬዜዳንት ጄዲ ቫንስ ከአሰቃቂው አደጋ ሰዎች እንዲተርፉ ሁሉም በፀሎት እንዲተጋ ጥሪ አቅርበዋል። የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት በኤክስ ገጻቸው ላይ ” እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር ” ብለዋል። መረጃው ከኤስቢኤስ፣ ኒውስኤክስ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው። ቪድዮ ፦ avgeekjake
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሂጃብ ተፈቅዶላቸው፤ ኒቃብ እና ጥቁር ማስክ እንዳያረጉ የተከለከሉ የዲላ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትምሕርት ጀመሩ

“ በቋሚነት ይሁን ለጊዜው የተብራራ ነገር የለም፡፡ አሁን ግን ተማሪዎቹ ገብተው ትምህርታቸውን መማር ጀምረዋል ” – የዞኑ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በአለባሳቸው ሳቢያ ግቢ እንዳይገቡ በመከልከላቸው፣ ከትምህርት፣ ከካፌና ከማደሪያ ውጪ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡ ተማሪዎቹ በሰጡት ቃል፣ ” 44 ሴት ተማሪዎችን ጥቁር ማስክ አድርጋችሁ ‘አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” ነበር ያሉት። ለቅሬታው ምላሽ የጠየቅነው ዩኒቨርሲቲው፣ እንደ ሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ በሴኩላሪዝምና ብዝሃ ሃይማኖትን ተረድቶና አክብሮ የሚሰራ ተቋም እንደሆነና ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ እንዳልተከለከለ ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ እንደማይደረግ ገልጾ ነበር። ተማሪዎቹ ግቢ እንዲገቡ ተፈቀዳላቸው ? ወደ ግቢ ገባችሁ ወይስ አሁንም ከግቢ ውጪ ናችሁ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ተማሪዎቹ፣ ” ለጊዜው ከስምምንት ተደርሷል ” ሲሉ መልሰዋል። ” በተወካዮቻችን በኩል ኒቃብ፣ ማስክና ሂጃብ ለብሰን መግባት እንደምንችል ተነገረንና ትላንት ገብተናል ” ብለዋል። በስምምነቱ መሰረት ለብሰው እንዲገቡ ከመነገራቸው ውጪ ሌላ የተባሉት ነገር እንደሌለ አስረድተው፣ ” ለጊዜው ግን ግቢ ገብተናል ” ነው ያሉት፡፡ በደብዳቤ ጭምር በመጠየቅ ጉዳያቸውን ሲከታተል የቆየውን የጌድኦ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትንም ግቢ እንደይገቡ ተከልክለው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ግቢ ገብተዋል ? ስንል ጠይቀናል፡፡ የዞኑ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምን አለ ? ” በቋሚነት ይሁን ለጊዜው የተብራራ ነገር የለም፡፡ ግን ተማሪዎቹ ገብተው ትምህርታቸውን መማር ጀምረዋል፡፡ በዘላቂነቱ ላይ እንደ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ ‘እስካሁን የተፋጠነ ምላሽ አላገኘንም’ እያሉ ያሉ በችሎት ሁሌ ነው የሚያነሱት፤ በኛ እምነትም የተፋጠነ ፍትህ እያገኙ አይደለም ” – የእነ አቶ ክርስቲያን ጠበቃ

“ ‘እስካሁን የተፋጠነ ምላሽ አላገኘንም’ እያሉ ያሉ በችሎት ሁሌ ነው የሚያነሱት፤ በኛ እምነትም የተፋጠነ ፍትህ እያገኙ አይደለም ” – የእነ አቶ ክርስቲያን ጠበቃ እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለድ ትላንት የችሎት ቀጠሮ ነበራቸው። ጉዳዩን የሚከታተሉ የቅርብ ሰዎች፣ “የእምነት ክህደት ቃል ለመስጠት ነበር ትላንት ተዘጋጅተው የሄዱት ግን ያ ሳይሆን ቀርቷል” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። በዝርዝር ምን አሉ ? “ ትላንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ክሱን አሻሽሎ ይቀርባል ተብሎ ስለተጠበቀ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ይሰጣሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ሐምሌ 29/2016 ዓ/ም ላይ ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ከዛ ‘አሻሽዬ አላቀርብም ብሎ ይግባኝ’ ብሎ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀረበ። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ የስር ፍርድ ቤቱ የወሰነው ትክክል ነው ብሎ ባለፈው ሐሙስ በድጋሚ ክሱን እንዲያሻሸል ትዕዛዝ ሰጥቶት ነበር። በዚያ መሠረት ትላንት አሻሽሎ መጥቶ የእምነት ክህደት ቃላተቸውን ይሰጣሉ፤ ክሱም ይሻሻላል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ግን ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አሻሽሎ አልመጣምና አሻሽሎ እንዲመጣ ብሎ ረዘም ያለ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር ፍርድ ቤቱ። ነገር ግን አቶ ዮሐንስና አቶ ክርስቲያን ባቀረቡት ጠንካራ ክርክር ምክንያት ክሱ ተሻሽሎ መጥቶ ለጥር 29 የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ” ብለዋል። ስለትላንቱን የችሎት ውሎ ማብራሪያ የጠየቃቸው የእነ አቶ ክርስቲያን ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ “ ከአራት ወራት በኋላ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በማጽናት ነው ትላንት የቀረቡት ”
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የታጠቁ ግለሰቦች መቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው ነበር ተባለ

የታጠቁ ግለሰቦች መቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው ነበር ተባለ በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መሀል እየተካረረ የመጣውን ውዝግብ ተከትሎ በዛሬው እለት የታጠቁ ግለሰቦች የመቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው እንደነበር ታውቋል። ሙከራው የተካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ቡድን አባላት መሆኑን ነበር ፤  ሙከራው ግን ያልተሳካ ነበር ብለውታል። “ታጣቂዎቹን ወደ ሬድዮ ጣቢያው ይዞ የገባው በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን የተሾመ ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ የተባለ ግለሰብ ነው” ያሉት ምንጫችን ድርጊቱ ሲከሽፍ የኤፍኤም ሬድዮ ጣቢያውን ማህተም ይዘው ሲወጡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል። በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የሕወሓት ክንፍ አባል የኾነው ግለሰብና ታጣቂዎቹ፣ ከጣቢያው ሠራተኞች ማኅተም በመንጠቅ ሠራተኞችን ስብሰባ ጠርተው እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። ግለሰቡ ወደ ጣቢያው ያመራውና ውዝግብ የተፈጠረው፣ የደብረጺዮን ቡድን ለመቀለ ከተማ የሾማቸው ምክትል ከንቲባ ረዳኢ በርኸ ጣቢያውን እንድመራ ሾመውኛል በማለት እንደኾነ ተገልጧል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል የጅምላ እና የዘፈቀደ እስር ያቁም ! አምነስቲ ኢንተርናሽናል

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ውስጥ ይፈጽመዋል ያለውን “የጅምላ” እና “የዘፈቀደ” እስር ለማስቆም ዓለማቀፍ ግፊት እንዲደረግ ጥሪ አድርጓል። በክልሉ ውስጥ አኹንም የዘፈቀደ እስር ቀጥሏል ያለው ድርጅቱ፣ መንግሥት በዘፈቀደ ያሠራቸውን ዜጎች በሙሉ እንዲለቅ ወይም በይፋ ክስ እንዲመሠርት ጠይቋል። ድርጅቱ፣ የኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች እንዲሁም አሕጉራዊና ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በዘፈቀደ የታሠሩ ዜጎች እንዲፈቱ ተጽዕኗቸውን ተጠቅመው ግፊት እንዲያደረጉም ጥሪ አድርጓል። Ethiopia: Urgent international action needed to end mass arbitrary detentions in the Amhara Region As today marks four months since the launch of a state-led campaign of mass arbitrary detention of thousands of people in Ethiopia’s Amhara region in September 2024, Amnesty International’s Regional Director for East and Southern Africa, Tigere Chagutah, said: “The international silence over the mass and arbitrary detention of thousands of people in Amhara region is beyond shameful. Ethiopia’s development partners, as well as African and global human rights bodies, must use their influence to publicly call for the release of all arbitrarily detained people. The world must stop turning a blind eye to Ethiopia’s human rights crisis as the Ethiopian government continues to trample on the rule of law. “Keeping thousands of people locked up for months without charge or trial is a travesty of justice and
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ፋኖ ነን የሚሉ መንግስት ያስታጠቃቸው ታጣቂዎች መምሕራንን እና ተማሪዎችን እያገቱ ነው።

በጎጃም አካባቢዎች በመምህራንና ተማሪዎች ዕገታ ምክንያት ዘንድሮ ማስተማር ጀምረው ያቆሙ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንና በርካታ ተማሪዎች በወላጆች ላይ በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ሳቢያ ትምህርት እያቋረጡ ነው። በርካታ የገጠር ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና የትምህርት ተቆጣጣሪዎች በየጊዜው ፋኖ ነን በሚሉ ታጣቂዎች ይታገታሉ ። እነዚህ ፋኖ ነን የሚሉ ታጣቂዎች የታጠቁት መሳሪያ በመንግስት የተደራጁ ናቸው የሚሉ መረጃዎች በሕዝቡ ዘንድ ይነገራል። ባንዳንድ አካባቢዎች ዕገታውን በመፍራት ወደ ትምህርት ቤት የማይገቡ መምህራን ደሞ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንደሚታሠሩ ምንጮች ገልጸዋል። በክልሉ የዚህ ዓመት የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ድረስ መራዘሙን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ትናንት አስታውቋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ተደራጅተው የጦር መሳሪያ እንዲገዙ ግዳጅ ተጣለባቸው

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች አንድ ለአምስት ተደራጅተው የጦር መሳሪያ እንዲገዙና የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁ የመንግሥት መዋቅሮች ጫና እያደረጉ መኾኑ ታውቋል። በተለይ አርሶ አደሮች በቡድን ለሚገዙት የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ፣ በአንድ አባውራ እስከ 10 ሺሕ ብር እንዲያዋጡ እየተገደዱ መኾኑን ምንጮች ተናግረዋል። መዋጮውን የማይከፍሉ ነዋሪዎች በእስራት እንደሚቀጡ የገለጡት ምንጮች፣ መዋጮውን የሚሰበስቡት የቀበሌ መዋቅሮች ናቸው ብለዋል። ኾኖም ለመሳሪያው መግዣ ገንዘብ የሚያዋጡ ነዋሪዎች፣ ሕጋዊ ደረሰኝ እየተሠጣቸው እንዳልኾነ ለማወቅ ተችሏል። የግዴታ መዋጮው በተለይ በምዕራብ ወለጋ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በቄለም ወለጋና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰማያዊ አብዮት በአዲስ አበባ እና የግንባር መረጃዎች

Posted in Amharic News, Ethiopian News, Video

ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ጠቅላላ ጉባኤው የከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ሊያካሄድ ነው

ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ጠቅላላ ጉባኤው የከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ሊያካሄድ ነው ከመጪው አርብ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚካሄደው የገዢው ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ፤ ፓርቲውን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች እንደሚመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ። ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚሁ ጠቅላላ ጉባኤ፤ የፓርቲው ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ እንደሚካሄድ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከአርብ ጥር 23 እስከ እሁድ ጥር 26 በአዲስ አበባው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በሚካሄደው በዚሁ ጠቅላላ ጉባኤ፤ በፓርቲው ፕሮግራም እና ደንብ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች የሚጸድቁበት እንደሆነ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ባለፈው ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች አፈጻጸም በአሁኑ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚገመገም አቶ አደም ተናግረዋል። እስከሚቀጥለው ጉባኤ ድረስ ፓርቲውን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮችም በዚሁ ጉባኤ ላይ እንደሚመረጡ አቶ አደም አክለዋል። በሁለተኛው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ፤ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ምርጫ እንደሚካሄድ ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ከእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች በተጨማሪ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ በተመሳሳይ መልኩ እንደሚካሄድ ምንጮቹ ገልጸዋል። የፓርቲው የኢንስፔክሽን እና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን አባላትም በዚሁ ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚመረጡ ምንጮች አክለዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዐማራን ሕዝብ ትግል ለማጨናገፍ አንደራደርም/ከነ ዘመነ ከነ ዝናቡ ጋር ተስማምተን ነበር/የአፈ ሙዝ ድል በዲፕሎማሲው ተደግሟል!

Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News, Video

ከመንግስት ጋር ለመደራደር የተዘጋጀው የፋኖ ክንፍ ንግግሩ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ

ከመንግስት ጋር ለመደራደር የተዘጋጀው የፋኖ ክንፍ ንግግሩ በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ (መሠረት ሚድያ)- ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ አልያም በአሜሪካ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል። መንግስት በዋናነት በእስክንድር ከሚመራው የፋኖ  ክንፍ  ጋር በቅርቡ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ እንደተወያየ እስክንድር ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልፆ ነበር። አክሎም በድርድሩ ላይ የኢጋድ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ ተወካዮች መገኘታቸውን ገልፆ ነበር። በውይይቱ ላይ በፋኖ ክንፉ በኩል የተነሱ ነጥቦች መከላከያ አካባቢውን በግዜያዊነትም ቢሆን ለቆ መውጣት፣ ክልሉን ማስተዳደር፣ በፌደራል መንግስቱ በስልጣን መወከል፣ የድሮን ጥቃት ማቆም፣ ለተጎዳው ህዝብ ለህይወት ሳይቀር ካሳ መክፈል እና የመሳሰሉት ናቸው ተብሏል። በመንግስት በኩል ደግሞ ትጥቅ በመፍታት ወደ ማሰልጠኛ መግባት፣ ጎጃም አካባቢ ላይ ያለውን ነገር ማስተካከል፣ በየከተማው ያለውን አደረጃጀት መረጃ መቀበል፣ ተጠያቂ የሚሆኑ አባላቱን አሳልፎ መስጠት እንዲሁም በምክክር ኮሚሽኑ ውስጥ መካተት ናቸው ተብሏል። “በመንግስት ዝግ ስብሰባ ላይ ሲያጨቃጭቅ የነበረው የነእስክንድር ክንፍ አቅም ጉዳይ ሲሆን ግምገማውም በሀገር ውስጥና በውጭ ተቀባይነትን ለማግኘት መነጋገሩ እንደ  አማራጭ ተወስዷል” ያሉን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጫችን ሸዋ ላይ ድርጅቱ የተሻለ አቅም እንዳለው፣ ነገር ግን ጎጃም ላይ የለም የሚባል ደረጃ ላይ እንደደረሰ መረጃ ቀርቦ ንግግር ተደርጎበታል ብለዋል። “ቢያንስ ሸዋን ማቃለሉ እንደ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በመንግስትና በተወሰኑ የፋኖ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የተደረገው የመጀመሪያው የድርድር ማመቻቸት ሙከራ የተሳካ ነበረ

ዋዜማ፡ በመንግስትና በተወሰኑ የፋኖ ታጣቂ ቡድኖች መካከል የተደረገው የመጀመሪያው የድርድር ማመቻቸት ሙከራ የተሳካ እንደነበረ በጉዳዩ የተሳተፉ የዲፕሎማቲክ ምንጭ ለዋዜማ ተናግረዋል። ስለውይይቱ ዝርዝር ይዘትና አንዳንድ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ መረጃዎችን መናገር እንደማይፈልጉ የገለፁት የዲፕሎማቲክ ምንጫችን ከፋኖ ታጣቂዎች አንድ አንጃ ከወከላቸው አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል። ከሌሎች ሁለት የፋኖ አንጃዎች ጋርም ውይይት ለማድረግ ጅምሮች መኖራቸውን ግን ደግሞ በውይይቱ ለመግፋት መደነቃቀፎች እንዳጋጠሙ ከምንጫችን ተረድተናል። ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት የመጀመሪያው የድርድር ቅድመ ውይይት የተካሄደው በአቶ እስክንድር ነጋ ከሚመራው “የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት” ተወካዮች ጋር እንደነበረ መረዳት ችለናል። የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የአፍሪቃ ሕብረትና የኢጋድ ተወካዮችን ያካተተው የዲፕሎማቲክ ልዑካን “የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት” ተወካዮችን ያነጋገረው በመንግስት ዕውቅናና ታጣቂዎቹ በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ተገኝቶ መሆኑን መሆኑንም ተገንዝበናል። የዲፕሎማቲክ ቡድኑ ሁሉንም የፋኖ ታጣቂዎች አንድ ላይ ለማነጋገር ፍላጎት ቢኖረውን ለውይይቱ ፍላጎት ካሳዩና ተወካዮቻቸውን ካሳወቁ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ተሳትፏቸውን ያቆሙ አንጃዎች መኖራቸውን ያሰባሰብነው መረጃ ያመለክታል። አንዳንድ አንጃዎች ጉዳዩ መልክ እስኪይዝ ድረስ ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት በምስጢር እንዲያዝ እንደሚፈልጉም አመልክተዋል። በመንግሥት በኩል የፋኖ ታጣቂዎች አንድ ሆነው ለድርድር መቀመጥ ካልቻሉ በተናጠልም ቢሆን የድርድርን ሀሳብ ከተቀበሉ ቡድኖች ጋር ለመደራደር ፍላጎት እንዳለው ቀደም ብሎ ማሳወቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ በኩል የተናጠል ንግ ግሩ የክልሉን ግጭት ማስቆም ይችል እንደሆነ ገምግሞ ስለ ቀጣይ ድርድር ውሳኔ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ስምተናል። የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የፋኖ ታጣቂዎችን ለማነጋገር ፍላጎት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንበረ ፓትሪያርክ የተሰጠ መግለጫ

“የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሠራ ነው” ======== ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ፣ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት፣ ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል። ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮዋን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣ በሊቃውንቷ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣ የሥነ ሥዕል፣ የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተ ክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣ በአስተምህሮዎቿ፣ በዕምነቷ፣ በንዋያተ ቅድሳቷ ላይ መሠረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል። ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቷን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው አንግበው የአማራን ሕዝብ ለዳግም ባርነት ለመዳረግ በሞቱ የሚደራደሩ የአይሁድ ሸንጎ ማኅበርተኞችን ትናንት በአደባባይ ሕዝባችንም ሠራዊታችንም የተመለከተው የአደባባይ ሐቅ ነው። የብልጽግና ሥርዓት በቅብብሎሽ የተረከበውን አማራ ጠልነት አተልቆ፣ አደርጅቶ፣ አጎምርቶ በሰው ልጆች ታሪክ ታይቶ ተሰምቶ የማያውቅ እልቂት በአማራ ሕዝብና በአማራዊ ማንነት ላይ ውርጅብኝ በሆነበት በዚህ ሰዓት ላይ የአርበኝነት፣ የሕቅና የፍትሕ ትግላችንን በድርድር ሰበብ ለማይጠረቃ የፖለቲካ ፍትወታቸው መወጣጫ መሰላል ለማድረግ የሚሞክሩ አካላትን ለሠራዊታችንና ለሕዝባችን መግለጥ እንወዳለን። ከፋፋይነት፣ ይሉኝታ የለሽ ነጣቂነት፣ ልጓም አልባ የሥልጣን ፍትወት ላይ የሚናውዙ አካላት ትግላችንን ትናንት በሕዝባዊ ግንባር፣ ሕዝባዊ ሠራዊት፣ ፋሕፍዴን ዛሬ ላይ ደግሞ በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ጭንብል ተሸፍነው ትግላችንን ለማቃለል፣ ለማሳነስ የሄዱበት ርቀት እጅጉን አሳዝኖናል። በደቡብ ወሎ ዞን፣ ዳውንት ወረዳ ልዩ ቦታው ኩርባክ በተባለ ቦታ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋና የወሎ የፋኖ ተወካዮች በሚል ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከኢጋድ፣ ከአብይ አሕመዱ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ንግግሮች መደረጋቸውን ከሂደቱ ጀምሮ በየተቋሞቻችን የመረጃና ደኅንነት ዘርፎቻችን በኩል ስንከታተለው የቆየነው ጉዳይ መሆኑን ሳንገልጽ አናልፍም። እሚገርመው ደግሞ እነዚህ አካላት ድርድሩን ሚዲያ ላይ ወጥተው በመሪያቸው በአቶ እስክንድር ነጋ እና በፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊው በረ/ኘ/ር ጌታ አስራደ በኩል ገልጸውልናል። በዚህ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብና ጥቁር ማስክ እንጂ ሂጃብ እንዳይለብሱ አልተከለከለም፤ ሀሰተኛ መረጃ ነው

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት የእስልምና እምነት ተከታይ / ሙስሊም ተማሪዎች ” በሃይማኖታዊ አለባበሳችን ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳንገባ ተደርገናል በዚህም ምክንያት በሁለት መስጊዶች ተጠልለን እንገኛለን ” ሲሉ  ቅሬታቸዉን አድርሰዋል። ” በዩኒቨርሲቲው ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ አልተከለከለም ኒቃብ ደግሞ አስቀድሞም በዩኒቨርሲቲ አይደረግም ነበር ” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለዉም ” በተለያዩ ማህበራዊ  ሚዲያዎች ዩኒቨርሲቲዉ ‘ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ሂጃብ መልበስ ከልክሏል ‘ በሚል የሚሰራጨዉ መረጃ ትክክል ያልሆነ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” ሲሉ ገልፀዋል።  “ 44 ሴት ተማሪዎችን ‘ጥቁር ማስክ አድርጋችኋል አናስገባም’ ብለው፣ ኒቃብ የለበስን 7 ሴቶችንም ከልክለውን ውጪ አደርን ” – ሙስሊም ተማሪዎች “ የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው ” – ዲላ ዩኒቨርሲቲ  የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ፣ ጥቁር ማስክ እንዳይለብሱ በመከልከላቸው ከትምህርታቸው እየተስተጓጎሉ በመሆኑ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠንከር ያለ ስሞታ አቅርበዋል። የተማሪዎቹ ዝርዝር ስሞታ ምንድን ነው ? “ ኒቃብና ጥቁር ማስክ እንዳንለብስ ነው የተከለከልነው። ክልከላው የጀመረው ከአንድ ወር በፊት ነበር። በዚህም ማመልከቻ አስገብተን ነበር መልበስ እንዲፈቀድልን። ሆኖም ግን ምላሽ ሳይሰጠን ቆዬ። ትምህርታችን በስርዓት እንዳንከታተል አስተጓጎሉን። ቅዳሜ፣ አንዲት እህት ማስክ አድርጋ፣ ሂጃብ ለብሳ በምትገባበት ወቅት ኦዲያ ካምፓስ በሁለቱም በሮች እንዳትገባ ከልክለዋታል። እንዲያውም ወንዶቹ የግቢው ጥበቆች አስፈራርተው ፊቷን አስከፍተዋታል። እንደዛም ሆኖ ማስክ ለብሳ ወደ ግቢ መግባት እንደማትችል ነግረው መልሰዋታል። ቅዳሜ ከሰዓት ሁለት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“መንግስት የመብት ጥሰት የፈጸሙትንም ሆነ ያስፈጸሙትን መጠየቅ ይኖርበታል” ኢሰመኮ

“መንግስት የመብት ጥሰት የፈጸሙትንም ሆነ ያስፈጸሙትን መጠየቅ ይኖርበታል” ኢሰመኮ መንግሥት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙት የትጥቅ ግጭቶች፣ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች እና የሰብአዊነት ሕጎች ጥሰት የፈጸሙ እና ያስፈጸሙ ኃላፊዎችን  እና አባላትን እንዲሁም የታጣቂ ቡድኖች አባላት ተጠያቂ ለማድረግ መንቀሳቀስ ይኖርበታል ሲል ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡ የሰብአዊ መብቶች ደረጃን የሚያሟላ የወንጀል ምርመራ እና የክስ ሂደት እንዲጀመር፤ እንዲሁም በግጭቶቹ በሰው ሕይወት፣ በአካል፣ በሥነ-ልቦና እና በንብረት ላይ ያደረሱትን ጉዳት በማጣራት ተጎጂዎች እንዲካሱ እና መልሰው እንዲቋቋሙ እንዲያደርግ ሲል ኮሚሽኑ በመግለጫው ጠይቋል፡፡ በአማራና በኦሮሚያ ክልል “ከወቅታዊ ጉዳዮች” ጋር በተያያዘ በሚል የተያዙና ተአማኒ ክስ ያልቀረበባቸው ታሳሪዎች እንዲሁም በማስገደድ የተሰወሩና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ ወይም ጉዳያቸው በመደበኛው የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት እንዲታይ፣ የመንግሥት የጸጥታና የአስተዳደር አካላት በቁጥጥር ሥር የሚውሉ ሰዎችን በመደበኛ ማቆያዎች ብቻ እንዲይዙና የተያዙ ሰዎች ያሉበት ቦታና ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው እንዲገለጽም ብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም የታጠቁ ቡድኖችን ጨምሮ በ3ኛ ወገኖች ከእገታ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ፣ከዳኝነት ስራቸው ጋር በተያያዘ ያለፍርድ የታሰሩ ዳኞችና መሰል የፍትህ አካላትም በአፋጣኝ ፍትህ እንዲያገኙ ሲል ጠይቋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በየቦታው የሚፈፀሙ ግድያዎች ተባብሰው ቀጥለዋል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በየቦታው የሚፈፀሙ ግድያዎች ተባብሰው መቀጠላቸውን ጠቆመ። ኢሰመኮ በዚህ የሩብ ዓመት ሪፖርቱ ከመስከረም ወር አጋማሽ 2017 ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. አጋማሽ ያለውን ጊዜ የዳሰሱ ግድያዎችን እና አስገድዶ ስወራዎችን ዳስሷል። በቀጥታ እንዲህ ይቀርባል: በአማራ ክልል ከመስከረም 6 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ፣ ቀበሌ 18፣ አዲስ ዓለም፣ ገንፎ ቁጭ፣ ቆሸ ሰፈር፣ ፋሲል ካምፓስ፣ አማኑኤል፣ ሎዛ ማርያም፣ አጣጥ እና አዘዞ በተባሉ የከተማው አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) መካከል በነበረው የትጥቅ ግጭት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተጸፈመ ወታደራዊ ዒላማን ያልለየ የጦር መሣሪያ ጥቃት እንዲሁም በሁለቱም ወገን በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ሕፃናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ቢያንስ 10 ሲቪል ሰዎች እንደተገደሉና  በአካል እና በንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና የዐይን እማኞች ለማወቅ ተችሏል። ከአንድ ሆስፒታል  በተገኘ  መረጃ  ብቻ በግጭቱ ምክንያት 6 ሴቶች እና 6 ሕፃናትን ጨምሮ በአጠቃላይ 32 ሲቪል ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የሕክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን ከነዚህ መካከል 1 ሰው ሆስፒታሉ ውስጥ ሕይወቱ ያለፈ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ከመስከረም 6 እስከ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ዳባት ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት መካከል ከነበረው የተኩስ ልውውጥ ጋር በተያያዘ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ዒላማን ባልለየ የጦር መሣሪያ ምክንያት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲስ አበባ ውስጥ የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ባለቤቱ ላይ ለመስማት የሚከብድ እጅግ ዘግናኝ የወንጀል ድርጊት የፈጸመው ግለሰብ በሞት ተቀጣ። (ከፍትህ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ) ” የሰው ስጋን የከተፈው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት ” ይላል ይህ የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ። ተከሳሽ ግለሰቡ ፀሃዬ ቦጋለ በየነ ይባላል። ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት እራሷን እንድትስት ያደርጋል። በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት ያስገባታል። ከዛም አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ ሽንት ቤት ውስጥ ይጨምራል። የቆረጠውን እግሯም ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ 30/12/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ይቆያል። በኋላ ከ1/13/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/1/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ በመሰወሩ ምክንያት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ይጣራል። ግለሰቡም በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግም በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአማራ ክልልና በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ተከትሎ በሠላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃትና እንግልት እየደረሰ ነው

የአማራ ማኅበር በአሜሪካ፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ተከትሎ በሠላማዊ ዜጎች ላይ “ጥቃት” እና “እንግልት” እየደረሰ ነው ሲል መንግሥትን ወቅሷል። ጸጥታ ኃይሎች በበዓሉ ማግስት፣ በአዲስ አበባ፣ ባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ወልድያ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ቡሬና ደምበጫ “ከሕግ አግባብ ውጭ ግድያ፣ የአካል ጥቃት፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገድዶ መሠወር እና የንብረት ውድመት አድርሰዋል” በማለት ማኅበሩ ከሷል። በተለይ ወጣቶች ከሚታሠሩባቸው ምክንያቶች መካከል፣ በዘፈን ታዋቂ የፋኖ መሪዎችን “አወድሳችኋል” የሚል እንደሚገኝበት ማኅበሩ ገልጧል። ማኅበሩ፣ በተለይ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ “ማንነትን መሠረት ያደረጉ ግፎችና እና ስደቶች” እንዲኹም “የዕምነት ነጻነትን የማፈን ተግባሮች” ያሳስቡኛል ብሏል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር ያስከተለው ምስቅልቅል እና ምሬት

የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር ያስከተለው ምስቅልቅል እና ምሬት (መሠረት ሚድያ)- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በተለይ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻ ከተደረገ ወዲህ የኑሮ ውድነት ተባብሶ ቀጥሏል። የመገበያያ ዋጋቸው እጅግ እየጨመሩ ከመጡ ምርቶች አንዱ ነዳጅ ነው። የዛሬ ሁለት አመት በዚህ ወቅት ቤንዚን በሊትር 61 ብር ነበር፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ይሸጥ ነበር፣ ኬሮሲንም በሊትር 67 ብር ነበር። አሁን ላይ ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል፣ ናፍጣ ደግሞ በሊትር 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፣ በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል። ታድያ የዚህ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ የህዝብ ትራንስፖርቱ ዋጋም በእጅጉ እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል። በተለይ በተለይ በአዲስ አበባ ዳርቻ አካባቢዎች በሰፈሮችና በኮንዶሚኒየምዎች የሚኖሩ ዜጎች ለትራንስፖርት የሚያወጡት ወጪ እጅግ በጣም ጨምሮ ኑሮን እንዳከበደባቸው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። ለምሳሌ በኮዬ ፈጬ፣ በአራብሳ፣ በቂሊንጦ፣ በቱሉዲምቱ ወዘተ… የሚኖሩ ዜጎች ከነዚህ መኖሪያ መንደሮች እስከ መገናኛ እንኳን ለመድረስ በአውቶብስ 20 ብር፣ በታክሲ ደግሞ 50 ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል። “ወቅታዊ ታሪፉ ደርሶ መልስ በአውቶቡስ 40 ብር፣ በታክሲ 100 ብር ነው መገናኛ ድረስ ብቻ። እኛ ግን አልፈን ሄደን መሀል ከተማ ነው የምንሰራው፣ ለትራንስፖርት ብቻ በቀን እስከ 130 ብር በትሹ እናወጣለን” በሚል አስተያየት የሰጡት እነዚህ ዜጎች ይህንንም ለማግኘት ብዙ ተሰልፈው እና ተንገላተው እንደሆነ ያስረዳሉ። “ይሄ እጅግ በጣም ኑሮአችንን አክብዶብናል፣ ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል። አቤቱታችንን በሚዲያችሁ አስተላልፉልን፣ የሚመለከተው አካል መፍትሔ ሊሰጠን ይገባል” የሚሉት እነዚህ ዜጎች የነዳጅ ድጎማ
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የግብጽ ተሳትፎ፤ “የትኛውንም ሀገር የማስፈራራት ዓላማ” እንደሌለው አልሲሲ ተናገሩ

በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የግብጽ ተሳትፎ፤ “የትኛውንም ሀገር የማስፈራራት ዓላማ” እንደሌለው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ የግብጽ በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ውስጥ መሳተፍ “የትኛውንም ሀገር የማስፈራራት ዓላማ” እንደሌለው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ “የሶማሊያን ደህንነት እና መረጋጋት ለማስፈን” ያለመ ባሉት አዲሱ ሰላም አስከባሪ ውስጥ፤ የግብጽ “ተሳትፎ አዎንታዊ” እንደሆነ ገልጸዋል። አል ሲሲ በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት ዛሬ ሐሙስ ጥር 15 ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር በካይሮ ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ሐሰን ሼክ ወደ ካይሮ ያቀኑት በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተገናኝተው፤ የሶማሊያ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ በተስማሙ በ12ኛው ቀን ነው። ግብጽ እና ሶማሊያ ያላቸውን ግንኙነት ወደ “ስልታዊ አጋርነት (strategic partnership) ለማሳደግ የጋራ ፖለቲካዊ ቃል ኪዳን” እንደተፈራረሙ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ተደርጓል። በሶማሊያ ያለው ሁኔታ ግብጽን ከ30 ዓመታት በላይ ሲያሳስብ የቆየ እንደሆነ በዚሁ መግለጫ ላይ የጠቀሱት ፕሬዝዳንት አልሲሲ፤ ሀገራቸው በሰላም አስከባሪው ተልዕኮ ውስጥ የሚኖራት ተሳትፎ በዋናነት “ለሶማሊያ ህዝብ ያላትን አጋርነት ለማሳየት ያለመ” እንደሆነ አስረድተዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዲላ ዩኒቨርስቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ በመልበሳቸው ከትምህርት ታገዱ ሲል እስልምና ምክር ቤት አማረረ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዲላ ዩኒቨርስቲ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ በመልበሳቸው ከትምህርት እንደታገዱ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ትምህርት የማግኘት ሕገመንግሥታዊ መብታቸው ተገፎ ወደ ዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ የተከለከሉት ሴት ተማሪዎች ባፋጣኝ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ የጠየቀው ምክር ቤቱ፣ ትምህርት ሚንስቴር ለችግሩ ዘላቂ አስተዳደራዊ መፍትሄ እንዲሰጥ በደብዳቤ መጠየቁን ገልጧል፡፡ በአክሱም ከተማ በኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ ተመሳሳይ እገዳ ከተጣለ ወዲህ፣ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲበጅለት ለትምህርት ሚንስቴር ሦስት ጊዜ ደብዳቤ መጻፉን የጠቀሰው ምክር ቤቱ፣ ኾኖም እስካኹን ምላሽ አለማግኘቱንና ይህ ደብዳቤም የመጨረሻው መኾኑን አውስቷል።
Posted in Ethiopian News

ከአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ መግለጫና የአንድነት ጥሪ!

የእውነተኛ ወንድማማችነት ዋጋ ከአልማዝ ወይም ከወርቅ የበለጠ ውድ ነው! ከአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ መግለጫና የአንድነት ጥሪ! የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በመመስረቱ የተሰማነን ታላቅ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን፣ እንኳን ደስ አላችሁም እንላለን። አንድነት ባለበት ሁሌም ድል አለ። ምክኒያቱም አንድ ስንሆን ጠንካራ፣ ስንከፋፈል ደግሞ ደካማ ስለምንሆን ነው። ለብቻችን ታግለን የተወሰኑ ድሎችን ልናገኝ እንችል ይሆናል፣ አብረን ከታገልን ግን ሙሉ ድል እናመጣለን፣ የአማራ ህዝብን ከጭቆና ቀንበር ነፃ እናወጣለን። በመካከላችን ልዩነት አይኖርም ማለት አይደልም። ሁሌም የስልት እና ፍላጎት ልዩነቶች ይኖራሉ። ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው። የድል አድራጊነት ዋናው መገለጫ በልዩነት ውስጥ አንድነት ፈጥሮ መታገል መቻል ነው። የትግል ስልታችንን አጣጥመን፣ ግለሰባዊ ፍላጎቶችን ገትተን አንድነት ማምጣት እና ትግላችንን በጋራ ማካሄድ ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው። ከዚህ በላይ እኛ በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ የመቀልበስ ግብን ያነገብን የህዝብ ልጆች ነን። ከዚህ ከትልቁ ግባችን አንፃር ሲታይ ያሉን ልዩነቶች ከዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም። በአንድ ላይ የቆሙ ትንሾች የተከፋፈሉ ብዙዎችን እንደሚያሸንፉ ሁሉ፣ ኃይላችን ያለው ከቁጥራችን መብዛት ሳይሆን በአንድነታችን ላይ ነው። የአማራ ህዝብ በቁጥር ብዙ ሆኖ እያለ እስካሁን ደካማ የሆነው አንድነት ባለመኖሩ ነው። በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ አንድነት የጎደለበትና የተሰባበረበት ምክኒያት ደግሞ የትግሉ ማዕከል የሆንነው እኛ አንድ መሆን ስላልቻልን ነው። በአንድ ስም ፋኖ ተብለን እየተጠራን፣ ለአንድ ዓላማ የአማራ ህዝብን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እየታገልን አንድ መሆን ግን አልቻልነም። ይባሱን ከራሳችን ጋር ጉልበት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የጌታቸው ረዳ ቡድን የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች ለሕወሓት ወግነው ግዚያዊ አስተዳደሩን ሊያፈርሱ ነው አለ

የትግራይ ሐይል አዛዦች ያስተላለፉት ውሳኔ ተከትሎ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ መጥራቱን የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ማምሻው ባወጣው መግለጫ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች “ከተልእኳቸው ውጭ ለአንድ ሕገወጥ ቡድን ወግነው ግዚያዊ አስተዳደሩን የማፍረስ፣ ስርዓት አልባነት የማንገስ እና ሰራዊት የመበተን ግልፅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል” ብሏል።የትግራይ ሐይል አዛዦች በዛሬው ዕለት ያስተላለፉትን ውሳኔ ግዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀውና “ሕጋዊ ይሁን ሞራላዊ ቅቡልነት የሌለው” ሲል ያመለከተው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መግለጫ፤ ከዚህ በተጨማሪ የፕሪቶርያ ውልንም ለአደጋ የሚያጋልጥ እና ሃላፊነት የጎደለው ብሎታል። ካለፈው ጥር 10 ቀን 2017 ዓመተምህረት ጀምሮ ስብሰባ ሲያደርጉ የሰነበቱ ሁለት መቶ ገደማ የሚሆኑ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያለው ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል። የወታደራዊ መሪዎቹ መግለጫ በንባብ ያቀረቡት ኮነሬል ገብረ ገብረፃዲቅ “የደከመ እና ተልእኮው የዘነጋ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲጠናከር የሚተኩ አመራር ተተክተው ሊስተካከል ይገባዋል። በግዚያዊ አስተዳደሩ ማቋቋሚያ መሰረት ሓምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ ያለው፣ የፕሪቶርያ ውል ተደራዳሪ እንዲሁም 14ተኛ ጉባኤ ያደረገ ህወሓት ግዚያዊ አስተዳደር ለማስተካከል የወሰነው ውሳኔ ያለ ያለመዘግየት ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፋችንን እንገልፆለን” ሲሉ አስታውቀዋል። ይህ ተከትሎ መግለጫ ያወጣው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራዉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር፥ የትግራይ ሐይል አዛዦች ውሳኔ የህዝብ ችግርን የሚያባብስ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትግራይ ጉዳይ ወዴት ?

የትግራይ ጉዳይ ወዴት ? በትግራይ ክልል ያሉ የበላይ ወታደራዊ ኃይል አመራሮች እንደሆኑ የገለጹ መኮንኖች ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ‘ የተዳከመ ‘ ያሉት በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ተነስቶ በሌላ እንዲዋቀር መወሰናቸውን ገልጸዋል። ” የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ አሳልፈናል ” ብለዋል። ” በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም የሌሎች መጠቀሚያ ሆኗል ” የሚል  ክስም አቅርበዋል። ” በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁልፍ ሥልጣን የነበራቸው አመራር እና አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ ውጪ የሕዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው ክህደት በመፈጸም የውጭ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል” ብሏል። በሕዝብ ጥቅም ላይ ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ ” የውጭ ኃይል ” ያሉት አካል ማንነትን በተመለከተ በግልጽ የተናገሩት ነገር የለም። የወታደራዊ አመራሮቹ በሰጡት መግለጫ በስፋት ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ድክመት ሲናገሩ የነበረ ሲሆን ” የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም እየሞከረ ነው ” የሚል ክስም አቅርበዋል። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ለተካሄደው (በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን) የህወሓት 14ኛ ጉባኤ እውቅና በመስጠት በጉባኤው ውሳኔ መሠረት የጊዜያዊ አስተዳደር የአመራሮች ለውጥ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን ጉባኤ የምርጫ ቦርድ እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች እውቅና እንደነፈጉት ይታወሳል። ወታደራዊ አመራሮቹ ” ህወሓት የትግራይን ጊዜያዊ አስተዳደር ለማሻሻል ያሳለፈው ውሳኔ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ” ያሉ ሲሆን ” ሠራዊቱን ወክለው በጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት የሆኑትን ግለሰቦች በመገምገም እምነት የሚጣልባቸው ያልሆኑትን በሌሎች እንዲተኩ ወስነናል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአማራ ፋኖ በጎጃም የፋኖዎችን ተጋድሎና ድል ሲዘግብልን የነበረው ፋኖ ዮሃንስ አለማየሁ ተሰውቷል

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !! የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ እረፍት ከአባልነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ግንባር ቀደም ትግል ሲያደርግ የነበረው ጀግናው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን ሌሊት ለጥር 13 አጥቢያ ዋሸራ በተባለ ቦታ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተናንቆ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ። ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ጎንጅ ወ እንዘግድም በተባለ ቦታ የተወለደ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ በፊት “በአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ ” ከፍተኛ አመራር በመሆን ወቅቱ የጠየቀውን ትግል አድርጓል ። ከዚያም አብይ አህመድ አማራን መውረሩን ተከትሎ ወደ ትውልድ ቀዬው እንዘግድም በመሔድ ቀደም ሲል የነበረውን ” ጎንጅ ወ እንዘግድም ብርጌድን” የአሁኑን “ንስር ብርጌድን” ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመመስረት አይተኬ የትግል አሻራ ያሳረፈ ጀግና ነበር። ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በሞጣ : በአዴት : በምላጭበር : በፈረስ ቤት በቋሪት ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ከባድ ውጊያ ያደረገ ልበ ቆራጥ አርዓያ ፋኖ ነበር። የአማራ ፋኖ በጎጃም ከተመሰረተ ዕለት ጀምሮ በአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኘነት ሀላፊ በመሆን ሰለቸኝ ታከተኝ ሳይል ያገለገለ ሲሆን ከቅንነት የመነጨ ልበ ቆራጥነትን ያስመሰከረ እና ታታሪነትን እና ለህዝብ ዋጋ መክፈልን መርህ ያደረገ ጀግና የፋኖ አመራር ነበር። የአማራ ፋኖ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኖርዌይ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ባስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዙ ተሰማ

የኖርዌይ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ በአገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ባስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዙን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኖርዌይ፣ የውጭ ዜጎችን መውጣት እውን ለማድረግ፣ ከመነሻ አጋራቸው ጋር በትብብር ለመስራት ጥረት እያደረገች መኾኗን ባለሥልጣናቷ መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። አውሮፓ ኅብረት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ለሙቀበል ትብብር አላሳየም በማለት፣ ከወራት በፊት በኢትዮጵያዊያን ላይ ጠበቅ ያለ የቪዛ ገደብ መጣላቸው ይታወሳል። ኾኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ኖርዌይ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በስደተኛ መጠለያዎች የኖሩ የተወሰኑ ስደተኞችን እንደተቀበለ የጠቀሱት ዘገባዎቹ፣ መንግሥት በዚኹ ትብብሩ ከቀጠለ ኖርዌይ በኢትዮጵያዊያን ላይ የጣለችውን የቪዛ ገደብ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ልታነሳ እንደምትችል መጠቆሟን ጠቅሰዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ በፖለቲካ ሴራና በጥቂት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጥላቻ’ ስቃይ እየደረሰበት ነው አሉ

“ክሱን የያዙ ጠበቆች ለሚድያዎች የክሱን ሒደት እንዳያስረዱ ዛቻና ማስፈራርያ እየደረሰባቸው ነው”- የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ቤተሰቦች (መሠረት ሚድያ)- ጥቅምት 2016 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ቤተሰቦች ‘በፖለቲካ ሴራና በጥቂት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጥላቻ’ ስቃይ እየደረሰበት ነው በማለት ተናገሩ። የቤተሰብ አባላቱ ለመሠረት ሚድያ በሰጡት ቃል “ያለፍትሕ ከታሰረ አንድ ዓመት ከአራት ወር ያህል ሆኖታል፣ አሁን ላይ የክልሉ መንግሥት በዳኞች ላይ በሚያደርሱት ፖለቲካዊ ጫና ዙርያ መረጃ ይፋ ማድረግ እንፈልጋለን” ብለዋል። አክለውም “ምንም እንኳን በቀረበበት ክስ ላይ በተገቢዉ መልኩ የተከላከለ ቢሆንም የክልሉ መንግስት የፍትህ ስርአቱን ለማዛባት ከሚያደርጉት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት በተጓዳኝ ክሱን  የያዙ ጠበቆች ለሚድያዎች የክሱን ሒደት እንዳያስረዱ ዛቻና ማስፈራርያ በማድረስ ላይ ነው” ያሉት እነዚህ የቀድሞው የሀዋሳ ከንቲባ ቤተሰቦች የመከላከያ ምስክር ተደርገዉ የተቆጠሩ የመንግስት ስራ ሀላፊዎቾ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ቃል እንዳይሰጡ ዛቻና ማስፈራራት፣ በሰበብ አስባብ ቀጠሮዎችን ማራዘምና በቂ የህክምና ክትትል እንዳያገኝ ከማድረግ አንስቶ ቤተሰቡን እና ልጆቹን ለችግር እንዲዳረጉ አስርገዋል ብለው ከሰዋል። “ኢትዮጲያ ህዝብና መላዉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድምጽ እንድትሆኑት ስንል በማክበር እንጠይቃለን” ብለዋል። ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ በከንቲባነት ዘመናቸው ህዝብን የሚጎዳ ጥፋት እንዳልሰሩ እና እሳቸውን ማሳደዱ ‘የስልጣን ፍላጎትና የእዉቅና ሽሚያ’ በማለት ከዚህ በፊት በሚድያዎች በኩል ተናግረው ነበር። የቀድሞ ባለስልጣኑ በህግ ሲፈለጉ ከቆዩ በኋላ ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የትግራይ ሕዝብ አሳር ሊያበቃ ይገባል መፍትሄ ይሰጥ”- ኢሕአፓ

“የትግራይ ሕዝብ አሳር ሊያበቃ ይገባል መፍትሄ ይሰጥ”- ኢሕአፓ ጥር 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ነባራዊ የትግራይ ክልል ሁኔታን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ በበርካታ ችግሮች እየተጨቆነ ያለው የክልል ማህበረሰብ አሳር ሊያበቃ ይገባል ሲል ገልጻል፡፡ በቅርቡ አክሱም ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች፣ ሂጃብ በማድረጋቸው የተነሳ በተወሰኑ ርዕሰ- መምህራን የተናጠል ውሳኔ ለፈተና እንዳይ መዘገቡ መደረጋቸውን፣ይህንንህገ-ወጥ የዕምነት ነፃነት ነፈጋን፣ ከህግም ከሀገራዊ እሴቶች ያፈነገጠ በመሆኑ በአጽኖኦት እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡ እንዲሁም ፍርድ ቤት እንዲያርሙ የሰጠውን ትዕዛዝ ለማክበር ፈቃደኞች አለመሆናቸው ደግሞ ከፍተኛ ዕብሪትና ህገ-ወጥነት ስለሆነ በአፋጣኝ በሚመለከታቸው ክልላዊና የፌዴራል ባለሥልጣናት አስገዳጅ የርምት ርምጃ እንዲወስድባቸው ፓርቲው አሳስቧል፡፡ የትግራይ ህዝብ በአንዳድ የመገንጠል ዓላማ ባላቸው ፖለቲከኞች የተነሳ ከጎረቤቱ የአማራና የአፋር ክልል ህዝብ ጋር ሁሌም በጠላትነት እንዲተያይ የሚደረገው የአንዳንድ ፖለቲከኞች ሸር ማብቃት አለበትም ተብሏል፡፡ በመሆኑም ሁለቱም የህወሓት ቡድኖች በንግግርና በመቻቻል አስቸኳይ ሠላማዊ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያበጁ እና በትግራይ ክልል የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን በማድረግ የህዝቡ ሁለንተናዊ ሠላም እንዲረጋገጥ መደረግ እንደሚገባው ኢሕአፓ አሳስቧል፡፡ በተጨማሪም ምንም እንኳን የትግራይ ህዝብ እንደ ፌደሬሽን አባልነቱ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 38 ወንበሮች ያሉት ቢሆንም ከጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ተወክሎ አያውቅም። ይህም ሲባል ባለፉት 4 ዓመታት በፓርላማው እና በፌደሬሽን ምክርቤቶች የሚተላለፉ ውሳኔዎች የትግራይ ህዝብን ፍላጎቶች ያካተቱ አልነበሩም፤ ስለዚህ ለዚህም አስቸኳይ ምርጫ በማካሄድ የትግራይ ህዝብ ጉዳዮችን በእንደራሴዎቹ እንዲወስን በህዝብ ተወካዮች እንዲወከል እንዲደረግ ጠቁሟል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ተከታታይ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ሆና ምንም አይነት ሀገራዊ ምክክር ማድረግ አትችልም”- ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

“ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ተከታታይ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ሆና ምንም አይነት ሀገራዊ ምክክር ማድረግ አትችልም”- ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ብሔራዊ መግባባት በሚል ርዕስ ዛሬ በተካሄደው 2ኛው የፓርላማ የዜጎች ፎርም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ በርካታ ሀሳብ እና አስተያየት ተስተናግደዋል፡፡ ሀሳባቸውን የሰጡት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በበኩላቸው ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ተከታታይ የፖለቲካ ቀውስ እና አለመግባባት እንዲሁም ጦርነት ውስጥ ምን አይነት ሀገራዊ ምክክር ሊደረግ ይችላል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ እንዲሁም የሰላም እና የጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ቢሆንም የውይይቱ ዋነኛ መወያያ ርዕስ አለመሆኑ ሊታሰብበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም “በትክክል አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ ውጤታማ የሆነ ሀገራዊ መግባባት አካሂደን የሀገራችንን የወደፊት ተስፋ መቅረጽ በምንችልበት ቁመና ላይ ነው ያለነው” በማለት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠይቀዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ፕ/ር መስፍን አርአያ የተነሱት ጥጣቄዎች አግባብነት ያላቸው መሆናቸውን ገልጸው ሀገራዊ ምክክር የሚደረገው በሶስት መንገድ ነው አንደኛውም በግጭት ውስጥም ተሆኖ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ አንጻራዊ ሰላም እንደሚያስፈል እና ከመንግስትም ሆነ ከተቋዋሚ አካላት ከሁሉም ህዝቦች ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለውይይት የሚሆን አስቻይ ሁኔታዎችን ፍጠሩልን ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማት አብይ አሕመድ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲያደርግ አዘዙ

ከስድስት ወራት በፊት የተደረገውን የውጪ ምንዛሪ ለውጡን ከግምት ውስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ መቅረቡን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። ጥቂት ወራት በፊት መንግሥት ከፍተኛ የተባለ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም፣ ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋማቱ ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ጋዜጣው መረዳቱን ጠቅሷል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ፣ ካሳለፈነው መስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል። አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያው እስከ 200 ሜጋ ዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ መገለፁን ያስታወሰው ዘገባው፣ ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ውስጥ 122 በመቶ መድረሱንም ጠቅሷል። ይህም ሆኖ፣ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ ዓለም ባንክ እና የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋምን(አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉት ዓለም ዓቀፍ የአገሪቷ አጋሮች የተለያዩ ድጋፎች ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ፣ መንግሥት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሬ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸውን ዘገባው አትቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አራት መቶ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ

ወደ አራት መቶ የሚጠጉ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሠራተኞች፣ “አይሶን ኤክስፔሪያንስ” በተሰኘ ወኪል ተቋም ይፈጸምብናል ባሉት የአሥተዳደር በደል ምክንያት የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ዋዜማ ሰምታለች። የሠራተኞች ማኅበር ሊቀ መንበሩ ሳላሃዲን ጀማል፣ ሠራተኞቹ የሥራ ማቆም አድማውን ካደረጉ ዛሬ ሁለተኛ ቀናቸውን እንዳስቆጠሩ ጠቅሰው፣ ሠራተኞቹ በተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ የሆኑ አሥተዳደራዊ በደሎች እንደሚደርስባቸው ለዋዜማ ነግረዋታል። ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ለማድረጋቸው፣ በወኪል ድርጅቱ በኩል የሚከፈላቸው ወቅቱን ያላገናዘበ ዝቅተኛ ክፍያ ዋነኛው ምክንያት መሆኑንም ነግረውናል። ወኪል ድርጅቱ ከፍተኛ የሚባል ደምወዝ ይከፈላቸዋል የተባሉ ሠራተኞችን በተጠና መልኩ ከሥራ እንዲሰናበቱ ከማድረጉ ባሻገር፣ እጅግ ከባድ የሚባሉ መመዘኛዎችን በማውጣት ሠራተኞችን ከሥራ እያባረረ እንደሚገኝም ሰምተናል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ተመሳሳይ የሥራ አይነት የሚሰሩ ሠራተኞች፣ በቋንቋና ማንነት ልዩነት ብቻ የሚደረግ ሕገ-ወጥ የደሞዝ ልዩነትና አድሎ መኖሩን የማኅበሩ ሊቀመንበር ለዋዜማ ነግረዋታል። በዚሁ የሠራተኞቹ አድማ ምክንያትም፣ ዛሬ ጥር 13፣2017 ዓ.ም እኩለ ቀን ድረስ፣ ሁሉም የሳፋሪኮም የጥሪ ማዕከላት ጥሪ እንደማይቀበሉ ዋዜማ ማረጋገጥ ችላለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጉራጌ ዞን ለ7 ወራት በእስር ላይ ያሉ “የአማራ ብሔር ተወላጆች” “ፍትሕ ተነፍገናል” እያሉ ነው

ዋዜማ- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ከባለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙ “የአማራ ብሔር ተወላጆች በፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኙ” ሰባት ወራት እንደሞላቸው ለዋዜማ ተናግረዋል። እነዚሁ ግልፅ ባልሆነ ውንጀላ በእስር ላይ የሚገኙት ዜጎች “በጸጥታ ኃይሎች በሚደርስባቸው ድብደባ ለአካል ጉዳት” መጋለጣቸውም ለዋዜማ ነግረዋታል። በጉራጌ ዞን “የአማራ ብሔር ተወላጅ” በሆኑ ነዋሪዎች ላይ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት እስር የተጀመረው ከባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጀምሮ እንደሆነ ዋዜማ ታስረው ከተፈቱና ከሌሎች ታሳሪዎች ቤተሰቦች ስምታለች። የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በቀበሌዎቹ የሚኖሩ “የአማራ ብሔር ተወላጆችን ‘ፋኖን ታሰለጥናላችሁ’፣‘ትደግፋላችሁ’፣ ‘የፋኖ ክንፍ ናችሁ’ ” በሚል ምክንያት ከመኖሪያ ቤት እና ከስራ ቦታ ወስደው እንዳሰሯቸው ነዋሪዎች ነግረውናል። በዞኑ በወልቂጤ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ ውስጥ በባለፈው የክረምት ወር ከ 100 በላይ የአማራ ክልል ተወላጆች ታስረው የነበረ ቢሆንም፤ “ገንዘብ የመክፈል አቅሙ ያላቸው እስረኞች ለመርማሪዎች እና ለፖሊስ አባላት እስከ 50 ሺህ ብር ጉቦ በመክፈል” ከእስር እንደተለቀቁ ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመላክታል። አሁን ላይ በአዳራሹ 80 የሚጠጉ ሰዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። በእነዚህ እስረኞቹ ላይ የጸጥታ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ ለአካል ጉዳት የተጋለጡ መኖራቸውን ዋዜማ ከታሳሪዎች ሰምታለች። በጉራጌ ዞን በአበሽጌ ወረዳ ስር በሚገኙ ዋልጋ እና ዳርጌ ቀበሌዎች አሁን ድረስ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች መኖራቸውንም አክለዋል። “[ታሳሪዎችን] መያዝ የተጀመረው ከሐምሌ ወር ጀምሮ ነው። በጣም ቆይቷል። በከፍተኛ ሁኔታ ስቃይ ውስጥ ነን” ሲል ከሐምሌ ወር ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኝ ምንጭ በጸጥታ ኃይሎች ይደርስብናል
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል

“የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል” – IOM መነሻውን ከጅቡቲ በማድረግ 35 ኢትዮጵያውያንን አሳፍሮ ወደ የመን ሲያቀና የነበረ የስደተኞች መርከብ በኃልኛ ንፋስ ተመቶ በደረሰው አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል አደጋው ቅዳሜ ዕለት (ጥር 10) መድረሱን፤ የ9 ሴቶች እና የ11 ወንዶች ህይወት ማለፉን የጠቀሰው ድርጅቱ በመርከቡ የነበሩ 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን ዜግነት ያላቸው መርከበኞች ደግሞ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል። https://yemen.iom.int/news/tragic-boat-capsizing-claims-20-lives-yemens-taiz-governorate
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ነዳጅ በኩፖን እንዲሆን ተወስኗል

“የነዳጅ ምርት እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ሽያጩ በኩፖን እንዲሆን ተወስኗል” የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በየጊዜው የነዳጅ እጥረት ከመሻሻል ይልቅ እየተባሰ በመምጣቱ ሽያጩ በኩፖን እንዲሆን ተወስኗል ሲል ያስታወቀውየደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ ነው፡፡ በቢሮው በኩል ለሁሉም ዞን ንግድና ገቢያ ልማት መምሪያ ዛሬ ተጽፎ በተሰራጨው ሰልኩላር ደብዳቤ መሰረት ከጥር 30 ጀምሮ ሁሉም የነዳጅ ማደያ ያለባቸው ከተሞች ከጥር 30/2017 ጀምሮ ነዳጅ በኩፖን እንዲሸጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ቢሮው የነዳጅ ምርት እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በተለይ የባለ ሁለት እግር ሞተሮች በየቀኑ ተመላልሶ መቅዳት ለኮንትሮባንድ ሽያጭ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ መንስኤዎች መሆናቸውን ከተደረገው ክትትል ለማረጋገጥ ተችሏል ብሏል። በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች የኩፖን ሥርዓት በመዘርጋቱ ሥርጭት ላይ ያለውን የቤንዚን ምርት በአግባቡ ማሰራጨት መቻሉንና ለክትትልም ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ማስተዋሉን ነው በደብዳቤው የጠቀሰው። በመሆኑም የነዳጅ ማደያ ያለባቸው ከተሞች ከጥር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ የትኛውም ተሽከርካሪ በኩፖን ብቻ እንዲስተናገድ እና ታርጋ የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሀጋዊ የተሽከርካሪ ሠሌዳ እስኪያወጡ ድረስ የግልም ሆነ የመንግስት ተሽከርካሪዎች እንዳይስተናገዱ ሲል በደብዳቤው ጠቅሷል። ቢሮው አክሎም “ህገ-ወጥ የሆኑትን ማክሰም አስፈላጊ በመሆኑ ተግባራዊ እንዲደረግ እየገለጽን የነዳጅ ምርት ሽያጭም ቢሆን በኤሌክትሮኒክስ ቴሌ ብር እና ሲቢኢ ብር/ የመገበያያ መንገዶች ብቻ እንዲፈጸም በጥብቅ እናሳስባለን፡፡” ሲል በሰርኩላር ደብዳቤው አስታውቋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፕሬዚዳንት ትራምኘ ንግግር ትርጉም (በአማርኛ)

(ተርጓሚ መምህር አቤል ጋሼ) 47ኛ ትላንት የአሜሪካ ው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ የተናገሩት ንግግር በጣም የሚገርም ነበር። በመጪው 4 ዓመታት በዚህ በአሜሪካም በአለም ዙሪያም: ብዙ ለውጥ የምናይ መሆኑን የሚጠቁም ኃይለኛ ንግግር ነው፡ ፡ በዚህ ፕሬዚዳንት ዘመን የሚሆኑትን ነገሮች ላጤነ የሚከተሉት የፖለቲካ የማኅበራዊ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ክንውኖች ን መሰረታዊ ለውጥ የሚጠይቁ ይሆናሉ : : ያስደሰተኝ አንድ ሐረግ :- ከዚህ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ የምናውቀው ሁለት ፆታ ነው፡ ፡ ወንድ ና ሴት :: ስለ ሁሉም ነገር ይኸ ንግግር በአማርኛ ተተርጉሞ ይዘቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ … እነሆ : የትርጉም ስህተትና ማስተካከል ካለው በቅድሚያ ይቅርታ እየጠየቅን የማሻሻያ አስተያየት ያዳብረናል … እርማት ካለ ይላኩልን …እናሻሽለዋለን :: https://drive.google.com/file/d/1b0ehpISH5SiYlWLOXM-0Oo-4wmDO91nR/view?usp=drivesdk
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

የእርጅና ሥነ ውበትና ታሪካዊ ዕሴት…(The Aesthrtics of Ageing and Historical Value) ( በጌታሁን ሃራሞ )

ፋሲልን ተጫወቱበት ! የእርጅና ሥነ ውበትና ታሪካዊ ዕሴት…(The Aesthrtics of Ageing and Historical Value) ( በጌታሁን ሃራሞ ) ጂዮርጅ ጊልበርት ስኮት እ.ኤ.አ. ከ1811-1878 በምድረ እንግሊዝ የኖረ ዕውቅ የ”Gothic Revival” አርክቴክት ነበር፡፡ በሕይወት ዘመኑ ይበልጥ የሚታወቀው እንግሊዝ ውስጥ የሚገኙ እድሜ ጠገብ ካቴድራሎችን በማደሱ ነበር፡፡ ሆኖም ስኮት በዕድሳቱ ወቅት ይከተለው የነበረው የ”Restoration” መርህ በወቅቱ ከነበሩ የኪነ ሕንፃ ሐያሲያን፣ የታሪክ ምሁራንና ፈላስፎች ውግዘትን ያስከትልበት ነበር፤ ከዕድሳት ጋር በተገናኛ ሰውዬው እንደልቡ የሚባል ዓይነት አርክቴክት ነበር፤ ስኮት ሲያሰኘው የዕድሜ ጠገቡን የካቴድራሉን ዕድሜ ጠገብ ኮርኒስ ፕላስተርንግ ሙሉ በሙሉ በማስነሳት በእንጨት እስከመተካት ይደርስ ነበር፤ አንዳንዴም በሕንፃው አርክቴክቼራል አካላት ላይ እስከ 4 ሜትር ቁመት በራሱ ሥልጣን ይጨምር ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ የቅርቡ የሆኑ ወደዳጆቹና ተማሪዎቹም ሳይቀሩ…ይኄማ ከ”Restoration”ንም የዘለለ የ“Remodelling” ሥራ ነው… በማለት ድፍረት የተሞላበትን የስኮትን የዕድሳት አካሄድ ይቃወሙ ነበር፡፡ ፋሲልን ተጫወቱበት !ይሁንና ጂዮርጅ ጊልበርት ስኮት ከሌሎች አርክቴክቶችና ምሁራን ለሚሰነዘርበት የሂስ ናዳ ግድ የሌለው ሰው ነበር፤ አልፎ ተርፎም “I am not a medieval architect” በማለት በጥንታዊ ሕንፃዎች ላይ የራሱን ወቅታዊ አሻራዎች ለማሳረፍ ይደፍር ነበር፤ ሆኖም ይህ ሽሽቱ በተለይም በዕድሜ ማብቂያው አካባቢ የሚያዋጣው ሆኖ አልተገኘም፡፡ እንደ ዊሊያም ሞሪስ ያሉና ለዕድሜ ጠገብ ቅርሶች ክብር ያላቸው አርክቴክቶች ይህ ሰው በጊዜ የእንደልቡ-ዕደሳቶቹን እንግሊዝ አለኝ በምትላቸው ቅርሶች ላይ መተግበሩን ካለቆመ ጉዳቱ ለማረም አዳጋች ወደሆነ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል ለእንግሊዝ ማህበረሰብ አሳወቁ፡፡ አደጋው ያሳሰባቸው አርክቴክቶች፣ የአርክቴክቸር ሐያሲያንና የታሪክ ምሁራን፣ በስኮት የዕድሳት ወንጀሎች
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

አሜሪካን አገር የስራ ፈቃድ የሌላችሁና ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ የተላለፈ መልዕክት

⚠️አሜሪካን አገር የስራ ፈቃድ የሌላችሁና ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ የተላለፈ መልዕክት 1) በዲሲ፣ ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ያላችሁ እና የሥራ ፈቃድ የሌላችሁ ኢትዮጵያውያን፤ ከነገ ጀምሮ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። በተለይ ያለ ሥራ ፍቃድ የምትሰሩ ከሆናች ሁ፤ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አስራ አምስት ቀናት ከቻላችሁ መስራት አቁሙ። በዲሲ እና አካባቢው ከነገ ጀምሮ ትልቁ የኢሚግሬሽን ወረራ (raids) የሚደረግበት ነው። ወረቀት የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን የሚያሰሩ ሰዎች የዚህ (raids) ትልቁ ትኩረት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። 2) በአሳይለም ላይ ያላችሁ ሁሉ እጃችሁ ላይ ዶክመንት ይዛችሁ ተንቀሳቀሱ። ለምሳሌ የሥራ ፍቃድ ያላችሁ የሥራ ፍቃድ ካርዳችሁን፣ የሥራ ፍቃድ ካርድ የሌላችሁ ደግሞ አሳይለም ፋይል ያደረጋች ሁበትን ሪሲት ይዛችሁ ተንቀሳቀሱ፤3) ቦርደር አካባቢ የምትኖሩ ሰዎች እና ወርቀታችሁ ያልተስተካከለላችሁ ሰዎች ፥ ከቦርደር አካባቢ ራቁ። ምክንያቱም የImmigration and Custom Enforcement ኦፊሰሮች በብዛት የሚኖሩበት ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።4) ማናቸውም የኢሚግሬሽን ኬዝ ያላችሁ እና በዚህ ጉዳይ ስጋት ያላችሁ ሰዎች የኢሚግሬሽን ጠበቆችን አናግሩ። ምንም ውሳኔ ከመወሰናችሁ በፊት ከኢሚግሬሽን ጠበቆች ጋር ተማክራችሁ አድርጉ።
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ መሆኑ ተገለጸ በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በአክሱም አካባቢ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል። ምክርቤቱ ለክልሉ መገናኛ ብዙሀን በላከው ደብዳቤ በአክሱም ከተማ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጀ ትምህርት ቤቶች ከጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የተፈፀመው ህገወጥ በሆነ የሂጃብ ክልከላ ምክንያት የእስልምና እምነት ተከታይ ሴት ተማሪዎች ለወራት ከትምህርት ገበታ እንዲገለሉ ማድረጉን አመላክቷል። ምክርቤቱ አክሎም እስካሁን ድረስ ለተለያዩ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ያልናቸው አካላት በአካልና በፅሑፍ ጥያቄ ስናቀርብ ብንቆይም እስካሁን ድረስ ጉዳዩ መፍትሄ ሳያገኝ መጥቷል ብሏል። እየተካሄደ ያለው ሰልፍም የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤትና ከክልሉ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ዋና ፅህፈት ቤት መነሻውን አድርጎ በሮማናት አደባባይ ፍፃሜውን እንደሚያደርግ ከትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት የተገኘው መልእክት አመላክቷል። በተመሳሳይ በአጠቃላይ አራት የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን እና እስካሁንም ድረስ የተደረሰ የጋራ መግባባት እንደሌለ እና ተማሪዎቹም ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዳልተመለሱ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እስማኤል አብድራህማን ገልጸው ነበር፡፡ እንዲሁም በአስተዳደር ደረጃ ማንም ሂጃብ አይልበሱ ብሎ የሚከራከር አመራርም ሆነ ግለሰብ ባይኖርም ለተፈጠረው ችግር መፍትሄ የሰጠም አለመኖሩም መገለጹ ይታወሳል፡፡ ” ሂጃቧን ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች  ”  – ሰልፈኞች የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከሂጃብ ክልከላ ጋር ተያይዞ የፍርድ ቤት እና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አዲስ አበባ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው የተገደሉትን ባለሃብት ገዳዮችን ይዣለሁ ሲል ፖሊስ ተናገረ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የባለሀብቱን ገዳዮች መያዙን አስታወቀ (መሠረት ሚድያ)- ሚድያችን ከሀያ ቀን በፊት ታዋቂው የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ምናለ ምሽት 1:30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ መዘገቡ ይታወሳል። መሠረት ሚድያ በወቅቱ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ባለሀብቱ በለሚ ኩራ፣ ወረዳ ዘጠኝ ‘አትሌቶች መንደር’ መውረጃ አስፓልት አጠገብ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ መኪና ውስጥ ሆነው የግቢው በር እንዲከፈት ክላክስ እያደረጉ ባሉበት ወቅት በጥይት ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ይፋ ባረገው መረጃ የባለሀብቱን ገዳይ እና አስገዳይን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ “ምንም እንኳን ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመቀየር ከወንጀሉ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሐሰተኛ ስም ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ለመጥፋት ቢያስቡም በተሰራው እረፍት አልባ ፖሊሳዊ ጥበብ በታከለበት የክትትልና የምርመራ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል” ያለው ፖሊስ የወንጀሉ ፍሬ የሆነው ንብረትነቱ የአቶ አብዪ አይተነው ፈንታ የውግ ቁጥር የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ እና ለማምለጥ የሞከሩበት እንዲሁም ሽጉጡን የደበቁበት ላንድክሩዘር ተሽከርካሪ በኤግዚቢትነት ተይዟል ብሏል፡፡ የምስራቅ ጎጃም ቢቸና ወረዳ ተወላጅ የሆኑት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደርባ ከተማ ከታቦት ማደርያ ላይ የደብር አስተዳዳሪ እና ሁለት ሚሊሺያዎች ተወስደው ተገደሉ

በደርባ ከተማ ከታቦት ማደርያ ላይ የደብር አስተዳዳሪ እና ሁለት ሚሊሺያዎች ተወስደው ተገደሉ (መሠረት ሚድያ)- በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል ከጫንጮ ከተማ 20 ኪ/ሜ ገደማ ርቀት ላይ በሚገኘው በተለምዶ ‘ደርባ ሲሚንቶ’ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ታጣቂዎች ከታቦት ማደርያ ላይ አንድ የደብር አስተዳዳሪ እና ሁለት ሚሊሺያዎችን ወስደው መግደላቸው ታውቋል። መሠረት ሚድያ ዛሬ የደረሰው መረጃ እንደሚጠቁመው ታጣቂዎቹ ከግድያው በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎችንም አግተው ይዘው ሄደዋል። “ግድያ የተፈፀመባቸው የደርባ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው” ብለው ለሚድያችን የተናገሩት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ሁኔታው የፈጠረው ድንጋጤ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። መሠረት ሚድያ በስልክ ያናገራቸው አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የአካባቢው ባለስልጣን “ድርጊቱን የፈፀመው ሸኔ ነው፣ ሶስት ሰው ገድሎ ስምንት ሌላ ሰው ይዞ ጫካ ገብቷል” በማለት ማረጋገጫ ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ ዙርያ ባለው የሸገር ከተማ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ (ሰላሌ) አካባቢዎች ታጣቂዎች በርካታ ጥቃቶችን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ይታወቃል፣ በዚህ መሀል በርካታ ንፁሀን ዜጎችም ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ። የመንግስት ሚድያዎች በተለይ የመንግስት አመራሮች ላይ በታጣቂዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዳይዘግቡ ጥብቅ መመርያ እንደተላለፈላቸው ከሰሞኑ የደረሰን ተጨማሪ መረጃ ያሳያል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ ተነሺ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ ተነሺ አርሶ አደሮች ተቃውሞ እያሰሙ መኾኑን አፍሪካን ኢንተለጀንስ ድረገጽ ዘግቧል። አርሶ አደሮቹ ቅሬታ ያሰሙት፣ ከካሳ እና ከሠፈራ ዕቅድ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። መንግሥት ለማስፋፊያው የቀጠረው የሊባኖሱ አማካሪ ኩባንያ፣ አርሶ አደሮች ይነሱባቸዋል ወደተባሉት ቦታዎች ቅድመ-ጥናት የሚያካሄድ የባለሙያዎች ቡድን መላኩንም ዘገባው አመልክቷል። አኹን ከሚኖሩበት ቀያቸው 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንዲሠፍሩ ይደረጋሉ የተባሉት አርሶ አደሮች እስከ 2 ሺሕ 500 ይደርሳሉ ተብሏል። ተነሺዎቹ አርሶ አደሮች፣ በአንድ ስኩዌር ሜትር 322 ነጥብ 5 ብር ካሳ እንዲከፈላቸው እንደታሰነ ከአርሶ አደሮቹና ከአንድ ደብዳቤ ላይ መመልከቱንም የዜና ምንጩ አውስቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

” ሁለት ፆታዎች ብቻ ነው ያሉት እነሱም ወንድ እና ሴት ናቸው ” – ፕሬዝዳንት ትራምፕ

” ሁለት ፆታዎች ብቻ ነው ያሉት እነሱም ወንድ እና ሴት ናቸው ” – ፕሬዝዳንት ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ እንደገቡ ከሚሰሯቸው ዋነኛ ስራዎች አንዱ በሀገሪቱ ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እውቅና መስጠት ነው። ይህም በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣን የመልቀቂያ ጊዜ ለትራንስጀንደር / ፆታቸውን ለሚቀይሩ ሰዎች የሚሰጠውን ከለላና ጥበቃ የሚሽር ነው። ለወንድ እና ለሴት ብቻ እውቅና መስጠት ትራፕም ከሚያስተላልፏቸው ትዕዛዛት አንዱና ዋነኛው እንደሆነ ታውቋል። ትራምፕ ቃለ መሀላ ሲፈጽሙ ፥ ” ከዛሬ ጀምሮ / ከእንግዲህ ወዲህ / የአሜሪካ መንግሥት ፖሊሲ እውቅና የሚሰጠው ለሁለት ፆታ ብቻ ነው እነሱም ወንድ እና ሴት ” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል። የአሜሪካ መንግሥት ከአሁን በኃላ እውቅና የሚሰጠው ለወንድ እና ሴት ፆታ ብቻ እንዳሆነ የገለጹት ትራፕም ፤ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ብዝሀነት፣ እኩልነትና አካታችነት የሚባሉ ፖሊሲዎችን ለማስወገድ የአፈጻሚ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉ ተነግሯል። ከዚህ ባለፈ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፤ ፆታቸውን የቀየሩ (ትራንስጀንደር) ሰዎች በሴቶች ስፖርት ላይ እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ትዕዛዝም ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትራምፕ ” ሰዎች ተፈጥሯዊ ፃታቸውን መቀየር የለባቸውም ” ብለው የሚያምኑ ሲሆን ከዚህ ቀደም ፆታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ መነገሩ ይታወሳል። 15 ሺህ ፆታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው። ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉ መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።
Posted in Ethiopian News

አዋሽ አካባቢ እየተከሰተ ያለው የእሳተ ገሞራ ልቀት የአውሮፕላን ጉዞዎችን አቅጣጫ ማስቀየር ጀመረ

አዋሽ አካባቢ እየተከሰተ ያለው የእሳተ ገሞራ ልቀት የአውሮፕላን ጉዞዎችን አቅጣጫ ማስቀየር ጀመረ (መሠረት ሚድያ)- ላለፉት በርካታ ወራት አዋሽ አካባቢ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው የእሳተ ገሞራ እና ተያያዥ የተስፈንጣሪ ልቀት ኢትዮጵያ ውስጥ የአውሮፕላን ጉዞዎችን ማስተጓጎል መጀመሩ ታውቋል። መሠረት ሚድያ ከአቪዬሽን ምንጮቹ፣ ከፍላይት ራዳር እንዲሁም ከአንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊ ማረጋገጥ እንደቻለው እሳተ ገሞራው ወደ አየር እየለቀቀ ያለው አቧራ መሰል ቅንጣት (dust particle) አውሮፕላኖች ጉዟቸውን እንዲቀይሩ ማስገደድ ጀምሯል። “እስከ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ድረስ በዚህ ምክንያት መስተጓጎል ነበር” ያሉት የአየር መንገድ ምንጫችን አሁን ላይ ስላለው ሁኔታ አጣርተው መረጃ እንደሚሰጡን ተናግረዋል። ክስተቱ በትናንትናው እለት አንድ ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ ሲበር የነበረ የበረራ ቁጥሩ EK724 የሆነ የኤምሬትስ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ መስመሩን ቀይሮ ወደ ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ሲጓዝ ፍላይ ራዳር ላይ ተመልክተናል (ምስሉ ላይ ይታያል)። በተመሳሳይ በትናንትናው እለት በ ET227 የበረራ ቁጥር ያለው አውሮፕላን በትናንትናው እለት ከጅግጅጋ፣ እንዲሁም ET375 ከሀርጌሳ ወደ አዲስ አበባ ሲበሩ አቅጣጫ እንዲቀይሩ እንዳደረገ ተመልክተናል። በአለም ዙርያ የሚከሰቱ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታዎች ወደ አየር የሚለቋቸው ቅንጣቶች በተለያየ ግዜ በረራዎችን ከማስተጓጎል አልፈው እስከነጭራሹ ሲያሰርዙ ተስተውሏል። የዛሬ 15 አመት ገደማ በአይስላንድ የተከሰተ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ 100,000 በረራዎችን አስተጓጉሎ የነበረ ሲሆን ይህም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ ከፍተኛው የአቪዬሽን መስተጓጎል ሆኖ ተመዝግቧል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በአመራሮቹ መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” – ብጹህ አቡነ ማትያስ

በአመራሮቹ መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ እየታየ ያለውን የሰላም ጭላንጭል የሚያጨልም ነው” – ብጹህ አቡነ ማትያስ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል እየተካረረ የመጣው ልዩነት በክልሉ የተገኘችውን የሰላም ጭላጭል የሚያጨልም ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀጻጻስ የሆኑት አቡነ ማትያስ ገልጸዋል፡፡ ብጹህነታቸው ይህን ያሉት ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል እና ለግዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በተናጠል በጻፉት ደብዳቤ ነው። ፓትርያርኩ በደብዳቤያቸው ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለመወያየት ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳካላቸው በመጠቆም ደብዳቤውን ለመጻፈ መገደዳቸውን አስታውቀዋል። “በእልክ እኔ እሻላለሁ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ እኔ ብቻ ነኝ ለህዝብ የማስበው በሚል በተፈጠረው ውስብስብ ችግር የሚያዝን እንጂ የሚደሰት ህዝብ የለም” ሲሉ ጠቁመዋል። “በአመራሩ መካከል የተፈጠረው መለያየት እንዳይበቃ በአንድነት ተስማምቶ ሲኖር በነበረው ህዝብ መካከልም ተጽእኖው እየወረደ ይገኛል” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል::
Posted in Ethiopian News

ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ ለጌታቸው ረዳና ደብረፂዮን ገብረሚካኤል መልእክት አስተላለፉ

” እየሄዳችሁበት ያለው መንገድ ሁሉንም የሚያጠፋ ፤ የተገኘችውንም ሰላም የሚያደፈርስ በመሆኑ ህዝባችሁ የሚሰጣችሁ ምክር እና ተግሳፅ ተቀብላችሁ በስክነት እና በማስተዋል የህዝባችሁን ጥያቄ እንድትመልሱ አደራ እንላለን ” – ቅዱስነታቸው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት  ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እና ለህወሓት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ምክር እና ተግሳፅ አስተላለፉ። ቅዱስነታቸው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ጥር 6/2017 ዓ/ም በፃፉት ደብዳቤ ነው። ቅዱስነታቸው በዚሁ ደብዳቤ ፤ ሁለቱን አመራሮች በአካል አግኝተው ለማነጋገር  እንዳልተሳካላቸው ገልፀው ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መሄዳቸው አሳስቧቸው ለመሪዎቹ ሃሳባቸው በፅሁፍ ለመገለፅ መገደዳቸው አስፍረዋል። አመራሮቹ በትግራይ ያለው ጊዜ የማይሰጥ ተደራራቢ ችግር ከመፍታት ይልቅ ከመደማመጥ እና መከባበር በወጣ አኳኋን  እርስ በርስ በመዘላለፍ መጠመዳቸው እንዳሳዘናቸው ጠቅሰዋል። መሪዎቹ ጥበብን እና የሰለጠነ አሰራርን እንዲታጠቁ መክረዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ ” ካህናት አበው ፣ የቤተክርስትያን ሊቃውንት ፣ ምእመናን ፣ የአገር ሽማግሌዎች የዕድሜ ባለፀጎች በሃዘን እያነቡ አካሄዳችሁን እንድታስተካክሉ ሲለምኗችሁ እና ሲመክሯችሁ ሰክናችሁ ማሰብ እና ማዳመጥ የተሰናችሁ ምክንያት ምን ይሆን ? ” ሲሉ ጠይቀዋል። ” ‘ የእኔ አካሄድ ብቻ ነው ልክ ‘ በሚል እልህ እና አስተሳሰብ የፈረሰ እንጂ የተገነባ ህዝብ እና አገር የለም ” ሲሉ በአፅንኦት ያስገነዘቡት ቅዱስነታቸው ፤ ” የናንተ መለያየት አልበቃ ብሎ በአንድነት እና በመከባበር የኖረውን ህዝብ ለማራራቅ እየሄዳችሁበት ያለው ርቀት ህዝብን ለማገልገል መቆማችሁን ጥያቄ ውስጥ የሚከት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ምስጢረ ጥምቀት፡ የክርስትና መግቢያ በር

ምስጢረ ጥምቀትcover ጥምቀት(Mystery of Baptism) የሚለው ቃል “አጥመቀ” (አጠመቀ) ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በተከማቸ ውሃ ውስጥ መነከር፡ መዘፈቅ፡ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። ምስጢረ ጥምቀት በምስጢራዊ (በሃይማኖታዊ) ፍቺው በተጸለየበት ውሃ (ማየ ኅይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ብሎ የመውጣት ሂደት ነው (ማቴ 28፡19)። ጥምቀት “የክርስትና መግቢያ በር” ናት፡፡ ምክንያቱም ከሌሎች ምስጢራት ስለሚቀድምና ለእነርሱም መፈጸም ቅድመ ሁኔታ ስለሆነ ነው፡፡ ጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት (ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና) ምሥጢር ነው። ሰው ከሌሎች ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመካፈል አስቀድሞ መጠመቅና ከማኅበረ ክርስቲያን መደመር አለበት፡፡ ስለዚህም ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት እንዲሁም ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው፡፡ የእምነታችን መሠረትም፣ የጸጋ ልጅነት የሚገኝበትም ምስጢር ነውና ከሁለቱም ይመደባል፡፡ የጥምቀት አመሠራረት የምሥጢረ ጥምቀት መሥራች ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ነገር ግን ከጌታችን ጥምቀት በፊት አይሁድ ለመንጻትና ለኃጢአት ሥርየት (ይቅርታ) የሚጠመቁት “ጥምቀት” ነበራቸው፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥባቸው የተቀደሱ ዕለታትና ቦታዎች ሁሉ ሰውነትንና ልብስን ማጠብ የእግዚአብሔር ቤት ማገልገያ የሆኑ ዕቃዎችን ሁሉ ማጠብ ማንጻት ሥርዓትና ልማድ ነበር፡፡ ይህም የእግዚአብሔርም ፈቃድ ያለበት አሠራር ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከመቅረባቸውና ለተቀደሰው አገልግሎት ከመግባታቸው አስቀድመው እግሮቻቸውንና እጆቻቸውን የመታጠብ ግዴታም ነበራቸው፡፡ ሰውነታቸውን ከአፍአዊ (ከውጫዊ) እድፍ በማጠብና ንጹሕ በማድረግ በባሕርይ ንጹሕና ቅዱስ በሆነው አምላክ ፊት ውስጣዊ ሕይወትን ንጹሕ አድርጎ የመቅረብን ሥርዓትና ምሥጢር የሚያመለክት መንፈሳዊ ሥርዓት ነበር፡፡
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

ኢትዮጵያን “የተድበሰበሰ ክስ” ከሚመሠርቱና ከሚያስሩ አገራት ተርታ ተመደበች።

ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ) ትናንት ባወጣው ልዩ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያን “የተድበሰበሰ ክስ” ከሚመሠርቱ ወይም “በሽብር” ወይም “በአክራሪነት” ውንጀላ ቅጣት ከሚጥሉና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ከሚያስሩ አገራት ተርታ መድቧታል። በዙህም ኢትዮጵያ ከግብጽ፣ ሩሲያ፣ ማይነማርና ቤላሩስ ተርታ ተመድባለች። ኢትዮጵያ ካሠረቻቸው ስድስት ጋዜጠኞች አምስቱ በአማራ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ከዘገቡ በኋላ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው ሪፖርቱ ጠቅሷል። ስድስተኛው ጋዜጠኛ የሺሃሳብ አበራ በመስከረም 2017 ዓ፣ም መታሠሩንና ባለሥልጣናቱ ጋዜጠኛው የታሠረበትን ምክንያት እስካኹን እንዳልገለጡ ወይም ክስ እንዳልመሠረቱበት ሪፖርቱ ገልጧል። ኤርትራ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 16 ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ ኾና የቀጠለች ሲኾን፣ በዓለም ላይ ደሞ ከኢራንና ቬትናም ጋር ሰባተኛዋ ቀዳሚ ጋዜጠኛ አሳሪ ተብላለች።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብይ አሕመድ በመጭው ምርጫ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠልፎ ለመጣል የሚያስችል አዋጅ እንዲረቀቅ አዘዋል

