በሶሪያ በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ22 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ደዌላ ሰፈር ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ኤሊያስ ቤተክርስትያን ላይ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 22 ሰዎች ሲሞቱ ከ63 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ሲሆን እሁድ በጸሎት ሰዓት ምዕመናን ባሉበት ነው።

የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በሰጡት መግለጫ ፦

“ISIS አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው አጥፍቶ ጠፊ በዋና ከተማው ደማስቆ ደዌላ አካባቢ በሚገኘው የቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት ተኩስ ከከፈተ በኋላ በተቀጣጣይ ፈንጂ ራሱን አጠፋ” ሲሉ ሁኔታውን ገልጸዋል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ተሰግቷል።

Source : SANA