ዕንቁራሪቶችና ሥነ ምህዳር
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
<table bgcolor=”blue”>
<tbody>
<tr>
<th>የፓስፊክ ዕንቁራሪት (ቡናማ)</th>
<th>የፓስፊክ ዕንቁራሪት (ግራጫ)</th>
<th>የፓስፊክ ዕንቁራሪት (አረንጓዴ)</th>
</tr>
<tr>
<td></td>
<td><a href=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/220px-pseudacris_regilla_side_wb.jpg”><img title=”220px-Pseudacris_regilla_side_wb” src=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/220px-pseudacris_regilla_side_wb.jpg” alt=”” width=”150″ height=”155″ /></a></td>
<td><a href=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/400px-pacifictreefrog2kjfmartin.jpg”><img title=”400px-Pacifictreefrog2kjfmartin” src=”http://worku.files.wordpress.com/2011/01/400px-pacifictreefrog2kjfmartin.jpg” alt=”” width=”150″ height=”155″ /></a></td>
</tr>
</tbody>
</table>
ቀበና ወንዝ ላይ ምርምር ሳደርግ ከጥናቱ ግኝት በላይ የተማርኩት እዚያው ሠፈር ተወልዶ ካደገ ሠው ጋር ባጋጣሚ ተገናኝተን ካደረግንው ውይይት ነው። “ቀበና ልጆች ሆነን” ብሎ ጀመረልኝ “መሸት ሲል የዕንቁራሪቶች ድምፅ የወንዙን ፍሰት ተከትሎ ያስተጋባ ነበር። አሁን ያ ድምፅ በፍጹም አይሰማም። ስለሱ ከሆነ ጥናትህ ብዙ አትድከም። ቀበና ወንዝ እስከወዳኛው ተለውጧል” ብሎ ተከዘ። እኔም በአስተያዬቱ ተመስጨ በወቅቱ የተሰማውን ስሜት ተጋራሁት። በትክክል እንዳስቀመጠው የዕንቁራሪት ዝርያ ቀርቶ ጥቃቅን ነፍሳት ለመሰብሰብ ተሳነኝ። በብዛት ያገኘሁት ፍጡር ቢኖር ሄሞግሎቢን የተባለውን ንጥረ ነገር በሰውነታቸው ውስጥ በገፍ ማከማቸትና የተገኘችውን ትንሽ አየር በመጠቀም መኖር የሚችሉ የአንድ ዝርያ ትላትሎችን ነው። እነሱ ደግሞ ጨርሰው በጠፉበት አካባቢ ከወንዙ ደለል ውስጥ ተሸጉጦ ትልቅ ቱቦ መሰል ነገር አየር ሊደርሰው በሚችልበት የውሃ ጥልቀት በመላክ መተንፈስ የሚችል ልዩ ፍጡር ብቻ ነው። የቀበና ወንዝ በየቀኑ ከፋብሪካ፣ ከቤት፣ ከአሊቤርጎ፣ ከሆቴል በሚለቀቅበት ቆሻሻ የተነሳ ለፍጡራን ከለላ ሊሆን ቀርቶ ለራሱም ሊሆን አልቻለም። ውሃ ስቀዳ ጭቅቅት፣ እንሣት ሳጠምድ ኮንዶም፣ ኦክሲጅን ስለካ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ነው ያገኘሁት። የወንዙ ሽታ ነፍሰጡር ሊያስጨነግፍ ይችላል። ዕንቁራሪቶች ጠፍተዋል፣ የቀበና ወንዝ ዜማቸውም ነበር ሆኗል።
ታዲያ ዕንቁራሪቶች ቢጠፉ ምንድነው? ሊባል ይችላል። ትልቁ ችግር ሲጠፉ ለብቻቸው አይጠፉም። ይዘውን ይጠፋሉ የሚል መላ ምት አለ። እሱን ወደኋላ እንመለስበታለን። ለጊዜው ግን እስቲ ከላይ በሥ ዕሉ ላይ ስለተመለከተው የፓስፊክ ዕንቁራሪት ትንሽ ላውጋችሁ። በጣም የሚደንቀው ነገር ይህ ዕንቁራሪት የወቅቶችን መፈራረቅ ተከትሎ እንደ እሥሥት ቀለሙን የመለዋወጥ ዐቅም አለው። የመጀመሪያው ቡናማ ቀለም ከአካባቢው ጋር በግሩም ሁኔታ እንዳመሳሰለው ልብ ይበሉ። ይህ ጥበብ የተፈጥሮ ጠላቶቹ በቀላሉ እንዳያጠቁት ይጠቅመዋል። ግራጫ ቀለሙም ቢሆን በመጠኑ አካባቢው ጋር ያዛመደው ሲሆን ተክሎች ቅጠላቸው ለምልሞ እሱን የሚያሳጡት ሆኖ ሲያገኘው ቶሎ ብሎ አረንጓዴ ቀለም ይላበሳል።
ወደ አገራችን እንመለስ። በቀበና ወንዝ ያውካካ የነበረው የዕንቁራሪት መንጋ እልም ብሎ ሲጠፋ እኛን ባያስጨንቀንም ፈረንጆች ግን የሚራቡበትን ጊዜ በቀናት አራዘሙብን ብለው ሰሞኑን ተፈጥሮ በሚለው ሳይንሳዊ መጽሄት ላይ ሥጋታቸውን ለህትመት አብቅተውታል። ለ30 ዓመታት የዘለቀው ጥናት የተካሄደው በደቡብ ካሮሊና ሲሆን የሌሊቱ አማካይ ሙቀት በ1.2 ድግሪ ሴንቲግሬድ በመጨመሩ የተነሳ እነዚህ እንቁራሪቶች የመራቢያ ጊዜያቸውን ወደኋላ ወይም ወደፊት ገፍተውታል።
የፓሲፊክ ዕንቁራሪቶች በውሃ ሥነ ምህዳር ውስጥ ያላቸው ሚና እንደ ማዕዘን ድንጋይ የሚታይ ነው። የማዕዘን ድንጋይ የተሸከመው ክብደት ከሌሎቹ ድንጋዮች ያነሰ ቢሆንም እሱ ከተነሳ ጠቅላላ ግንቡ ይፈርሳል። ዕንቁራሪቶቹም በምግብ ትሥሥሩ ውስጥ ተመሳሳይ ሚና ስለሚጫወቱ የነሱ መጥፋት ከላይም ሆነ ከታች ያለውን የምግብ ሰንሰለት አደጋ ላይ ይጥለዋል። በ1990ዎቹ አካባቢ የተደረገውን ጥናት ምርኩዝ በማድረግ በተወሰደ ዕርምጃ በሎንዶን የሚገኘው የቴምስ ወንዝ አሁን የተለያዩ ዕንቁራሪቶች፣ የዓሣ ዝርያዎችና ሌሎች እንስሳት መራባት እየጀመሩ እንደሆነ ሰሞኑን ተገልጿል። ከዚህ የምንረዳው ቁም ነገር አሜሪካዊ ወይም እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው ዕንቁራሪት የመኖር ተስፋ ሲለመልም የቀበናው ኢትዮጵያዊ ዕንቁራሪት ግን አንድም ጨለምተኛ ሆኖ ላይመለስ ተሰዷል፣ አለዚያም ዝርያው ከጠፋ ዓመታት ተቆጥረዋል ማለት ነው። ፍየል ትወልድ መንታ አንዱን ለወናፍ አንዱን ለመጣፍ ተብሎ የለ!
ምንጭ፡ http://www.nature.com/nature/journal/v468/n7327/pdf/4681004b.pdf
ወርቁ ለገሠ (01/01/11)