አብይ አሕመድ በመጭው ምርጫ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠልፎ ለመጣል የሚያስችል አዋጅ እንዲረቀቅ አዘዋል፤ በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ረቂቅ ማሻሻያው፣ ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አዋጅ የሚጥሱ ፓርቲዎችን ሕጋዊነት ከመሰረዙ በፊት በጥፋቱ ክብደት ልክ እስከ 5 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ማገድ የሚያስችለውን ሥልጣን የሚሠጥ ነው። ቦርዱ የጣለበትን እገዳ የተቃወመ ፓርቲ፣ ውሳኔው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል የተሻሻለው አዋጅ ይፈቅዳል። ቦርዱ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ የማይችልባቸው “ኹኔታዎች” የሚለው አንቀጽም፣ የጸጥታ ችግር፣ ወረርሺኝ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ተብሎ ተዘርዝሯል። ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች ምርጫ የተመዘገቡ ዕጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር፣ የምርጫው ውጤት እስኪገለጽ በወንጀል ተጠርጥረው እንዳይያዙ የሚከለክል አንቀጽም በማሻሻያው ተካቷል። አዲሱ የምርጫ ቦርድ ማሻሻያ አዋጅ በመጭው ብርጫ እሸነፋለሁ ብሎ የሰጋው አብይ አሕመድ የፃፈው መሆኑ ታውቋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አርሶ አደሮች የስንዴ ምርት የበላይ አካል ትዕዛዝ ነው በሚል እንዲሸጡ ተገደዱ

መንግሥት በኦሮሚያ ክልል በክላስተር ከተዘራው የስንዴ ምርት 70 በመቶውን ከአርሶ አደሮች በወቅታዊ የገበያ ዋጋ ገዝቶ እየወሰደ መኾኑን ታውቋል። ባኹኑ ወቅት አንድ ኩንታል ነጭ ስንዴ በገበያ ላይ 5 ሺሕ 500 ብር እየተሸጠ ሲኾን፣ አርሶ አደሮች ግን በማዳበሪያ ዋጋ ውድነት የተነሳ ዋጋው አትራፊ እንዳልኾነ ተናግረዋል። አርሶ አደሮች፣ የምርታቸውን 70 በመቶ ለመንግሥት ለመሸጥ የገቡት ስምምነት ባይኖርም፣ የበላይ አካል ትዕዛዝ ነው በሚል እንዲሸጡ እየተገደዱ መኾኑን ገልጸዋል። ኾኖም ይህ አሠራር በክልሉ ወጥ በኾነ ኹኔታ እየተተገበረ አይደለም ተብሏል። የስንዴ ግዥውን ትዕዛዝ የሚያስፈጽሙት፣ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮች እንደኾኑ ተሰምቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኑሮ ውድነቱ ዋና ዲዛይነር የብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ የመለስ ዜናዊን አስተዳደር አማረሩ

የኑሮ ውድነቱ ዋና ዲዛይነር የብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምኅረቱ፣ የመለስ ዜናዊ መንግሥት የመረጠው የኢኮኖሚ ዕድገት ቅርጽ ችግር እንደነበረበት ከጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ከኾኑት ወይዘሮ ቢልለኔ ሥዩም ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል። አሁን ያለው የኑሮ ውድነትና የአይ ኤም ኤፍ ፖሊሲ ጥገኝነት የፈጠረውን የራሳቸውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ያንቆለጳጰሱት የባንኩ ገዢ በኢኮኖሚ ዕቅዶች አመራረጥ፣ አተገባበርና በፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ችግሮች እንደነበሩበት ማሞ ገልጸዋል። የአገሪቷን ኢኮኖሚ ያላሸቁት የአለም ባንክ ሰራተኛው ማሞ፣ ከለውጡ በፊት 70 በመቶ ገደማ የባንኮች ብድር ለመንግሥት ብቻ ይሠጥ እንደነበርና ባኹኑ ወቅት ግን 80 በመቶው ገደማ የባንክ ብድር ለግሉ ዘርፍ እየተሰጠ መኾኑን ማሞ አውስተዋል። ይህን ይበሉ እንጂ ባንኮ ምንም አይነት ብድር የማይሰጡና በርካታ ቅድመ ሁኔታ ደርድረው ደንበኞቻቸውን እያራቁ ሲሆን የባንኮች ከፍተኛ መሰናክል የሆነው ማሞ ምህረቱ የሚመሩት ብሄራዊ ባንክ መሆኑ ይታወቃል። የአገሪቱ ኢኮኖሚ በተዘው በጀት ዓመት በ8 ነጥብ 45 በመቶ ያድጋል ብሎ ተብሎ እንደሚጠብቅም በቀን ሁለትና ሶስት መመሪያ የሚያስተላልፈው የብሄራዊ ባንክ ገዢው በዶላር ተከፋዩ አቶ ማሞ ጠቅሰዋል። አቶ ማሞ ምህረቱ ሃገሪቷን የአለም ባንክ እና የአይ ኤም ኤፍ ባሪያ ካደረጉ በኋላ ደምወዝ የሚከፈላቸው ከአለም ባንክ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኤርትራ በያዘቻቸው ሦስት የአዘርባጃን መርከቦች ላይ ምርመራ እያደረገች መኾኗ ታወቀ

ኤርትራ ባለፈው ጥቅምት ወር በያዘቻቸው ሦስት የአዘርባጃን መርከቦች ላይ ምርመራ እያደረገች መኾኗን የአዘርባጃን ጋዜጦች ዘግበዋል። በመርከቦቹ 18 የአዘርባጃን ዜጎችን ጨምሮ 24 መርከበኞች እንደሚገኙ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ሦስቱ መርከቦች በኤርትራ የባሕር ኃይል ቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ከስዊዝ ካናል ወደ አቡዳቢ በመጓዝ ላይ ሳሉ በአስቸጋሪ የአየር ኹኔታ ሳቢያ ወደ ኤርትራ ባሕር ክልል በመግባታቸውና ከኤርትራ ባሕር ኃይል ጋር የተሟላ ግንኙነት ሳያደርጉ በመቅረታቸው እንደነበር ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የአዘርባጃን ባለሥልጣናት መርከቦቹን ለማስለቀቅ አዲስ አበባ በሚገኘው የኤርትራ ኢምባሲና በሌሎች የግንኙነት መስመሮች በኩል ጥረት ማድረጋቸውን ቀደም ሲል ገልጸው ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የሚከለክለውን መመሪያ አገደ

በትግራይ ክልል የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የሚከለክለውን መመሪያ ትናንት ማገዱን የሙስሊም ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ከትምህርት የታገዱ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ያዘዘው ፍርድ ቤቱ፣ በሂጃብ ምክንያት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ያገዱ ትምህርት ቤቶችም ጥር 16 ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሠጡ ማዘዙን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት እገዳው እንዲነሳ ክስ መመስረቱን ባለፈው ሳምንት ገልጦ ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ደኅንነት አካላት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጽሙት ወከባ አሳስቦናል! ( 50 የመብት ተሟጋች ድርጅቶች)

50 አሕጉራዊና ዓለማቀፍ መንግሥታዊ ያልኾኑ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት የዜጎችን የመደራጀት መብት ለማክበር ቁርጠኝነቱን እንዲያረጋግጥ ትናንት በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል። የደኅንነት አካላት በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚፈጽሙት ወከባ አሳስቦናል ያሉት ድርጅቶች፣ አፈናው ፈጽሞ “ተቀባይነት የሌለው” እና አንዳንድ አገራትን “መጠነ-ሰፊ ግጭት ውስጥ የከተተ” አካሄድ ነው በማለት አውግዘዋል። መንግሥት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች፣ በአገሪቱ “ያለ ፍርሃት” እና “ያለ ገደብ” ሥራቸውን እንዲያከናውኑ እንዲፈቅድ፣ የሲቪክ ምኅዳሩን ከሚያጠቡ ርምጃዎች እንዲቆጠብ፣ የመብት ተሟጋቾችን ጥበቃ ተቀዳሚ ተግባሩ እንዲያደርግና በሲቪል ማኅበራት ላይ የጣለውን እገዳ እንዲያነሳም ድርጅቶች ጠይቀዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሠራተኛ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር የሚፈጸመው ሕግን ባልተከተለ መንገድ ነው ( የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች )

የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች፣ በኩባንያው ውስጥ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የሠራተኛ የደረጃ ዕድገትና ዝውውር የሚፈጸመው ሕግን ባልተከተለ መንገድ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለዋዜማ ገልጸዋል። የሠራተኛ ዕድገትና ዝውውር ይፋዊ ማስታወቂያ ወጥቶ በውድድር መኾኑ ቀርቶ፣ በሃላፊዎች ውሳኔ ብቻ እየተፈጸመ እንደኾነ ሠራተኞቹ ተናግረዋል። ባኹኑ ወቅት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የተቋሙ ቅርንጫፍ የሚሠራ ሠራተኛ ለደረጃ ዕድገት ከተማዋ ውስጥ ባለ ሌላ ቅርንጫፍ መወዳደር የማይችልበት ኹኔታ እንደተፈጠረም ዋዜማ ያነጋገረቻቸው ሠራተኞች ጠቅሰዋል። ዋዜማ በጉዳዩ ዙሪያ የኩባንያው የሠራተኛ ማኅበር ፕሬዝዳንት ካሳሁን ሰቦቃ ማብራሪያ እንዲሠጧት ጠይቃ የነበረ ቢኾንም፣ ካሳኹን ማብራሪያ ለመስጠት በቅድሚያ የሥራ አስፈጻሚው ውሳኔ ያስፈልጋል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኦቪድ ሪል ስቴት ………… በዚህ ዘመን የህዝብን እውነት እና የሚድያን ስራ ማፈን አይቻልም።

ኤሊያስ መሰረት ኦቪድ የተባለው ድርጅት የዛሬ አመት ገደማ በሸጣቸው ቤቶች ላይ ቅሬታ ያላቸው ቤት ገዢዎች ለመሠረት ሚድያ ተከታታይ መረጃ ሲልኩ ነበር የቅሬታቸው መሰረትም ቃል በተገባላቸው መሰረት የቤቶቹ ግንባታ እየተካሄደ አይደለም የሚል ነበር፣ ለዚህም የሳይቶቹ የምስል እና የቪድዮ ማስረጃ አለ። ይሁንና በዚህ ያልተደሰቱት ኦቪዶች ሁለት ነገር አደረጉ: አንደኛው የመሠረት ሚድያ ፕላስ (Meseret Media+) የዩትዩብ ቻናል ሞኒታይዜሽንን ሪፖርት አርገው አዘጉ፣ በሌላ በኩል እኔን አናገሩ። ቻናሉን ማዘጋታቸው ትክክል እንዳልሆነ ነግሬያቸው (እንዳዘጉ የተናገሩበት የድምፅ ቅጂ/ሪከርድ ሙሉው አለ) በዜናው ላይ ማንኛውም አይነት ቅሬታ እና ትክክል አይደለም ብለው የሚያስቡት ነገር ካለ ላኩት እና አጣርተን ስህተት ከሆነ ሌላ የእርምት ዜና እንሰራለን አልኩ። እሺ ተባብለን ከጨረስን በሗላ ግን “በአምስት ቀን ውስጥ የመረጃዎቻችሁን ምንጭ አምጡ፣ ወይም እንከሳለን” ብለው ማስፈራርያ መሰል ‘ድንፋታ’ በኢሜይል ላኩ 🙂 ማስፈራርያው መሠረት ሚድያ ላይ እና ኢትዮ ፎረም ላይ እንደሆነ በሶሻል ሚድያ ገፆቻቸው ፅፈው አየሁ። የሚገርመው ዜናው መሠረት ሚድያ ላይ ከወጣ በኋላ ቤት ገዢዎችን ጠርተው መዘግየት የተፈጠረው በአዲሱ ‘ሴት ባክ’ ህግ ወዘተ እንደሆነ እና በቅርቡ ግንባታ እንደሚጀመር ራሳቸው ተናግረዋል። ዜናው ውሸት ነው ብለው ካሰቡ ቀላሉ ማስረጃ በዜናው ላይ የተጠቀሱትን የጉለሌ እና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሳይቶቻቸውን በምስል እና ቪድዮ አስደግፈው አቅርበው የመሠረት ሚድያ ዜናን ውሸት ማጋለጥ ነበር፣ ግን አላረጉም። ሁሉ በእጃቸው እና በደጃቸው የሆነ መስሏቸው ይሁን መንግስት አዲስ አበባ ሊያገኝ ያልቻላቸውን ጋዜጠኞች በዚህ በባለቤትነቱ ዙርያ ብዙ ህዝብ
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

በቤኒሻንጉል ጉምዝ አንድ ወጣት “የዐይንህ ቀለም አላማረንም” ብለው በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለውታል

እናት ፓርቲ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ታጣቂዎች የመተከል ዞን ዋና መቀመጫ ወደኾነችው ግልገል በለስ ከተማ ታኅሣስ 24 ቀን እኩለ ቀን ላይ ይገባ የነበረ አንድ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ኬላ ላይ በማስቆም አንድ ወጣት “የዐይንህ ቀለም አላማረንም” ብለው አስወርደው በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለውታል በማለት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አውግዟል። ፓርቲው፣ ታጣቂዎቹ በእርቅ ስም ከጫካ ተመልሰው ባካባቢው ከሚገኝ ካምፕ የተቀመጡ ቡድኖች ናቸው በማለት ከሷል፡፡ ግድያውን የተመለከቱ ተሳፋሪዎች በከተማው ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት መረጃውን አድርሰው እንደነበርና ኾኖም የሠራዊቱ አባላት ትዕዛዝ አልተሰጠንም በማለት ርምጃ እንዳልወሰዱ መስማቱንም ፓርቲው ጠቅሷል። ፓርቲው፣ በቡለን ወረዳ ቡለን ከተማ ታጣቂዎች ትናንት ንጋት ላይ ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው አንድ ሰው መግደላቸውንና ነዋሪውን ከፍተኛ ሥጋት ውስጥ መክተታቸውንም አመልክቷል። ፓርቲው፣ መንግሥት በሰላም ስም ይፈጽመዋል ያለውን ሸፍጥ እንዲያቆም፣ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡና ግልገል በለስ ከተማ መግቢያ ላይ ያለው ኬላ እንዲነሳ ጠይቋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት እየፈጸሙባቸው ይገኛል።

” ገንዘቡን ካላገኘን በቀር እንዳንደውልላቸው አስጠንቅቀውናል። በጣም ተጨንቀናል ” – ቤተሰብ በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት እየፈጸሙባቸው ይገኛል። ከእነዚህ ታጋቾች መካከል የሀገራችን ልጅ ነሒማ ጀማል አንዷ ናት። ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል፤ ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው። ‘ ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ‘ የተሰኘው ተቋም በኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች ‘ ኩፍራ ‘ በምትባለው የሊቢያ ግዛት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ። ነሒማ በፎቶዎቹና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታያለች። የነሒማ ጀማል ቤተሰቦች ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ተልኮላቸው የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል። የነሒማ እህት ኢፍቱ ጀማል ፤ ነሒማ ከ8 ወራት በፊት ከሻሸመኔ ከተማ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ሊቢያ እንደተሰደደች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ተናግራለች። ” ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ይልኩልናል። ስትሰቃይ ያሳዩናል። የድምፅ መልዕክትም ልከውልናል። እህታችን ‘ ገንዘብ ላኩላቸው ካልሆነ ይገድሉኛል ‘ ስትል ይሰማል ” ስትል አስረድታችለች። ነገር ግን ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ አጋቾቹ የጠየቁትን ገንዘብ የመላክ አቅም የለውም። ‘ ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ ‘ የተባለው ሊቢያ የሚገኙ ስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ተቋም እንዳለው የ20 ዓመቷ ነሒማ ጀማል ባለፈው ግንቦት ሊቢያ ከገባች ከቀናት በኋላ ነው በታጣቂዎቹ እጅ ውስጥ የገባችው። በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ስቃይ ሲደርስባት እና ስትደበደብ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ለቤተሰቦቿ ተልከዋል። ኢፍቱ እንደምትለው ቤተሰቡ የተጠየቀውን ገንዘብ ለማሰባሰብ እርዳታ ቢጠይቅም እስካሁን ድረስ ሊሞላላቸው አልቻለም። ቤተሰቡ የነሒማን ድምፅ ከሰማ ሁለት ሳምንት እንዳለፈው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቀይ ባሕር አዋሳኝ ያልኾነ አገር ቀይ ባሕር ላይ ወታደራዊ ወይም የባሕር ኃይል እንዲያቋቁም አይፈቀድለትም !

የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ባደር አብደላቲ፣ የቀይ ባሕር አዋሳኝ ያልኾነ አገር ቀይ ባሕር ላይ ወታደራዊ ወይም የባሕር ኃይል እንዲያቋቁም ሊፈቀድለት እንደማይችል ተናግረዋል። አብደላቲ ይህን የተናገሩት፣ ከኤርትራና ሱማሊያ አቻዎቻቸው ጋር ካይሮ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ ቅዳሜ’ለት የመጀመሪያ ስብሰባቸውን ካካሄዱ በኋላ፣ የሦስትዮሽ ስብሰባቸውን በየጊዜው ለማካሄድ ተስማምተዋል። ቀጣዩ የሚንስትሮች ስብሰባ ሞቃዲሾ ውስጥ እንደሚካሄድ የገለጡት አብደላቲ፣ ኹለተኛውን ዙሪያ የመሪዎች ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑንም ጠቁመዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በየፍርድ ቤቱ የሚሰጡ ውሰኔዎች ደካማ፣ ሕጋዊ ውሳኔ ብቻ የመወሰን ስልጣን ስላላቸው ብቻ የሰጧቸው ውሳኔዎች ናቸው

“ በየፍርድ ቤቱ የሚሰጡ ውሰኔዎች ደካማ፣ ሕጋዊ ውሳኔ ብቻ የመወሰን ስልጣን ስላላቸው ብቻ የሰጧቸው ውሳኔዎች ናቸው ” – የሕግ ባለሙያ ጥጋቡ ደሳለኝ ጠበቃና የሕግ ባለሙያ ጥጋቡ ደሳለኝ፣ በሴቶችና ህፃናት የወሲብ ጥቃት ፈጻሚዎች ላይ “ ከ15 እስከ 25 ዓመት ጽኑ እስራት ” የሚለው ድንጋጌ ችግሩ እንዲስተካከል ስላላደረገ መሻሻል እንዳለበት ተናገሩ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጠበቃና የሕግ ባለሙያው ጋር ያደረገውን ቆይታ ያንብቡ። Q. ህፃናትን የደፈሩ የስጋ ዝምድና ያላቸው ግለሰቦች ላይ ፍ/ቤቶች የሚጥሉት ቅጣት በማነሱ ድርጊት ፈጻሚዎችን “ አይዟችሁ በርቱ የሚል እየሆነ ነው ” የሚሉ ትችቶች ተበራክተዋል፣ ከሕጉ አንጻር በፍርድ አሰጣጥ ምን መስተካል አለበት ? አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ፦ “ በወንጀል ሕጉ ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የቅጣት ደረጃ ‘ከ እስከ’ የሚል የግርጌና የራስጌ አይነት የቅጣት ስርዓት ነው ያለው። ሰፊ ነው ክፍተቱ። ለምሳሌ እድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት የአስገደድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመ ሰው ከ15 – 25 የሚደርስ፤ ማፈን፣ ማታለል፣ ማነቅ አይነት ተደራራቢ ወንጀል ካለው  የእድሜ ልክም ሞትም ሊሆን ይችላል። እድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ የሆኑ ህፃናትና አጠቃላይ በሴቶች የሚፈጸም ወሲባዊ ጥቃት ከሆነ ደግሞ እንደ ድርጊቱ አፈጻጸም ከ5 ዓመት እስከ 25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲፈረድ የሚል ነው። ዳኞች 10፣ 15 ዓመት ቢፈርዱ ልክ ናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 79 መሰረት ዳኞች የሚሰጧቸው ውሳኔዎች ፍትሃዊ፣ ነጻና ገለልተኛ እንደሆነ ታሳቢ ይደረጋል። የእኛ አገር ዳኝነት በተጻፈ ሕግ ብቻ ነው
Posted in Amharic News, Ethiopian News

” ለ1,523 ቀናት ያህል በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን ” – ተፈናቃይ ወገኖች በመቐለ

” ለ1,523 ቀናት ያህል በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን ” – ተፈናቃይ ወገኖች ዛሬ ጥዋት በመቐለ ሰላማዊ ስልፍ ተካሂዷል። ሰላማዊ ሰልፉ ” በቃን ወደ ቄያችን መልሱን ” ባሉ የተፈናቃይ መጠለያዎች ውስጥ በሚገኙ ወገኖች አማካኝነት ነው የተደረገው። የመቐለ ሮማናት አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ ፓሊስ ከተሸከርካሪ እና ከእግረኞች እንቅስቃሴ ነፃ  እንዲሆኑ ተደርገው ነበር። በመቐለ እና ከመቐለ ውጪ ባሉት የተፈናቃይ መጠለያዎች የሚገኙ ወገኖች ” ይበቃል !! ” በሚል በሦስት አቅጣጫ ወደ ሮማናት አደባባይ ተሰባስበው ድምጻቸውን አሰምተዋል። ሰልፈኞች በሮማናት አደባባይ እንደደረሱ ፦ – ለ1523 ቀናት በፕላስቲክ ቤት መኖር ይብቃን ! – የፕሪቶሪያ ስምምነት በሙሉነት ይተግበር ! – ወደ ቤታችን መልሱን ! – ጦርነት እንጠየፋለን ፤ ሰላም እንሻለን ! – ዓለም ድምፃችንን ስሚ ! – በመቀጠል ያለው የተፈናቃዮች ሞት ይብቃ ! – ህገ- መንግስት ይከበር !  … የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል። ተፈናቃዮቹ በተወካያቸው በኩል ባሰሙት መግለጫ ፥ በመላ ትግራይ የሚገኙ ተፈናቃዮች በረሃብ እና መድሃኒት እጦት እየሞቱ መሆናቸው ጠቅሰዋል። ለማሳያ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ወዲህ  ብቻ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የተፈናቃይ ማቆያ ጣብያዎች ይኖሩ የነበሩ ከ812 በላይ ወገኖች ህይወታቸው ማጣታቸው ገልፀዋል። መሰል ሰለማዊ ሰልፍ የዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት እንደሚኖር ተነግሯል። የዛሬው የማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ሰላማዊ ነበር። የተፈናቃይ ስልፈኞቹን ጥያቄ እና የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ ካለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ተከታትሎ ያቀርባል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሎስአንጀለስን ሞቅናት! (በእውቀቱ ስዩም)

ሎስአንጀለስን ሞቅናት! (በእውቀቱ ስዩም)ትናንትና ሎስአንጀለስ በእሳት ስትነድ፥ እኔ በአጋጣሚ ጓደኞቼን ለመሰናበት እዚያው ከተማ ውስጥ ነበርሁ፤ ሆሊውድ አካባቢ በእግሬ እየተንሸራሸርሁ ድንገት ቀና ብየ ሳይ፥ ከተማው እንደ ደመራ ይንቦገቦጋል፤ መጀመርያ ላይ ፥የዮዲት ጉዲትን ፊልም እየሰሩ ነበር የመሰለኝ፤ ብዙ ሳይቆይ የሳት አደጋ መኪና እየተብለጨለጨ ባጠገቤ አለፈ፤ነገሩ “ሲርየስ” መሆኑን ያወቅሁት፥ የሆሊውድ አክተሮች ልጆቻቸውን እንኮኮ አዝለው፥ የቤት እቃቸውን ባንሶላ ጠቅልለው፥ ሲራወጡ ስመለከት ነው ፤ ደንብ አስከባሪ የሚያባርራቸውን የመገናኛ ቦንዳ ሻጮችን አስታወሱኝ፤ ቻክኖሪስ ባንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛ ታዝሎ፥ ሳል እያጣደፈው ከቤቱ ሲወጣ አይቼ “እድሜ አተላ “ብየ ተከዝኩ::እያወካ እየተጋፋ ከሚሸሸው ሰው መሀል ተቀላቅየ መሮጥ ጀመርሁ፤ቀጣዩ ፌርማታ ላይ ትንፋሽ ለመሰብሰብ ቁጭ ባልሁበት፥ የሆነ ፖሊስ መጣና፤“Are you ok?” አለኝ፤“ እድሜ ልኬን ለፍቼ፥ እቁብ ጥየ ፥ ያፈራሁት ቤቴና ንብረቴ በእሳት ጋየ” ብየ መለስኩለት፤“ስራህ ምንድነው ?”መቸም በዚህ ሰአት ላይ ሊያጣራ አይችልም ብየ በማሰብ፥“ ቀን የጣለኝ የሆሊውድ አክተር ነኝ “ አልሁት፤“ምን ፊልም ላይ ሰርተሀል?””በማርቲን ሉተር ኪንግ የህይወት ታሪክ ዙርያ፥ በሚያጠነጥን ፊልም ውስጥ ከበድ ያለ ሚና ነበረኝ ” አልሁት፤ፖሊሱ አልተፋታኝም፤“ምን ሆነህ ነው የተወንከው?”“ ማርቲን ሉተርኪንግ ፥ ሁለት መቶ ሺህ ህዝብ ሰብስቦ ንግግር የሚያደርግበት ትእይንት ትዝ ይለሀል?” አልኩት፤“አዎ”“ ከህዝቡ መሀል አንዱን ሆኜ ተውኛለሁ፤ ፊልሙ ጀምሮ አንድ ሰአት ከሶሰት ደቂቃ ከአምሳ ሁለት ሰከንድ ላይ ራሱን እሚነቀንቀው ሰውየ እኔ ነኝ “ፖሊሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ወስዶ ከተፈናቃዮች ጋራ ቀላቀለኝ፤ የከተማው ከንቲባ ዘለግ ያለ ንግግር አደረጉ ፤” የተወደዳችሁ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በተያዙ የአገዛዙ ካድሬዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወስዷል ። – ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ/ ዳንግላ

ባንዳን የማፅዳት ስራችን ተጠናክሮ የሚቀጥል የየለት ተግባራችን ነው ‼️ በተያዙ የአገዛዙ ካድሬዎች ላይ አብዮታዊ እርምጃ ተወስዷል ። እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ የአዲሱ ትውልድ አቢዮት ከሰልፍ እስከ ሰይፍ በደረሰው ተጋድሎው ውስጥ ህዝባችንን በጠላትነት ፈርጀው የሀሰት ትርክት ነዝተው ሊያጠፋን ከተነሱ ጠላቶቻችን እኩል ምናልባትም አንዳንዴ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን በላይ ህዝባችንን ሁሉን አቀፍ መከራ ያደረሱበት ከህዝባችን ውስጥ የወጡ እና ለሆዳቸው ያደሩ ባንዳዎች እንደሆኑ በትግላችንን ያረጋገጥነው እውነታ ነው ። ብርጌዳችን በቀን 28/04/2017ዓ.ም በዳንግላ ወረዳ ጊሳ ቀበሌ ላይ ከጨፍጫፊው የብልፅግና ስርዓት ትእዛዝ ተቀብለው እና በአገው ሸንጎ መሩ የአዊ ዞን አስተዳደር በተሰጣቸው ተልኮ መሰረት ህዝባችንን ለዳግም ባርነት ለመዳረግ አለኝ የሚሉትን ሀይል አግተልትለው የገቡትን በአቶ ጌትነት ማረልኝ የቀድሞው የዳንግላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የተመራ የጥፋት ቡድን ላይ በወሰደው የተቀናጀ እርምጃ ይዘውት የገቡት አራጅ ሰራዊት ሙሉ ለሙሉ ሲደመሰስ አቶ ጌትነት ማረልኝን ጨምሮ አራት የአገዛዙ አመራሮች ከአንድ ሹፌራቸው ጋር ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በውጊያ መሀል ጥይት ጨርሰው ተማርከው እንደነበር በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ማሳወቃችን ይታወሳል ። ግለሰቦቹ በፋኖ ሲማረኩ የመጀመሪያቸው አይደለም ከዚህ በፊት የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ዳንግላ ከተማን በተቆጣጠረበት ወቅት በብርጌዳችን ተይዘው እና ምክር ተሰጧቸው በሀይማኖት አባቶች ፊት በፈጣሪያቸው እና በቤተሰቦቻቸው ምለው ድጋሚ ወደ ብልፅግና የጥፋት መንገድ ላይገቡ ተገዝተው በሰላም የተለቀቁ ቢሆንም በፈጣሪ ፊት የገቡትን ማህላ ክደው የብልፅግና ወንጌልን በመቀበል በተለያዩ መድረኮች ፋኖን ካለ ስሙ ስም ሲሰጡ በዳንግላ ከተማ እና በዙሪያው የአማራ ልጆች በግፍ
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች በምን ጉዳዮች ላይ መከሩ ፤ ምንስ ተስማሙ ?

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች በምን ጉዳዮች ላይ መከሩ ፤ ምንስ ተስማሙ ? የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ዛሬ በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል። ከውይይቱ በኃላ የጋራ መግለጫ ወጥቷል። ምን ተባለ ? – በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። – በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና ግንኙነት በማጠናከር ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል። –  የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ እና በየመዲኖቻቸው ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ውክል እንዲኖር ለማድረግ ተስማምተዋል። – መሪዎቹ ለቀጣናው መረጋጋት የሁለቱ ሀገራት የጋራ የእርስ በርስ እምነት ፣  መተማመን እና መከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል። – ቀጠናዊ ግንኙነቶችን ለማሻሻል፣ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር እና የጋራ እድገትን ለማስቀጠል በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል። – መሪዎቹ የጸጥታ ትብብር ማስቀጠልና ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል። በቀጠናው ፅንፈኛ ታጣቂ ሃይሎች እየፈጠሩ ያሉትን አሳሳቢና እየጨመሩ  ያሉ ስጋቶችን በመገምገም መሪዎቹ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር ለጸጥታ ተቋሞቻቸው መመሪያ ለመስጠት ተስማምተዋል። – በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ ላይ ተወያይተዋል ፤ አጽንኦትም ሰጥተዋል። የበለጠ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር በማድረግ የንግድ ልውውጥን ለማሳለጥ እና የጋራ ብልጽግናን ለመፍጠር የመሰረተ ልማት ትስስሮችን ለማስፋት ተስማምተዋል። – ለአንካራው ስምምነት በጓደኝነት እና በአብሮነት መንፈስ ቁርጠኝነታቸውን ዳግም ያረጋገጡ ሲሆን  በስምምነቱ ላይ የታቀዱትን የቴክኒክ ድርድሮችን ለማፋጠንም ተስማምተዋል።
Posted in Amharic News, Articles, Ethiopian News

በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ሰፊ መጋዘን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች ተይዘው ይገኛሉ ተባለ

ኢሰመኮ፣ በታኅሣሥ ወር ባደረጋቸው ክትትሎች በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ አጠገብ በሰፊ መጋዘን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች ተይዘው እንደሚገኙ አስታውቋል። ኢሰመኮ፣ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ቦታ የማስገባት ድርጊት መቀጠሉን እንደተረዳ ገልጧል። ወደ ማቆያ ማዕከሉ ከገቡት መካከል፣ በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ የእርሻ ጣቢያዎች ተወስደው እንዲሠሩ የተደረጉ እንደሚገኙበት የጠቀሰው ኢሰመኮ፣ ድርጊቱ የሰዎቹን ሰብዓዊ መብቶች የሚጥስ ነው ብሏል፡፡ የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሠለ፣ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በግዳጅ ወደ ማቆያ አስገብቶ መያዝ ወይም ያለፍቃዳቸው ወደተለያዩ አካባቢዎች መውሰድ ባስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል።
Posted in Ethiopian News

” ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ” – ቅዱስነታቸው

” ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ” – ቅዱስነታቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ። ቅዱስነታቸው ፤ በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ” ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ አባታዊ ጥሪ በድጋሚ እናስተላልፋለን ” ብለዋል። ቅዱስነታቸው ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግርና ጭንቀት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል። ” በትሕትና መንፈስ እርስ በርስ መገናዘብ ተፈጥሮ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል ታደርጉ ዘንድ አደራችን የጠበቀ ነው ” ብለዋል። በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በትግራይ ክልል ስለሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ በአባታዊ የሰላም ጥሪ መልዕክታቸው አንስተዋል። ” መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው ” ያሉት ቅዱስነታቸው ” ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን ” ብለዋል። በሌላ በኩል ቅዱስነታቸው በመሬት መንቀጥቀጥ እየተጨነቁ ላሉ እና ስለተጎዱ ልጆቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል። ” የመሬት መንቀጥቀጥ ባለበት አካባቢ እየተጨነቃችሁ ያላችሁ ልጆቻችን ረድኤተ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት የምታስባችሁ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች በወታደራዊ ካምፖ ውስጥ ኢ-ሰብዓዊ በኾነ አያያዝ እየተንገላቱ ይገኛሉ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ዞን በእስር ላይ የሚገኙ ከ450 በላይ የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች ከአንድ ወር በላይ በፖሊስ ጣቢያና በወታደራዊ ካምፖ ውስጥ ኢ-ሰብዓዊ በኾነ አያያዝ እየተንገላቱ ይገኛሉ ሲሉ የፋብሪካው ሠራተኞች ተናግረዋል። የፋብሪካው ሠራተኞች የታሠሩት፣ የፋብሪካው ይዞታ የኾነውን መሬት አርሳችሁ ለግል ጥቅማችሁ አውላችኋል ተብለው መኾኑን ምንጮች ጠቁመዋል። አብዛኞቹ ታሳሪዎች በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩና ፋብሪካው የማይጠቀምበትን ባዶ መሬት በእጃቸው እየቆፈሩ በቆሎና ሰሊጥ በመዝራት የተወሰነ ጥቅም ሲያገኙ የነበሩ እንደኾኑ ምንጮቹ ተናግረዋል። ፋብሪካው በመለዋወጫ እጥረትና በጸጥታ መጓደል ሳቢያ ለወራት ምርት እንዳቆመ ይገኛል።
Posted in Ethiopian News

