የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡
ኮንፌዴሬሽን ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት እንደሆነ የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል፡፡

ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው ብለዋል፡፡
ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል፣ ልብስ ይለብሳል ፣ ህክምና ይሄዳል ብለዋል፡፡
ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ያሉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉ ጥያቄ