ጥረህ ግረህ ብላ
የቤት ሠራተኛ፣ ፓይለት ፕሮፌሰር
የፍ/ቤት ዳኛ መሃንዲስ ሚ/ር
በሥራ አደባባይ አንዱ ካንዱ ሳይበልጥ
የዋሁ ሲፈጋ ጮሌው ሳይቀመጥ፤
የበኩር ልጅ ሳይሆን የፓርቲ ደጋፊ
የዘር ሃረግ ጎታች የጎጥ ተለጣፊ
ሠው በሠውነቱ የተከበረበት
አንዱ ከፍ አንዱ ዝቅ ብሎ ያልታዬበት…
ጥረህ ግረህ ብላ
የቤት ሠራተኛ፣ ፓይለት ፕሮፌሰር
የፍ/ቤት ዳኛ መሃንዲስ ሚ/ር
በሥራ አደባባይ አንዱ ካንዱ ሳይበልጥ
የዋሁ ሲፈጋ ጮሌው ሳይቀመጥ፤
የበኩር ልጅ ሳይሆን የፓርቲ ደጋፊ
የዘር ሃረግ ጎታች የጎጥ ተለጣፊ
ሠው በሠውነቱ የተከበረበት
አንዱ ከፍ አንዱ ዝቅ ብሎ ያልታዬበት…
እዚህ አሜሪካ ኤሌክትሮኒክስ የተገጠመላቸው የነዳጅ ማደያ ሮቦቶች የቀዳንውን ነዳጅ መጠን አሳይተው ዋጋ ይቀበሉን እንጅ ልክ እንደ ሰው ይሸውዳሉ እየተባለ ይወራል። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…
የቤልጅጉ ንጉሥ ሊዎፖልድ 2ኛ የአፍሪቃን አህጉር ለመቀራመት በ1884 ዓ.ም የበርሊን ኮንፈረንስ እንደጠሩ ይነገራል። በዚህ ኮንፈረንስ ዩናይትድ ስቴትስ ስትቀር ሌሎች ታላላቅ የአውሮፓ መንግሥታት ተወካዮቻቸውን ልከዋል። በሙሉ ለማንበብ ከፈለጉ እዚህ ይጫኑ…
ሆድዎትን በዕጅዎ ደግፈው በሁለቱም ዓይኖችዎ ጣምራ የዕንባ ዘለላዎች እስከሚወርዱ ድረስ ከትከት ብለው እንዲስቁ ምክንያት የሚሆን ጓደኛ ካለዎት እንደ ግል ሃኪምዎ ይቁጠሩት። ሳቅ ወይም ቀልድ ጤናማ ህይዎት ለመምራት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ምርምሮች አረጋግጠዋል። ሳቅና ጤንነት ምን አገናኛቸው የሚል ጥያቄ ማንሳትዎ አይቀርም። …
በአጼ ኃ/ሥላሴም ሆነ ከዚያ በፊት ባላገር መብቱን ያስከብር የነበረው ከመንግሥት በሚመደብለት ፖሊስ ወይም ነጭ ለባሽ አልነበረም። በጉልበቱ ነው። Read more…
ሃያ አራት የህንድ ዜጎች ኢትዮጵያ በሚገኙ የቆዳና ሌጦ ፋብሪካዎች ተቀጠሩ ተባለ። ለማንበብ እዚህ ጠቆም ያድርጉ…
ብኩንነታቸው ላይ አፅንዖት ለመስጠት ዲስ-ግሬስ የሚል ቅፅል የተሰጣቸው የሮበርት ሙጋቢ ባለቤት- ግሬስ ሙጋቢ የባለቤታቸውን 85ኛ የልደት በዓል በ2009 አክብረዋል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ሚስ ሙጋቢ የሚጠቀሙባቸው መጫሚያዎች ከ3000 በላይ ሲሆኑ እንደየቀለማቸው የፅዳት ቀለም ሳይኖራቸው አይቀርም። ልዕልቷ በየቀኑ አዲስ ጫማ እንዲጫሙ ቢደረግ …
ሰሞኑን በኢትዮሜዲያ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የድረሱልኝ ጥሪ ሳነብ አዘንኩኝ። የኦርቶዶክስ ሃይማኖትና የሳይንስ ተቋማት ኮሶ ከተጣባቸው ቆይቷል። አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ሆነው ሲሾሙ ማልቀስ፣ ምህላ መግባት፣ ኢትዮጵያ ታበጽህ ዕደዊሃ ሃበ እግዚአብሄር ማለት ያን ጊዜ ነበር። አቡነ ጳውሎስ የክርስትና ዕምነት ተከታያቸውን የመንግሥተ …
ከአንድ መቶ ስልሳ ዓመት (1850 ዓ.ም) አንስቶ የተመዘገበውን የዓለማችን አማካይ ሙቀት መሠረት በማድረግ ያለፈው 1998 ከፍተኛው ሙቀት የተከሰተበት ሲሆን 2010 ደግሞ ሁለተኛ ሆኗል። የብሪታኒያ ኢንስቲትዩት ሰሞኑን እንዳስታወቀው ይህ መረጃ የዓለም አየር ንብረት ቀስ በቀስ እየተዛባ መምጣቱን ይጠቁማል ብሏል። ከታች …
የቤላረስ ተወላጅ በሆኑት ኢቭጀኒ ሞሮዞቭ ኢንተርኔትና ተምኔታዊ ግንዛቤው፡ የኢንተርኔት ነፃነትና አሉታዊ ተፅዕኖ በሚል ርዕስ የተጻፈ 408 ገፆችን ያካተተ አዲስ መጽሓፍ ገበያ ላይ ውሏል።
በሽህ የሚቆጠሩ የኢራን ወጣቶች ሰኔ ወር 2009 በተደረገው ምርጫ ድምፃችን ተነጥቋል በማለት ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ተቃዋሚዎችን አስመልክቶ …