“የፓርቲውን አባላት እና አመራሮች በማስፈራራትና በማሰር ትግሉን ማስቆም አይቻልም”- ኢሕአፓ

“የፓርቲውን አባላት እና አመራሮች በማስፈራራትና በማሰር ትግሉን ማስቆም አይቻልም”- ኢሕአፓ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ባወጣው መገለጫ በሐረር ክልል የሚገኙት አባሎቻቸው እና አመራሮች ያለ በቂ ምክንያት በጸጥታ ሀይሎች መወሰዳቸውን አስታውቋል፡፡ በዚህም በክልሉ የሚገኘውን ኢሕአፓ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራር የጸጥታ ሀይሎች ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው እንዳሰሯቸው እና ወደ ፍርድ ቤትም እንዳላቀረቧቸው ገልጿል፡፡ እንዲሁም እንደታሠሩ ለመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት መጠየቅ ይቻል የነበረ ቢሆንም ከጥቂት ቀናት በፊት ግን ከነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ አውጥተው ወዴት እንደወሰዷቸው አልታወቀም ተብሏል፡፡ በመሆኑም ሕገ መንግሥትን ማስከበር በሁሉም እርከን ላይ ከሚገኙ የመንግሥት ባለሥልጣኖች የሚጠበቅ ግዴታ ቢሆንም የብልጽግናው መንግሥት አገልጋዮች ሕጉን አላግባብ መጠቀማቸው እና ከስርዓት ውጪ መሆናቸው አሳፋሪ ነው ሲል ፓርቲው ኮንኗል፡፡ በተጨማሪም አባላቶቹ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ እና በፓርቲው አባሎች ላይ የሚደረገው ማስፈራራት፣ ማፈንና ማሰር በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ትራምፕ ቃለ- መሃላ በሚፈጽሙበት እለት ሰንደቃላማ ዝቅ ማለቱን አልወደዱትም።

የካርተር ሽኝት -ባንዲራ በግማሽ ዝቅ ማለቱ እና የተመራጩ ፕሬዚዳንት የትራምፕ ቅሬታ ትራምፕ ቃለመሃላ ሲፈፅሙ ሰንደቃላማዉ ዝቅ እንዳለ ይቆያል በ 100 ዓመታቸዉ በቅርቡ በሞት የተለዩት 39ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር አስክሬን፤ የቀድሞ እና ተተኪ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች በተገኙበት በትናንትናዉ እለት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ብሔራዊ ካቴድራል ሽኝት ተደረገለት። በሽኝት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ አዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ፣ ቢል ክሊንተን እና ባራክ ኦባማ ተገኝተዋል። የቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና አዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጎን ለጎን ተቀምጠዉ ሲያወሩ የሚታይበት ክስተት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። የቀድሞዉን ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተርን ሞትን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ ሰንደቅ ዓላማ በግማሽ ዝቅ ብሎ እየተዉለበለበ ነዉ። ይህ ደግሞ ለሰላሳ ቀናት ይቀጥላል። በአሜሪካ ከጎርጎረሳዉያኑ 1954 ዓም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለዉ አንድ ፕሬዚዳንት ሲሞት ለ30 ቀናት ሰንደቅ አላማ በግማሽ እየሚዉለበለብ የሚደረግበት የህግ አሰራር፤ ትራምፕን አስቆጥቷል። ቃለ- መሃላ በሚፈጽሙበት እለት ሰንደቃላማ ዝቅ ማለቱን አልወደዱትም። ትራምፕ የፊታችን ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም 45 ኛዉ የዩናይትድ ስቴትስ በመሆን ቃለ-መሃላ እንደሚፈጽሙ ይታወቃል። ትራምፕ ቃለ መሃላ በሚፈጽሙበት እለት የአሜሪካ ሰንደቅ አላማ በግማሽ መዉለብለቡን ይቀጥላል። ይህን ዉሳኔ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለመቀየር ሃሳብ እንደሌላቸዉ መናገራቸዉም ተነግረዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዋነኛነት በነዳጅ ስርቆትና ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩት የመንግስት ባለስልጣናት መሆናቸው የፓርላማው አባላት ተናገሩ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓት አዋጅን በኹለት ተቃውሞና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ ባጸደቀበት ወቅት፣ በሕገወጥ የነዳጅ ግብይት ውስጥ የመንግሥት ባለሥልጣናት እጅ እንዳለበትና የሕጎች ተፈጻሚነት ዝቅተኛ እንደኾነ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። አዋጁ፣ ከመንግሥት የዋጋ ተመን ውጪ ነዳጅ መሸጥ ወይም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል ከ3 እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራትና ከ300 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብር እንደሚያስቀጣ ደንግጓል። የነዳጅና ኢነርጅ ባለሥልጣን፣ አዋጁ የማደያዎችን የነዳጅ ግብይት በዲጅታል ክፍያ ብቻ በማድረግ ከታሪፍ በላይ የሚፈጸሙ ሽያጮችን ለመቆጣጠር ያግዛል ብሏል። አዋጁ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ የማድረግን ሥልጣን ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ሠጥቷል። ባንጻሩ የነዳጅና ኢነርጅ ባለሥልጣን የነዳጅ ዋጋ ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን አልተሰጠውም። ባኹኑ ወቅት በአገሪቱ 500 ወረዳዎች የነዳጅ ማደያ እንደሌላቸውም በዚኹ ወቅት ተገልጧል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብይ አሕመድ ተቃዋሚ ኃይሎችን ባለሃብቶችን እና ሌሎች አካላትን ለማጥቃት ያዘጋጀውን አዋጅ አጸደቀው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ 10 ዓመት ወደኋላ ሂዶ ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን የመመርመርና የመውረስ ሥልጣን ለመንግሥት የሚሰጠውንና በርካታ ትችቶች ያስተናገደውን አዋጅ ዛሬ በሦሰት ተቃውሞና በአራት ድምጸ ታቅቦ አጽድቆታል። የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች፣ አዋጁ ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የማይፈለጉ ባለሃብቶችን፣ የኃይማኖት መሪዎችንና ግለሰቦችን ለማጥቃት የተዘጋጀ ነው በማለት ተቃውመውት ነበር። አዋጁ ቢያንስ በነጋሪት ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ብቻ ተግባራዊ እንዲደረግ የጠየቁ የተቃዋሚ የምክር ቤት አባላትም ነበሩ። አዋጁ፣ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙት ዜጎች ላይ ጭምር ያነጣጠረ ነው፤ አስፈጻሚ አካላትም አዋጁን ለማስፈጸም አቅም የሌቸውም የሚሉ ትችቶችም ተንጸባርቀዋል። የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በበኩሉ፣ አዋጁ ሃብት የማፍራትና ንብረት የማውረስ ሕገመንግሥታዊ መብትን አይቃረንም በማለት ለትችቶቹ ምላሽ ሰጥቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

” ሰማይ ላይ ያየነዉ እንግዳ ነገር ፍርሀት ዉስጥ ጥሎናል ” – ነዋሪዎች

” ሰማይ ላይ ያየነዉ እንግዳ ነገር ፍርሀት ዉስጥ ጥሎናል ” – ነዋሪዎች ዛሬ ምሽት በበአርባ ምንጭ ፣ ወላይታ ሶዶ ፣ ቡርጂ ፣ ሱሮ ባርጉዳ (ምዕራብ ጉጂ ዞን) እና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በሰማይ ላይ የታየዉ ተምዘግዛጊ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ነገር ፍርሃት አንደጫረባቸዉ የአካባቢው ነዋሪዎችተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ” ምሽት 2 ሰዓት ገደማ ሮኬት መሳይ ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በሰማይ ቅርብ ርቀት ወደ ደቡብ አቅጣጫ መጓዙን አስተዉለናል ” ብለዋል። ” አልፎ አልፎ እንደሚስተዋሉ ተወርዋሪ ኮከቦች ቶሎ ታይቶ የሚጠፋና በፍጥነት የሚጓዝ አለመሆኑ ነዉ ፍርሃት የጫረብን ” ያሉን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ” በርከት ያለ ህዝብ ሰማይ ሰማዩን እያዬ እየተጠባበቀ ይገኛል ” ብለዋል። ይኸው ተቀጣጣይ ብርሃናማ ነገር በኢትዮጵያ አልፎ በኬንያ ሰሜናዊ ምስራቅ አካባቢዎች እንዲሁም በኬንያ ሞያሌ በኩብ ታይቷል። ለመሆኑ ነገሩ ምንድነው ? በሚል የዘርፉን ጉዳይ ወደሚከታተሉ አካላት ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ ብናደርግም ለጊዜው አልተሳካም። ስልክም አያነሱም። የባለሙያዎችን እና የዘርፉን ጉዳይ የሚከታተሉ ተቋማት ስልክ ተነስቶ መረጃው እንደደረሰን እናቀረባለን። ሲሆን ሲሆን ለእኛ ሀገር እንዲህ ያለ ክስተት ሲያጋጥም እንዲሁም ዜጎች ግርታ ውስጥ ሲገቡ ወደ ሚዲያ ወዲያው ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ነገሩን ግልጽ ማድረግ ይገባ ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤርትራ መንግሥት ቀይ ባሕር ላይ ሦስት የአዘርባጃን መርከቦችን እንዳገተ ተሰማ

የኤርትራ መንግሥት ቀይ ባሕር ላይ ሦስት የአዘርባጃን መርከቦችን እንዳገተ የአዘርባጃን ባለሥልጣናት ማስታወቃቸውን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኤርትራ 18 የአዘርባጃን ዜጎች የኾኑ የመርከብ ሠራተኞችን የያዙ ሦስት መርከቦችን ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ ገደማ በቁጥጥር ሥር ያዋለችው፣ መርከቦቹ ከስዊዝ ካናል ወደ አቡዳቢ በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደኾነ የአዘርባጃን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መናገሩን ዘገባዎቹ ገልጸዋል። በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ መርከቦቹ ወደ ኤርትራ ሉዓላዊ የባሕር ግዛት ገብተው እንደነበርና ይህም ለኤርትራ ባለሥልጣናት ቀደም ብሎ ተነግሯቸው እንደነበርም ሚንስቴሩ ገልጧል። ሚንስቴሩ፣ መርከቦቹንና ሠራተኞቻቸውን ለማስለቀቅ በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ ባለሥልጣናት ጋር እየተነጋገረ መኾኑን ጠቅሷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዛሬ ይጀመራል ተብሏል

የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዛሬ ዓርብ የአክሲዮን ሽያጭና ግዢ ግብይቱን በይፋ እንደሚጀመር መስማቱን ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የሚሠማሩ ባለሃብቶች የውጭ ምንዛሬ ገቢያቸውን በቀላሉ ከአገሪቱ እንዲያስወጡ የሚፈቅዱ ሕጎችን እንደቀረጸና ኾኖም ኩባንያዎች በአገሪቱ ሊኖራቸው የሚችለውን የኢንቨስትመንት የቆይታ ጊዜ እንደሚወስን የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በአዲሱ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚያቀርቡ ጥላሁን መጠቆማቸውንም የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል። ኢትዮጵያ፣ አብዮቱ ከመፈንዳቱ በፊት ለ14 ዓመታት የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ እንደነበራት አይዘነጋም።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

ተከስቶ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአዋሽ 23 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲሆን የጀርመኑ የጂኦሳይንስ ሪሰርች ማዕከል መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 5.0 መመዝገቡን አሳውቋል። የአሜሪካ ጃኦሎጂካል ሰርቬይ ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.9 መለካቱን አመላክቷል። ንዝረቱ አዲስ አበባ የተለያዩ ሰፈሮች ተሰምቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ባንኮች አዳዲስ ቅርንጫፎችን መክፈት እና አዳዲስ ሰራተና መቅጠር አቆሙ

ንግድ ባንኮች ከተያዘው ዓመት መግቢያ ጀምሮ የሚከፍቷቸው ቅርንጫፎች ቁጥር በእጅጉ መቀነሱን ታውቋል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ይልቅ ነባር ቅርንጫፎቻቸውን እያጠፉና የሠራተኛ ቅጥር እያቆሙ መኾኑን  የባንኮቹ ምንጮች ገልጸዋል። ባንኮች ቅርንጫፍ መክፈት ያቆሙት፣ ወጪያቸውን ለመቀነስና ወይም አገልግሎታቸውን ዲጅታል ለማድረግ በማቀዳቸው ነው ተብሏል። ኹሉም ባንኮች፣ አዳዲስ የሠራተኞች ቅጥር እያወጡ እንዳልሆነ ነግረውናል። ለአብነትም፣ አቢሲኒያ ባንክ ባለፉት ኹለት ዓመታት አዳዲስ ሠራተኞችን ያልቀጠረ ሲኾን፣ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታትም ላለመቅጠር ዕቅድ መያዙን የባንኩ ምንጮች ተናግረዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአክሱም በትምሕርት ቤት ሂጃብ አትልበሱ መመሪያ ጭቅጭቁ ወደ ፍርድ ቤት ሄደ

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የጣለውን እገዳ ለማስነሳት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱን ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመፍታት ረገድ ደብዳቤ ከመጻፍ ያለፈ ውጤታማ ሚና አልተጫወተም ያለው ምክር ቤቱ፣ በሂጃብ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የመቀመጥ ዕድል ተነፍጓቸዋል በማለት ከሷል። እገዳው የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ብቻ ሳይኾን፣ ባጠቃላይ የሴቶችን ሰብዓዊ መብት የጣስ ድርጊት ነው በማለትም ምክር ቤቱ እገዳውን በድጋሚ አውግዞታል። የትምህርት ቢሮው ችግሩን በጥቂት ቀናት ውስጥ ካልፈታ፣ ቀጣይ ሕጋዊ ርምጃዎችን እንደሚወስድ ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት አስጠንቅቆ ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኦሮሚያ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ካቢኔ አመራሮች ወደ ወታደራዊ ማዕከላት ከተቱ

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እያለ የሚጠራው አማጺ ቡድን፣ የኦሮሚያ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ካቢኔ አመራሮች ለመንግሥት ኃይሎች ወታደራዊ ዘመቻ የሎጅስቲክ ድጋፍ ለመስጠት ወደ ወታደራዊ ማዕከላት መክተታቸውን ተረድቻለኹ ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ቡድኑ፣ ታጣቂዎቹ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ወረዳ የምትገኘውን ጋርቦ ከተማ ትናንት መቆጣጠራቸውንም ገልጧል። ቡድኑ፣ ታጣቂዎቹ በሰዲን ሶዶ ወረዳ ሐርቡ ጩሉሌ ከተማን ጭምር ተቆጣጥረው፣ በከተማዋ ውስጥ በወታደራዊ ማዕከላት ውስጥ ከትመው የነበሩ የመንግሥት የበታች አመራሮችን ማርከዋል ብሏል። ኾኖም ቡድኑ የጠቀሳቸውን ከተሞች ስለመቆጣጠሩም ኾነ በወታደራዊ ዘመቻ ተሳትፈዋል ያላቸውን የአካባቢውን አመራሮች ስለመማረኩ ለጊዜው ከነጻ ምንጭ አልተረጋገጠም።
Posted in Ethiopian News

የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ የቢትኮይን ማዕከል ለመግዛት ከስምምነት ደረሰ

ቢ አይ ቲ ማይኒንግ የተባለው የቻይና ኩባንያ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በ14 ሚሊዮን ዶላር የቢትኮይን ማዕከል ለመግዛት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት መፈጸሙን የቻይና የዜና ምንጮች ዘግበዋል። የቢትኮይን ዲጂታል ማዕከሉ 51 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም እንደሆነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ በዘርፉ ሲሠማራ፣ ከአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት ውጭ በውጭ አገር ያለው ኹለተኛው ማዕከሉ ይሆናል ተብሏል። ኩባንያው ኢትዮጵያ ውስጥ ሙዓለ ንዋዩን ለማፍሰስ ከመንግሥት ጋር ስምምነት የተፈራረመው፣ የአገሪቱ ኤሌክትሪክ ዋጋ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲወዳደር በአንጻራዊነት ርካሽ በመኾኑ እንደኾነ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። ማዕከሉ፣ 18 ሺሕ ያህል የቢትኮይን ማቀነባበሪያ ማሽኖች እንደሚኖሩትና ኩባንያው አሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ ውድድር ከገጠመው ማዕከሉ አሮጌ ማሽኖችን በመንቀል ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያዛውርም በዘገባዎቹ ላይ ተገልጧል። የቢትኮይን ማገበያያ ማዕከላት የኤሌክትሪክ ፍጆታቸው እጅግ ከፍተኛ እንደኾነ ይነገራል።
Posted in Ethiopian News