አምባሳደር ሱሌይማን – የታገሉትና የታዘቡት የተበላሸ አሰራር

አምባሳደር ሱሌይማን – የታገሉትና የታዘቡት የተበላሸ አሰራር

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ናቸው፡፡በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ዘመናት በተለይም በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር በነበሩበት ወቅት ያጋጠማቸውን የሥራ ላይ ችግሮች፣የታዘቡትንና የታገሉትን የሌብነት ሂደት እና በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለመጠይቅ ።

አዲስ ዘመን፤ አምባሳደር ሱሌይማን ማን ናቸው ?

አምባሳደር ሱሌይማን፤ ውልደቴና ዕድገቴ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮፈሌ ወረዳ ነው፡፡ ከደሀ አርሶ አደር የተገኘሁ ልጅ ነኝ፡፡ አካባቢው በወቅቱ የትምህርት ዕድል ያገኘ አልነበረም፡፡ እኔ ለትምህርት በደረስኩበት ወቅት የስውዲሽ ሚሽን በመንደሬ መሰረተ ትምህርት ይከፍታል፡፡ በዛን ጊዜም የሰባት ዓመት ልጅ ነበርኩ፡፡ ከብት ማገዱን ትቼ በዕድሉ ለመጠቀም ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡

ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ ጥያቸው የሄድኳቸው ከብቶችም የተሰጣ እህል በልተው፣ ማሳ ገብተው ጥፋት በማድረሳቸውም ለቤተሰቤ አቤቱታ ቀረበ፡፡ በዚህ ምክንያትም ከቤተሰቤ ጋር አጋጨኝ፡፡ እኔም በትምህርት ቤቱ የተመደበውን አዲሱን አስተማሪያችንን በአማላጅነት ይዤ ቤተሰቤ ጋር ሄድኩኝ፡፡ መምህሬም ከቤተሰቤ ጋር አስማማኝ፡፡ በትምህርቴ እንድቀጥልም መንገድ ጠረገልኝ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ትምህርቴን አላቋረጥኩም፡፡

እስከ ስድስተኛ ክፍል ስዊድሽ ሚሽን፣ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴንም በአቅራቢያ በሚገኝ የመንግሥት ትምህርት ቤት ተማርኩኝ፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ወደ አሰላ በመጓዝ እስከ 12ኛ ክፍል አጠናቀቅኩ፡፡ በመቀጠልም ወደ ውትድርና ገባሁ፡፡ በመጀመሪያ በስፔሻል ፎርስ ተቀጥሬ ፍቼ ከተማ ስልጠና ላይ እያለሁ በካዴትነት ተመለመልኩ፡፡ በ1970 ዓ.ም በጦር ትምህርት ቤት እያለሁ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ መጥቶ ተፈትኜ ጥሩ ውጤት ባገኝም በዛን ጊዜ አልገፋሁበትም፡፡ ወደ ትምህርት ዓለም የተመለስኩት በ1988 ዓ.ም ነው፡፡

አዲስ ዘመን፡- ወደ ትምህርት ዓለም ከተመለሱ በኋላ የነበሩበት ቆይታስ?

ሙሉ ቃለ ምልልሱን ለማንበብ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡፡

http://press.et/?p=802#


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE