ኢሕአፓ የአብይ አሕመድን ስብሰባ ረግጦ ወጣ

ኢሕአፓ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ካደረጉት ወይይት ረግጦ መውጣቱን የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ሚስጥረሥለሴ ታምራት ለዋዜማ ተናግረዋል። የፓርቲው ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው የወጡት፣ ዐቢይ ለአራቱም ተወካዮች ጥያቄ የማቅረብ ዕድል ሳይሠጡ ለሌሎች ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት በመጀመራቸው መኾኑን ሚስጢረሥላሴ አስረድተዋል። ተወካዮቹ ከአዳራሹ ሲወጡ፣ የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዓለምጸሐይ ጻውሎስ ለምን ረግጠው እንደወጡ እንደጠየቋቸውና ምላሽ እንደሠጡ ታውቋል። በውይይቱ በትክክል ስንት ፓርቲዎች እንደተሳተፉ ለጊዜው ማረጋገጥ አልተቻለም።