የአባላቶቹ መልቀቅ ያስደነገጠው ኢዜማ የደበቀውን “ያለፉት አምስት ዓመታት የፖለቲካ ሁኔታዎች ግምገማ” ሰነድ ይፋ ሊያደርግ ነው።

የአባላቶቹ መልቀቅ ያስደነገጠው ኢዜማ የደበቀውን “ያለፉት አምስት ዓመታት የፖለቲካ ሁኔታዎች ግምገማ” ሰነድ ይፋ ሊያደርግ ነው።
Imageየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴ መጋቢት 02/2015 ዓ.ም. ባደረገው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ በሥፋት ለማጥናት፣ በተጨማሪም እንደሀገር እየሄድንበት ያለውን የፖለቲካ አካሄድ እና በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ያሉ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታን ቆም ብሎ በመገምገም ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎቻችንን ማስመር እንዲቻል የጥናት ግብረ ኃይል እንዲቋቋም፣ ግኝቱንም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርብ ውሳኔ ማሣለፉ ይታወሳል።
ግብረ ኃይሉ የሃገራችንን የአምስት ዓመት ጉዞ በስፋትና በጥልቀት በመፈተሽ እንደዚሁም ኢዜማ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ያለፈበትን አራት የትግል ዓመታት እንደሀገር አሁን ከደረስንበትና ከተደቀኑብን አደጋዎች አንፃር ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶችን በሰከነ መንፈስ ተንትኖ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የሚያሣይ “ያለፉት አምስት ዓመታት የፖለቲካ ሁኔታዎች ግምገማ” ሰነድ አዘጋጅቶ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም. በብሔራዊ ሥራ አሥፈፃሚ ኮሚቴው ጸድቋል።
ሰነዱ በተለያየ ደረጃ ካሉ አባላት ጋር ውይይት እንደሚደረግበት መገለፁ የሚታወስ ሲሆን ከነገ ግንቦት 19/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከፓርቲው የፓርላማ አባላት፣ የብሔራዊ ህግ ተርጓሚና አሥፈፃሚ ኮሚቴ፣ ኦዲት ኮሚቴ፣ በፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስር ከሚገኙ ቋሚ ኮሚቴ እና ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ አባላት ጋር በሰነዱ ላይ ውይይት ያደርጋል።
ይህ ውይይት በቀጣይ ሳምንታት ከዞን ምክርቤቶች እና ከምርጫ ክልሎች ከተውጣጡ አመራር እና አባላት ጋር የሚደረግ ይሆናል።