ፍሪደም ሀውስ የተሰኘው ግብረ ሠናይ ድርጅት የ2010 ዓለማቀፋዊ የፖለቲካ ነጻነትና የሲቪል መብት መከበር አስመልክቶ በ194 አገሮች ላይ ያካሄደውን ጥናት ይፋ አድርጓል። ከፍተኛ የፖለትካ ነጻነትና የሲቪል መብቶች ጥሰት የሚታይባቸው አገሮች 7 ነጥብ ሲሰጣቸው በአንፃሩ ከፍተኛ የፖለቲካን የሲቪል ህብረተሰብ ነፃነት የተከበረባቸው ደግሞ …
ንብ ብዙ ጊዜ የታታሪነት ምሳሌ ሆና ትጠቀሳለች። አበቦች ቀስማ ማር ለመፈብረክ ጥበብ የተካነችውን ንብ ወያኔ በ2005ቱ ብሔራዊ ምርጫ አርማው አድርጎ ተጠቅሞባታል። የኢትዮጵያ ህዝብና ንብ ሆድና ጀርባ የሆኑበት ጊዜ ቢኖር ያን ጊዜ ብቻ ነው። በተረፈ ግን “ይሠሯል ከልብ እንደንብ” እየተባለ ሥራ …
<table bgcolor=”blue”>
<tbody>
<tr>
<th>የፓስፊክ ዕንቁራሪት (ቡናማ)</th>
<th>የፓስፊክ ዕንቁራሪት (ግራጫ)</th>
<th>የፓስፊክ ዕንቁራሪት (አረንጓዴ)</th>
</tr>
<tr>
<td></td>
<td><a href=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/220px-pseudacris_regilla_side_wb.jpg”><img title=”220px-Pseudacris_regilla_side_wb” src=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/220px-pseudacris_regilla_side_wb.jpg” alt=”” width=”150″ height=”155″ /></a></td>
<td><a href=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/400px-pacifictreefrog2kjfmartin.jpg”><img title=”400px-Pacifictreefrog2kjfmartin” src=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/400px-pacifictreefrog2kjfmartin.jpg” alt=”” width=”150″ height=”155″ /></a></td>
</tr>…
ንብ ቀፎው ሲነካበት ግው ብሎ ይተማል። ፉክክር የለም። አባቶቻችን ይህን ፈለግ በመከተል ዳር ድንበራቸው በተደፈረ ቁጥር ልክ እንደንብ በመቆጣት ግዳይ ጥለው አልፈዋል። እነሱ ሞተው እኛን አኖሩን ማለት ነው። እንዲህ ዓይነቱ መስዋዕትነት በተለያዩ የ እንስ ሳት ዝርያ የሚስተዋል ሲሆን በዕፅዋት ዓለም …
ቹክቺ የተባሉት ዘላኖች ሩሲያ በሚገኘው ቹኮትስኪ የባህር ሠላጤ ይኖራሉ። እነዚህ ሰዎች ከጥንት ጀምሮ እያደኑ ወይም በባህር ላይ እያሠገሩ የኖሩ ሰዎች ናቸው። የሶቬት ህብረት በ1920ዎቹ የአምራቾች የህብረት ሥራ ማህበር እንዲያቋቁሙ ያስገደዳቸው ሲሆን የሶቬትን ውድቀት ተከትሎ የህብረት እርሻው ፈርሷል። የፖሊሲው ውጤት? አብዛኞቹ …
የተወሰኑ ሰዎች በጮርቃነቱ የተነቀለ ካሮት (Baby carrot) የተሻለ የምግብ ይዘት፣ ጣዕምና መስህብ አለው ብለው ስለሚያምኑ ከጎመራው ካሮት በላይ አዘውትረው ይመገቡታል። ይህን የተመጋቢ ምርጫ ልብ ያለው ማይክ የተባለ የካሊፎርኒያ ገበሬ አንድ ቀን ለዬት ያለ ሃሳብ መጣለት። መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የጎመራ ካሮት …
የምንበላው ምግብ የመጠጥ ውሃችን
የምንኖርበት ቤትና ቀያችን
የመዝናኛ ሥፍራ የትምህርት ቤታችን
አላቸው እንደምታ ለጤንነታችን።
ያቆሸሽነው ሠፈር የበከልንው ውሃ
አድርጎን ይኖራል የጤንነት ድሃ።
ታዳጊ ህጻናት፣ ጎልማሳው ወጣቱ
የሚለከፉብን ሴት፣ ወንድ አዛውንቱ
መርገም እኮ አይደለም ከሰማይ የመጣ
የጽዳት ጉድለት ነው የአካባቢ ቁጣ።…
ከወያኔ ዛፍ የወይን ፍሬ እንደማይለቀም ሁሉ የውሸት ምንጭ ከሆነች ነፍስ ሃቅ አይፈልቅም። የምትዋሽ ነፍስ የህሊና ክስ ስለሚመሰረትባት ሁልጊዜ ታፍራለች። ከገሃዱ ዓለም ጋር ባለው ቁርኝት የተነሳ ዕውነትን ለማስታወስ ብዙ አንቸገርም። ውሸት ግን የራሳችን ፈጠራ በመሆኑ ማስታወስ እንችል ዘንድ ዕንቅልፍ አጥተን መሥራት …