አቶ ለማና አቶ ገዱ ሲወዳደሩ #ግርማ_ካሳ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ሕወሃት ሳትከረበት በፊት ትልቅ ትግል የነበረባቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነበሩ። ከአቶ ለማ መገርሳ ጋር ሲነጻጸሩ።

አቶ ለማ በኦህዴድ ውስጥ ያሉ የሕወሃት አገልጋዮችን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጥርተው( ብዙም ስላልነበሩ) ኦህዴድ ከሕወሃት ገለልተኛ እንዲሆን በቀላሉ ነበር ማድረግ የቻሉት። አቶ ገዱ ግን ብአዴን ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ ህወሃትና አፍቃሪ ህወሃት ስለነበሩ እንቅስቃሴያቸው በገመድ ላይ እንደመራመድ ነበር። እንደውም አንድ ወቅት የስራ አስፈጻሚ ውስጥ የሞሉት አፍቃሪ ህወሃት የብአዴን አመራሮች፣ አቶ ገዱን እስከማንሳትና ራሺያ አምባሳደር አድርጎ እስከመሸኘት የወሰኑበትም ጊዜ ነበር። ያኔ ለአቶ ገዱ በጣም ከባድ ነበር።

አሁን ደግሞ የተገላቢጦሽ ሆኗል። በአማራ ክልል ትልቅ መረጋጋት አለ። ለተወሰኑ ቀናት በመተማ አካባቢ ሕወሃት አስርጎ ባስገባቸው አንዳንድ ቡድኖች ⶭግር ተፈጥሮ ነበር። ከዚያ ውጭ ግን በአሁኑ ወቅት መረጋጋት የት ነው ያለው ቢባል በአማራ ክልል ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ አብን፣ ግንቦት ስባት፣ ሰማያዊ…በነጻነት ይንቀሳቀሳሉ። የአማራ ቴሌቪዥን በአሰደናቂ ሁኔታ ገለልተኛ ነው።

አቶ ለማ መገርሳ ግን በጣም እየተንገዳገዱ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። በኦሮሞ ክልል በፍጹም መረጋጋት ብሎ ነገር የለም። ሕግና ስርዓትን ማስጠበቅ አልቻሉም። የቀበሌ፣ ወረዳ፣ ዞን የኦህዴድ አመራሮች እነ አቶ ለማን  አይሰሙም፤ የሚሰሙት እነ ጃዋርን ነው። አቶ ለማ ወለጋንና ሃረርጌ ማስተዳደር ትልቅ ፈተና ሆኖባቸዋል። እነ ጃዋርና ኦነጎች ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ነው የከተቷቸው። አቶ ለማ የሚሰሩትን እያፈረሱባቸው። የኦሮሞ ማህበረሰብ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር በማቀራረብ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በኢንቨስትመንት በስራ እድል የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ አቶ ለማ ሲደክሙ ፣ ኦነጎችና ጃዋሪያን ደግሞ ጥረታቸው ላይ ዉሃ ይከለብሱበታል።

አሁን አሁን ሳስበው አቶ ለማ በጣም እያሳዘኑኝ መጥተዋል። እረም መድሃኔአለም ብርቷቱን ይስጣቸው!!!